” በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ሌላ ግጭት እንዳይፈጠር እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አሁን ነው” የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ለአልጀዚራ በላኩትና አልጀዚራ “እርምጃ አሁን” ሲል ባተመው ጹሁፍ ጥቅል አሳቡ ዓለም በሙሉ ኢሳያስን ወደ ቀደመው የቁም እስር ይመልስ ዘንድ ጥያቄ የቀረበበት ነው። “ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ ኃያላን አገራትና ህብረቶቻቸው፣ በተለይም መካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ የበምስራቅ አፍሪካ ኢሳያስ እየያያዙት ያለው እሳት እንደማይምራቸው በማስረጃ አስረድተዋል። “እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አሁን ነው” ሲሉም ጥሪ አስምተዋል።
“የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት እንዲቀሰቀስ ለማድረግ እየሰሩ ነው። መቆም አለበት“ሙላቱ ተሾመ ወርቱ
የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ “በአፍሪካ ቀንድ ሌላ ግጭት እንዳይፈጠር እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አሁን ነው ” ሲሉ በአልጀዚራ ባሰራጩት ጽሁፍ አሳሰቡ፡፡የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት እንዲቀሰቀስ ተግተው እየሰሩ እንደሆነም በግልጽ ዘርዝረው አስረድተዋል፡፡
“ጦርነት የኤርትራ መንግስት ዋና ስራውና ጭንቀቱ እዚህም እዚያም ግጭት መቀስቀስ ነው፡፡ አማፂያንን ማደራጀትና መደገፍ ጦርነትና መከፋፈልን የሚፈልጉ መንግስታትን መደገፍ የኤርትራ መንግስት መለያው ይመስላል” ሲሉ በጹፋቸው ያብራሩት ዶክተር ተሾመ፣ ይህን መንግስት የቀጥናው ትርምስ ዋና አክተር በመሆኑ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ሊደረግበት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡
የአፍሪካ ቀንድ ታሪክና ወቅታዊው እውነታዎቹ ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር የተሳሰረ፣ሁከት የበዛበት ክልል እንደሆነ ሙላቱ ተሾመ አመልክተዋል፡፡ አክለውም ቀጣናው ልክ እንደ መካከለኛው ምስራቅ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ የሚጠቀሙበት፣ የተለያዩ አህጉራትን የሚያገናኝ ስትራቴጂያዊና ጠንካራ ጂኦፖለቲካዊ ፉክክር የሚታይበት መድረክ መሆኑን አስምረውበታል፡፡
ኤርትራ በዚህ ግጭት መለያው በሆነው የአፍሪቃ ቀንድ ውስጥ ተሳታፊና ተዋናይ ሆና ኖራለች። ግማሽ ምዕተ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ፣ ኤርትራ በቀጠናው በተለያዩ አካባቢዎች በሚፈጠሩ ግጭቶች ውስጥ በተለያየ ደረጃ ስትሳተፍ መኖሯን ዶክተር ሙላቱ ገልጸዋል፡፡
ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ በኤርትራ ሴራ መታመሳቸውን ያወሱት ሙላቱ ተሾመ፣ ኤርትራ ትርምስ የምትፈጥረው በብዙ ኪሎሜትር ርቀት ተጉዛ እንደሆነ በማሳየት ኢሳያስ አፉወርቂ ጸብ ጠማቂ መሆናቸውን አሳይተዋል።
