የቪኦኤ ይዘጋ ዜና እንደ “ውሾች በመርዝ ተገደሉ ያክል እንኳ ስፍራ አላገኘም” ሲሉ ግርምታቸውን የሚያካፍሉ ጥቂት አይደሉም፡፡ ለጊዜው ቢቢሲ አማርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛን በመተው ቪኦኤና ጀርመን ድምጽ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያቋቋማቸውን አካል ጥቅምና ማናቸውም ፍላጎት ለመተግበር፣ ለማስጠበቅ፣ ለመከላከል ወዘተ የተቋቋሙ እንደመሆናቸው ዜናው ትልቅ ትርጉም እንዳለው እነዚሁ ክፍሎች ይገልጻሉ፡፡
ቢቢሲ፣ ሌሎች በማሜሪካ ተቋማት የሚደጎሙ “ነጻ መሳይ” ሚዲያዎችን ጨምሮ የሚዲያዎቹ ባለቤቶች ኢትዮጵያ ላይ ጥቅማቸውን አስልተው ለሚጫወቱት ማናቸውም ዓይነት ግልጽና ድብቅ ጨውታ የሚጠቀሙት በዜግነት ” ኢትዮጵያዊ” የሆኑትን መሆኑ ጉዳዩ በሚገባቸው በኩል ዜናው መጨረXአው ምን ሊሆን እንደሚችል እየተከታተሉ ነው፡፡
ከላይ የተባሉት አስተያየቶች እየተደመጡ ያሉት በፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የመንግሥት ብቃት መሥሪያ ቤት (Department of Government Efficiency – DOGE) የኃላፊነት ሹመት የተሰጣቸው የምድራችን አንደኛ ቱጃር ኤሎን መስክ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ (ቪኦኤ) እንዲዘጋ ሲሉ ገጻቸው በይፋ ማስታወቃቸውን ተከትሎ ነው።
በአዲስ አበባ ባለቤት አልባ ውሾች በገፍ እየተፈለፈሉ አላፊ አግዳም ላይ እያደረሱ ባለው ጉዳት፣ በበሽታ የመለከፋቸው ጣጣ፣ የጤናና ተመሳሳይ ጉዳዮች ያማረራቸው “የት ነው የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ” በሚል ከፍተኛ ትችትና ውግዘት ሲያሰሙ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ ዘግይቶም ቢሆን ያደመተው ቢሮው በርካታ ባለቤት አልባ ውሾችን ባስወገደበት ወቅት የተሰማው ተቃውሞ ከቪኦኤ የመዘጋት ዜና የበለጠባቸው ሚዲያዎች በርካቶችን አስገርሟል፡፡
ሰብለወርቅ ኃይሉ እንዳለችው፣ ጤነኛ አእምሮ ላላቸውና በውል ኢትዮጵያዊ ነን ለሚሉ ቪኦኤ እንዲዘጋ ያበሰረው ዜና ላይ በሚዲያዎቻቸው የውይይት አጀንዳ በመክፈት ያለማቋረጥ ዜናውን ህዝብ ጆሮ ማስረሽ ይገባቸው ነበር፡፡
“የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮና የነጻ አውሮጳ ሬዲዮ (Radio Free Europe/Radio Liberty) በአሜሪካውያን ግብር ከፋዮች የሚደጎሙ የሚዲያ አውታሮች ናቸው፤ በእነዚህ አውታሮች ውስጥ የሞሉት የግራ ክንፍ አክቲቪስቶች ናቸው፤ … ከነዚህ ጋዜጠኞች ጋር ለዓሥርተ ዓመታት ሠርቻለሁ፤ ለእነርሱ ሥራው ያለፈውን ዘመን ቅርስ የማስጠበቅ ዓይነት ነው፤ መንግሥት የሚደጉማቸው የሚዲያ አውታሮች አያስፈልጉንም” ሲሉ የፕሬዚዳንት ትራምፕ የልዩ ተልዕኮዎች ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ሪቻርድ ግሬኔል አስታውቀው ነበር፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ በመላው ኣለም በ48 ቋንቋዎች ይቀርባል። በተገባደደው የ2024 በጀት ዓመት በጀቱ 944 ሚሊዮን ዶላር ጠይቆ 857 ሚሊዮን ዶላር እንደተፈቀደለት መረጃዎች ይናገራሉ፡፡ የመዘጋቱ ዜና ይፋ የሆነው ቪኦኤ ይህን ያክል በጀት እያነከተ የሚሰራው ኝ እንደ አገር ረብ የሌለው ነው በሚል እንደምታ ነው፡፡ እንደውም በሌሎች አገራት ውስጥ መንግስት የመገልበጥና አመሽ የርማስነሳት ዓላማ አንግቦ የሚሰራ አገራትን ከሚያፈርሱና ከሚያተራምሱ ሚዲያዎች መካከል የሚመደብ እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት ትችት የሚሰነዘርበት ነው፡፡
