ሰሞኑን በሻዕቢያና በትህነግ ታጣቂ መሪዎች ዙሪያ ሲወጡ የነበሩ መረጃዎች ይፋ እየሆኑ ነው። በአፍሪካ ፖለቲካና ኢኮኖሚ አውዶች ላይ ጥልቅ ትንተና በመጻፍ የሚታወቀው Africa Intelligence/ አፍሪካን ኢንተለጀንስ በዛሬው እትሙ “የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ወደ አስመራ አቅንተው በኤርትራ ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል ተደረጎላቸው ረዥም ሰዓት የፈጀ ውይይት አድርገዋል” ሲል ከዲፕሎማቲክ ምንጮቹ መረጃ ማግኘቱን አስታውቁ ሪፖርት አድርጓል።
አፍሪካን ኢንተለጀንስ (Tigray leaders dangerously torn between Addis Ababa and Asmara ዜናውን እዚህ ላይ ያንብቡ ) ሲል ያሰራጨው ዜና ጉዳዩን በቅርብ ለሚከታተሉ ወገኖች ብዙም እንግዳ ባይሆንም፣ መንግስት በስፋት እየሰራበት ላለው የዲፖሎማሲ አቅጣጫ ታላቅ ተጨማሪ ግብዓት እንደሆነ ተሰምቷል። ዜናው ሻዕቢያ በእነ ደብረጽዩን ለሚመራው ታጣቂ ኃይል የሎጂስቲክ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት መደረሱን ይፋ ካደረገው ግምገማ ጋር የገጠመ ሆኗል።
እነዚሁ ከመቀለ ወደ አስመራ ያቀኑት የአንጃው ሰራዊት አመራር ወኪሎች፣ የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፉወርቂ ጦረንት ሲቀሰቀስ በኤርትራ ምድር እንዳይሆን አስቀድመው በያዙት ዕቅድ መሰረት ጦርነቱን ትግራይና አማራ ክልል ላይ እንዲደረግ ቃል መግባቱ ታውቋል። ይህንኑ ዜና ኢትዮሪቪው ከቀናት በፊት ዘገባ ነበር።
የሻዕቢያ መንግስት ኢትዮጵያ ላይ ታጣቂ በማደራጀት ሰላሟን በማደፍረስ የሚታወቅ በመሆኑ በርካታ ዜጎች “ኢሳያስ በቃው ሊባል ይገባል” የሚል አስተያየት በሚሰጡበት ወቅት በአማራ ክልል ቀውስ እንዲነሳ ቀድሞ የሰራው ሻዕቢያ የኤርትራም ህዝብ አሁን ላይ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተ ቤተሰቦቻቸውን ያገኙ ዲያስፖራዎች እየተናገሩ ነው።
ሻዕቢያ በወልቃይት ላይ ልዩ አጀንዳ እንዳለውና ከትህነግ በላይ ይህን ፍላጎቱን ለማሳካት የጎጃም አካባቢ ፋኖዎችን መያዙን በመረጃም አስደግፈን መዘገባችን አይዘነጋም። ይህንኑ ዜና የሚያጠናክር መረጃ ከትግራይ ይፋ መሆኑ የኢሳያስ አፉወርቂ “አማራን እወዳለሁ” ተረት የጥሪ ደወል ሆኗል። በተፈናቃዮች ስም የሚምለው የትህነግ አንጃ የሚሳካ ከህነ ሻዕቢያ ከወልቃይት ድርሻ እንዲኖረው ከጎጃም ፋኖዎችና ከትግራይ ኃይሎች ጋር ውል መቋጠራቸው ተሰምቷል።
የተለያዩበት ዋና ምክያት ለበርካቶች እንቆቅልሽ ቢሆንም ትህነግ ለሁለት ከተከፈለ በሁዋላ በዶ/ር ደብረጽዩን ከሚመራው ቡድን ጋር የወገኑ ናቸው የተባሉ የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች ከአስመራው መንግስት ጋር ሲመሰጥሩ ከርመዋል። ለዚህም የቪዲዮ ማስረጃ ሳይቀር መንግስት እንዳለው ጠቅሰን ከወራት በፊት አመልክተን ነበር። የተለያዩ የትግራይ ተቃዋሚ አመራሮችና አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን ይህንኑ ዕውነት መመስከሩም የሚዘነጋ አይደለም።
በሽሬ በገሃድ ምሽግ ቁፋሮና የሰራዊት ስምሪት ሲያካሂድ የቆየው የትህነግ ክፋይ ታጣቂ ኃይል፣ ወደ ኤርትራ የሚወስዱ የጥርጊያ መንገዶችን ለሎጂስቲክና ለተለያዩ አጋጣሚዎች ሲገነባ መሰነበቱም ከአይን እማኞች ተሰምቷል።
ይህ ሁሉ ከሆነ በሁዋላ ሻዕቢያ ሴት ወንድ፣ ሽማግሌ ወጣት፣ ጡረተኛ ጎልማሳ ሳይለይ ክተት ማወጁን ከአስመራ ምስክሮች ስማቸውን ሸሽገው ማስታወቃቸውን የተለያዩ ሚዲያዎች አስታውቀዋል። ይህ በኤርትራ ባለስልጣናት ማስተባበያ ያልቀረበበትን የክተት አዋጅ ተከትሎ ነው እነ ምግበና ፍስሃ የተባሉት የትግራይ ሰራዊት አመራሮች ግምገማ አስርገው ወልቃይት ላይ ጦርነት መክፈት እንደ አንድ ህዝብን የሚማርክ ስትራቴጂ አድርገው ሊጠቀሙበት መወሰናቸው የተሰማው።