በነጮቹ አቆጣጠር ከ1993 ወዲህ የመጀመሪያውና ብቸኛው የኤርትራ ፕሬዝዳንት የሆኑት ኢሳያስ አፈወርቂ አገራቸው ከድንበሯ በብዙ ኪሎ ሜትሮች ርቀው በሚገኙ በታላላቅ ሀይቅ አገሮች ውስጥ በመግባት ግጭቶች ውስጥ መነከሯን አብራርተዋል።
የኢሳያስ ለ32 ዓመት በኤርትራ ላይ የነገሱ አራጊና ፈጣሪ መሆናቸውን ያወሱት የወድሞ ፐሬዚዳንቱ፤ ኢሳያስ ዘመኑን የሚመጥን የአስተዳደር ተቋማት እንደሌላቸው ሲያሳዩ፣ በኤርትራ ሕገ መንግሥት የለም። ፓርላማ የለም። ሲቪል ሰርቪስ የለም ብለዋል። ኤርትራ ውስጥ አግባብ ያለው በተዋረድ የሚሰራ ህግ አስፈፃሚ፣ ህግ አውጪ እንደሌለ ገልጸው፣ ያለው አንድ ነገር ነው።ባለስልጣኑ አንድ ብቻ ነው እሱም ፕሬዝዳንት ኢሳያ ነው ብለዋል።
በፕሬዚዳንትነታቸው ዘመን በርካታ ጉዳዮችን በዝርዝር የሚያውቁትና የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መልእክተኛ የሆኑት ዶክተር ሙላቱ በኤርትራ ያለውን የአስገዳጅ ውትድርና ጣጣውን በጽሁፋቸው አስፍረዋል። የችግሩን ግዝፈት ሲያሳዩ ኤርትራ ከህገ ወጥ ወርቅ በተጨማሪ ወደ ውጭ ኤክስፖርት የምታደርገው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣት ወንዶች እና ሴቶን እንደሆነ ገልጸዋል።
በአውሮፓና በተለያዩ ዓለማት በስደተኛ ቁጥር ሰፊውን ድርሻ የያዙት የኤርትራ ወጣቶች ውትድርና ፍርሃቻና በስጋት እንደሚሰደዱ፣ በስደትም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህይወታቸው በባህርና በበረሃ እንደሚያልፍ የተለያዩ መገናኛዎች በተለያዩ ጊዜ መዘገባቸው ይታወቃል። ሙላቱ ተXኦመ ይህንኑ በመድገም “በህገ ወጥ መንገድ ወደ ጎረቤት ሀገራትና አውሮፓ የሚሰደዱ ህይወታቸውን የሚያጠፉ” ሲሉ ስለ ኤርትራዊያን ወጣት ሴትና ወንዶች መከራ በስፋት አብራርተዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ፕሬዚዳንቱ ቀውስ ጠማቂ በመሆናቸው እንደሆነም ደጋግመው ለማሳየት ሞክረዋል። ኤርትራዊያን በግዳጅ ውትድርና አገልግሎት ላለመግባትና በአገዛዙ ባህሪ ሳቢያ ለማምለጥ ሲሉ ከሀገራቸው በገፍ እንደሚሰደዱ ጥገኛነት በሚጠይቁባቸው አገራት የመረጃ ቋቶች ውስጥ በስፋት የሚገለጽ ነው።
“ጦርነት የኤርትራ መንግስት ዋና ስራ ጭንቀቱ ነው። እዚህም እዚያም ግጭት መቀስቀስ፣ አማፂያንን መደገፍ፣ አማፂያን ወይም መንግስታት ጦርነትና መከፋፈልን የሚፈልጉ መንግስታትን መደገፍ የኤርትራ መንግስት ዋና ተግባር ይመስላል” ሲሉ ሙላቱ ተሾመ አልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ድምዳሜያቸውን አሳይተዋል፡፡
ሙላቱ ተሾመ በትህነግ ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ሊጠቀሙበት ሙከራ እያደረጉ መሆኑን አመልክተዋል። ይህ በትግራይ የተቃዋሚ ድርጅቶችና በጊዜያዊ አስተዳደሩ በግልሽና በተዘዋዋሪ ሲገለሽ የነበረውን እውነታ፣ በገሃድ ለዓለም ይፋ አድርገዋል። አክለውም ጦርነት እንዳይነሳ እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አሁን እንደሆነም ለዓለም የዲፕሎማሲ አክተሮች እርምጃ ውሰዱ ሲሉ አሳስበዋል።
በሰሜን ከትህነግ ጋር የተካሄደውን ጦርነት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመውበት እንደነበር ያወሱት ሙላቱ ተሾመ፣ ጦርነቱን ታከው የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ ዘልቀው በመግባት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን አመልክተዋል።