የፕሬዚዳንት ትራምፕ የልዩ ተልዕኮዎች ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት ሪቻርድ ግሬኔል የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ ኤሎን መስክ በኤክስ ገጻቸው “እኔም እስማማለሁ፤ መዘጋት ነው ያለባቸው፤ አውሮጳ አሁን ነጻ ሆናለች፤ ማንም የሚያዳምጣቸው የለም፤ እዚያ የተሰገሰጉት አክራሪ የግራ ክንፍ ጽንፈኛ ዕብዶች ናቸው። ስለ ራሳቸው ነው እያወሩ ያሉት ግን ለዚህ ተግባራቸው አንድ ቢሊዮን የአሜሪካንን ግብር ከፋይ ገንዘብ በየዓመቱ ያቃጥላሉ” በማለት ፍሬ ቢስ ተቋም መሆኑን ገልሸዋል፡፡
ከጥቂት ቀናት በፊት የአሜሪካ መንግሥት የተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ለተለያዩ የሚዲያ አውታሮች በየዓመቱ የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ይፋ አወጥቶ ነበር። ይህ ለየሚዲያው ለአባልነት (subscription) በሚል ከመንግሥት የሚከፈለው ገንዘብ በተለይ ባለፈው ሳምንት ለፖለቲኮ (Politico) ለተባለው ሚዲያ በ2024 ዓም ከስምንት ሚሊዮን ዶላር በላይ (ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ) መከፈሉ ይፋ ከተደረገ በኋላ መንግሥት ለማንኛውም ሚዲያ የሚከፍለው ክፍያ መቆም አለበት ሲባል ቆይቷል።

በዚህ ምክንያት ከፖለቲኮ በተጨማሪ ለአሶሺየትድ ፕሬስ ፣ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ወዘተ የአሜሪካ መንግሥት የሚፈጽመው (የsubscription) ክፍያ መቆም እንዳለበት ኤሎን መስክ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ልዩ መልዕክተኛው “እንዲያውም ሳይውል ሳያድር ነው መቆም ያለበት” ሲሉ የኤሎን መስክን አቋም አጉልተው ተናግረዋል።
የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ በ1942 ዓም (እኤአ)፣ የነጻ አውሮጳ ሬዲዮ ደግም በ1949 ዓም (እኤአ) የተቋቋሙ ሲሆን ሁለቱም በአሜሪካ የስለላ ድርጅት ሲአይኤ የሚደጎሙ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተደጋጋሚ ከደረሰባቸው ነቀፋ በኋላ ግን የአሜሪካ መንግሥት በቀጥታ የሚደጉማቸው የሚዲያ ተቋማት ሆነዋል።
የነጻ አውሮጳ ሬዲዮ በተለይ ትኩረት የሚያደርገው በምሥራቅ አውሮጳ፣ ማዕከላዊ ኢሲያ፣ ካውኬዢያ (ከቀድሞ የሶቪየት ኅብረት የተገነጠሉት አገራት) እና በመካከለኛው ምስራቅ ነው። ሬዲዮ ጣቢያው ለ23 አገራት በ27 ቋንቋዎች ፕሮግራሙን የሚያቀርብ ሲሆን ዓመታዊ በጀቱ ከመቶ አርባ ሚሊዮን ዶላር በላይ (ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ) ነው።
የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ በበርካታ አገራት የፖለቲካ ነውጥ እንዲነሳ በመደገፍና በማስተባበር እንዲሁም የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማድረግ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ተቋም ነው። ሠራተኞቹም በዚሁ የተቋሙ መርህ መሠረት የተሰጣቸውን ወይም የተላለፈላቸውን የቀጣሪው አገር አቋም ለማራመድ ወስነውና ለሕጉ ፈርመው የሚሠሩ ናቸው። አገራቸው ላይም ቢሆን የሚፈጸም ማንኛውም የአሜሪካ ፍላጎት ተግባራዊ ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ በተቋሙ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ይምላሉ፡፡ አማርኛ፣ ትግርኛና ኦሮምኛ ላይ የሚሰሩት የቪኦኤ ተቀጣሪ ዜጎች በዚሁ ውል መሰረት መቀጠራቸው ልብ ይሏል፡፡
እንግዲህ የቪኦኤ ይዘጋ ዜና ትርጉሙ ከፍ ያለ እንደሆነ የሚሰላው በዚሁ መነሻ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ላይ ከደርግ ጊዜ ጀምሮ ቪኦኤ በገዛ ዜጎቻችን አንድበት ምን ሲፋሽም እንደነበር የሚያስታውሱ ከስሌት በዘለለ በርካታ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡
የቪኦኤ መዘጋት ዜና በውሾች መገደል ዜና እንዲሸፈን የተሞከረው፣ የቪኦኤ መዘጋትን ከያዙት ዓላማ ጋር በማዛመድ ጉዳቱ የገባቸው ወገኖች እንደሆኑ የሚገልጹ፣ ቪኦኤ በገዛ አገራችን ዜጎች በዘመነ ደርግና አሁን ደግሞ በቅርቡ ከትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ጋር በተደረገው የህግ ማስከበር ጦርነት ወቅት ሲያቀርቡ የነበረውን ዘገባ በማስታወስ እንደ በረከት ይቆጥሩታል፡፡
በጣሊያን ወረራ ወቅት ጀኞች “እምቢ ለአገሬ” በማለት ወራሪውን ኃይል ሲገጥሙ፣ በተቃራኒ ለጣሊያን አድረው የአገራቸውን ጥቅምና ክብር አሳልፈው የሰጡ መኖራቸውን በማንሳት የሚዲያውን የዘመኑ ተጋድሎም በዚሁ ስሌት የሚያሰሉ ጥቂት አይደሉም፡፡
አቶ ሰብስቤ ኃይሉ ከሁለት ዓመት በፊት በዛጎል ዜና ላይ “ነጮቹ በየትኛውም መስፈርት ይህን ሚዲያዎችን በየአገራቱ ቋንቋ የሚያራቡት በአገራቱ ህዝብ ጥቅም ላይ ተመስርተው ለማገልገል ሳይሆን ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ነው፡፡ ይህም የሚሆነው ለጥቅም ሲሉ አገራቸውን ለሌሎች ጥቅም አሳልፈው በሚሰጡ ‘ጋዜጠኛ ተብዬዎች’ ነው” በማለት መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
የሚዲያዎቹ ተፈጥሮ የገባት ሩሲያ ባለፈው ዓመት የነጻ አውሮጳ ሬዲዮን “የማያስፈልግ ድርጅት” ብላ በመሰየም የአገሪቱ የፍትሕ ሚኒስቴር መ/ቤት በሬዲዮ ጣቢያው የሚሠሩትን ጋዜጠኞችና ሌሎች ሠራተኞች፣ ለጣቢያው የገንዘብ ድጎማ የሚያደርጉትንና በሚዲያው ቃለመጠይቅ የተደረገላቸውን ሁሉ በማጋለጥ ክስ መመሥረቷን የተለያዩ ሚዲያዎች አሰራጭተው ነበር፡፡ ይህን የሩሲያን ዜና ተከትሎ ” የትህነግ ጦር አዲስ አበባ ዙሪያ ደረሰ” በማለት ከሌሎች ተልእኮ ያነገቡ ሚዲያዎች ተከትለው በተለያዩ ቋንቋዎች የፈጠራ ዜና ሲሰሩ የነበሩትን ከሶ ከአገር ውስጥ እስከማባረር የሚደርስ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ በወረራው ወቅት የነበረውን የሚዲያ ዘመቻ የሚቃወሙ ዜጎች መንግስትን ሲወቅሱ ነበር፡፡