በተለያዩ አውዶች ይፋ የሆነው ይህ መረጃ ምንጩ ስብሰባውን በቅርብ ሲከታተሉ ከነበሩና የትግራይ ህዝብና ንብረት ላይ ሊረሳ የማይችል ወንጀል ከፈጸመው ሻዕቢያ ጋር የሚደረገውንና የተደረገውን አዲስ ጥምረት ከሚቃወሙ አካላት ነው። መንግስትም ዝርዝር መረጃ እንዳለው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ እየገለጹ ነው።
እነ ምግበና ፍሰሃ ከሰሞኑ ምክክር አካሂደውታል በተባለ ግምገማ የትግራይ ህዝብ ጀርባውን እየሰጣቸው በመሆኑ ኡየተነሳ ዳግም የህዝብ ስሜት ለማነሳሳት ይበጃል ያሉትን ስልት ነድፈዋል።
ፋኖ መፈረካከሱን፣ የተረፈውም ከመንግስት ጋር ውይይት መጀመሩን፣ ሸኔም እያበቃለት እንደሆነ፣ ተበታትኖ እጅ እየሰጠ መሆኑን፣ በደቡብ ከኬኒያ መንግስት ከባድ ድብደባ ደርሶበት እንደተበተነና እንደተማረከ፣ የተማረከውም ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ እየተሰጠ መሆኑን በመዘርዘር ግምገማ ያካሄዱት የትህነግ አንጃ ወታደራዊ አመራሮች፣ በትግራይ ውስጥም የደረሰባቸውን መገፋት ዳሰዋል።
በትትግራይ ህዝቡ አንጃውን ኃይል እየተፋ መሆኑን፣ ጀርባውን መስጠቱን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ሕዝቡ አንጃውን ቡድን በኃይል አማራጭ ለመገዳደር ከጫፍ መድረሱን እነ ምግበ ገምግመዋል።
ይህ እንዚሁን አፈንጋጮች ከሚቃወሙ ወታደራዊ መኮንኖች የወጣው መረጃ አያይዞም ህዝቡን ወደ ትህነግ ለመለስ ይበጃል ያለውን አማራጭ ዕቅድ አስቀምጧል። በዚሁ መሰረት ህዝቡን በድጋፉ ጎራ ለመመለስ ልክ እንደቀድሞው ሁሉ ለትግራይ ህዝብ “ጠላት መፍጠር” የሚለውን አካሄድ ለመድገም ወስነዋል።
በዚሁ ድምዳሜ መሰረት ይህ አፈንጋጭ ኃይል ከሻዕቢያ ጋር ከመከረ በሁዋላ፣ ፌደራል መንግስት በፋኖና ሸኔ ላይ ድል ስላገኘ ቀሪውን ሰላም የማስከበር ስራ ለክልሎች በመተው ሰራዊቱን ከማንቀሳቀሱ በፊት መቅደም እንደሚገባቸው ወስነዋል።
ላሰቡት ጦርነት ይረዳ ዘንድ በነዳጅ ክምችት ዙሪያ በበቂ ሁኔታ ሲዘጋጁበት እንደነበር አመልክተው ቀሪውና አስፈላጊው የነዳጅ አቅርቦት ከሻዕቢያ በኩል በበቂ ደረጃ አቅርቦት እንደሚኖር ቃል እንደተገባላቸው ገልፀዋል።
በዚና ሌሎች ግልጽ ባላደረጉዋቸው የጦርነት የዝግጅት መሰረት፣ “መንግስት ተፈናቃይ በመመለስ ህዝቡን ሳይነጥቀን ምዕራብ ትግራይን ማስመለስ በሚል ሽፋን ጦርነት ከፍተን እየጠላን ያለውን ህዝብ ከጎናችን ማሰለፍ ካልቻልን የትግራይ ህዝብ ራሱ እየገጠመን ሊበታትነን” ይችላ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።
በትግራይ ምንም ኣይነት ጦረነት ሊቀሰቀስ አይገባም የሚል አቋም ያላቸው የቀድሞ የትህነግ ደጋፊ ሚዲያዎች፣ ባለፈው ጦርነት “ግፋ በለው” በማለት ላስጨረሱት ወጣትና ላደረሱት ጠቅላላ ጥፋት ዕርምት በመውሰድ ይመስላል የነ ደብረጽዮንን ቡድና የሰራዊቱን አመራሮች ” ባህላዊ፣ ማሰብ የማይችሉ፣ ዘመን የማይመረመሩ፣ ቆሞ ቀሮች ” ወዘተ እያሉ እያወገዟቸው ነው። በውስጥም “አንዋጋም፣ ጦርነት ስልችቶናል” በሚል በስፋት ተቃውሞ የሚያሰሙ ሰልፈኞች በተደጋጋሚ አደባባይ በመውጣት ድምጽ ሲያሰሙ እንደነበር የሚታወስ ነው።
በወልቃይት የህብ፣ የአስተዳደሩንና የመከላከያን ዝግጅት የሚያውቁ ” እንኳን አሁን በፊት ትህነግ ሁሉ እያለው አልተሳካም” የሚል ምላሽ አላቸው። እነዚሁ ወገኖች ቁማሩ ሁሉ ቆሞ መጠለያ ጣቢያ ያለው ህዝብ ወደ ቀዬው እንድሰፍር መረባረቡ እንደሚበጅ አመልክልተዋል። ከመንግስት ወገን ምንም የተባለ ነገር የለም።