አንድ ሊሸፈን የማይገባው እውነት ቢኖር “ይህ የአሜሪካንን መንግሥት አቋም የሚያንጸባርቅ ነው” በሚል በቪኦኤ በየቀኑ በአማርኛ በሚተላለፈው ፕሮግራሙ ላይ የሚቀርበው ርዕሰ አንቀጽ ምስክርነት ነው፡፡ ይህ ማለት ፕሮግራሙ የሚያራባው ማናቸውም ዝግጅቶች የአሜሪካ አቋም ላይ ተቸክሎ እንጂ በሌላ በማናቸውም አግባብ እንዳልሆነ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ቪኦኤ በቀጠራቸው ኢትዮጵያዊ ዜኘት ያላቸው ሰራተኞቹ አማካይነት ሸረ ኢትዮጵያና ኢየኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳ መረጃ ሲያሰራጭ ኖሯል፡፡ መንግስት አፍርሷል፡፡ በቅርቡም ለሁለተኛ ጊዜ መንግስት ሊገለብጥ ከሌሎች ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ሚዲያዎች ጋር በመናበብና በመቀባበል ሰርቷል፡፡ ወደፊትም አሜሪካን እስከጠቀመ ድረስ ይሠራል፡፡
የደርግ መንግሥት እንዲወድቅና የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ትህነግ ወደ ሥልጣን እንዲመጣ ቪኦኤ ከሲአይኤ ጋር በመሆን በእነመለስ ዜናዊ የሚመራውን የትግራይ ነጻ አውጪ ቡድን ሲደግፍና የሚዲያ ሽፋን ሲሰጣቸው መቆየቱን ማስረጃ ጠቅሰው የሚናገሩ፤ “ተግባሩ ለገንዘብ ሲባል የአገር ጥቅም፣ ሉዓላዊትና ክብርን መሸጥ በመሆኑ በአደባባይ እንደ ሌሎች የሽብርና ክህደት ወንጀሎች በእኩል ተቆጥሮ ሊፈረጅ ይገባዋል” በሚል ክስ ሲያሰሙ መቆየታቸው ቀደም ካሉ ጹሁፎችና ሪፖርቶች መረዳት ይቻላል፡፡
ትህነግ በሰሜን ዕዝ ላይ እጅግ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከፈጸመ በኋላ በተገባው የኅልውና ጦርነት ቪኦኤ የመንግሥትን ኃይል የሚያዳክም፣ በተቃራኒው ደግሞ ትህነን የሚደግፍ ዘገባ በተደጋጋሚ፣ በሥልትና በመመጋገብ ኢትዮጵያና ሕዝቧ ላይ ክፉ የፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ተልዕኮውን ሲፈጽም እንደቆየ ማስተባበል በማይቻልበት ደረጃ ለታሪክ ተቀምጧል፡፡ ይህንኑ ሲዘግቡ የነበሩትም የዚህ ታሪክ ተዋኛን ሆነው ይኖራሉ፡፡
የኢትዮጵያን ማናቸውንም መልካም ዜናዎች በሤራ በማጀል የሚያቀርበው ቪኦኤ፣ ኤለን መስክ እንዳሉት በውስጡ “የተሰገሰጉት” አማርኛ፣ ትግሪኛና ኦሮሚኛ ተናጋሪ ቅጥረኛ “ኢትዮጵያውያን” አማካይነት ምን ያህል አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ እያመረቱ ለማኅበራዊ ሚዲያ እንደሚቀልቡ በወጉ ለሚረዱ የመዘጋቱ ዜና የላቀ ትርጉም የሰጣቸው በዚሁ መመዘኛቸው ነው፡፡
ህዝብን የሚያስጨርሱና ለህዝብ መፈናቀል ዋና ተጠያቂ የሆኑትን አደባባይ በማቅረብ ነጻ የማውጣት፣ ዕውቅና እንዲያገኙ የማድረግና ያጠፉትን ከህሊና ሊጠፋ የማይችል ጥፋት እንዲያስተባብሉ መድረክ በመስተት ስልታዊ ዝግጅቶችን ሲያሰራጭ የነበረው፣ ከላይ የተዘረዘሩትን ጥቂት ጉዳዮች የተገበረው ቪኦኤ እንዲዘጋ የቀረበው ዕቅድ ሚዛን የደፋውና ውጤቱ አጓጊ የሆነው በዚሁ መመዘኛ ነው፡፡
ይህ ሲባል በጤና፣ በኢኮኖሚና በአንዳንድ ማህበራዊ ጉዳዮች ጥሩ ዘገባ አልቀረበም በሚል ጥቅል ፍረጃ ሳይሆን፣ ጣቢያው በስልታዊ አካሄዱ ከሚረጫቸው፣ ሲረጫቸው ከነበሩትና በተግባር ኢትዮጵያ ላይ ካስደረው ጥቁር ጠባሳ አንሳር በይፋ የመዘጋቱን ዜና በጉጉት ይጠበቃል፡፡
Read This Regime change is old, dangerous trick of US
Over the years, “regime change” has become the main option for the US to maintain its hegemony. It seems the targets were countries with so-called dictatorships. Actually, they were those that opposed US interests, challenged US hegemony, or did not “follow” the US order.