ሙላቱ ተሾመ በጹፋቸው ባይገልጹትም ትህነግ በሰሜን ዕዝ ላይ በከፈተውና “ቅጽበታዊ” ሲል በተኩራራበት የክህደት ተግባሩ፣ ሳቢያ ሻዕቢያ ትግራይ ውስጥ ገብቶ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ውድመት፣ ዘፊያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ወዘተ ተግባራትን መፈጸሙ በማስረጃ የተያዘ ሲሆን በደብረ ጽዮን የሚመራው ትህነግ ከሻዕቢያ ጋር ዳግም ተሻርኮ ጦርነት ለመቀስቀስ መስራቱ በድፍን ትግራይ ተቃውሞ አስነስቷል። አፍቃሪ ትህነግ የነበሩና ” ያዘው፣ ግፋ በለው” ሲሉ የነበሩ የማህበራዊ ገጽ ሚዲያዎችና አቀንቃኞች ሳይቀር እንቅስቃሴውን ” ባህላዊ፣ ዘመን ያማያነቡ፣ ፖለቲካ የማይተነትኑ፣ የቀጠናውንና የዓለምን አሁናዊ አካሄድ የማይረዱ ” ወዘተ በማለት ዘልፈዋቸዋል። እየዘለፏቸው ነው።
እንግዲህ ይህ እየሆነ ባለበት ወቅት ነው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት “ተጽዕኗቸውን ለማስፋፋት ላላቸው ፍላጎት” እንቅፋት አድርገው እንደወሰዱት፣ ጦርነቱ እንዲቀጥል ፍላጎት እንደነበራቸው፣ ዶክተር ሙላቱ ይፋ ያደረጉት።
ይህን ከጠቀሱ በሁዋላ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አማራ ክልል ውስጥ በተቀሰቀሰው ጦርነት ውስጥ መነከራቸውን በይፋ ገልጸው ክስ ያሰሙት።ይህ ብቻ ሳይሆን ከላይ እንደተጠቆመው ኢሳያስ አድርገዋል የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት የሚቃወሙ የትህነግ ቡድኖችን መለያቸው የሆነውን ግጭት ለመጠቀም እየሞከሩ እንደሚገኙ አመልክተው ተቃውሞ ያቀረቡት።
ገና ከጅምሩ የፕሪቶሪያው ስምምነት ያስኮረፋቸው ኢሳያስ መቆሙ አፉወርቂ፣ ካገገመ በሁዋላ ቀድሞውኑ የስምምነቱ ተቃዋሚነታቸውን አንግበው ከተነሱት አንድ ክፋይ የትህነግ አመራሮችና የታጣቂዎቹ መሪዎች ጋር በመሆን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ዶክተር ሙላቱ ግልጽ አድርገዋል።
ዶ/ር ሙላቱ በእነ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራውን ቡድን ከኢሳያስ ጋር እያሴሩ እንደሆነ ጠቅሰው ክስ አሰምተዋል። አክለውም የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት እንዲፈርስ የሚፈልጉ እንደ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረግ እንደሚያስፈልግም አመልክተዋል።
ጦርነት የኤርትራ መንግስት ዋና የገቢ ምንጩ መሆኑን፣ እዚህም እዚያም የሚቀሰቅስ ግጭት፣ አማፂያንን፣ወይም መንግስታትን በመደገፍ ጦርነትን ማባባስ፣ ዘወትር አጥፊ በሆኑ እንቅስቃሴዎች መጠመድ ልዩ ባህሪ መሆኑን በስፋት በዘረዘሩበት ጹፋቸው ዶክተር ሙላቱ ኢሳያስ በኢትዮጵያ ሰሜን ክፍል ድጋሚ ግጭት እንዲቀሰቀስ እየሰሩ ነው፣ከአሁኑ እርምጃ መውሰድ ይገባል ብለዋል።
የሻዕቢያን ታሪካዊ የጦርነት ዳራ የዳሰሱት ዶክተር ሙላቱ፣ ከረጅም ጊዜ መለያየት በሁዋላ ከኤርትራ ጋር የተደረገው እርቅ የረጅም ጊዜ የሰላም ልዩነት አለማምጣቱን አሳዛኝ ብለውታል “… ምክንያቱም ለአቶ ኢሳያስ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የንግድና የመሰረተ ልማት ትስስር መፍጠር ምንም ፋይዳ አልነበረውም። ለሁለቱም ሀገራት ጠቃሚ ቢሆንም ለኢኮኖሚ ትብብር ምንም ፍላጎት አልነበራቸውም” ሲል አስረድተዋል። እሳቸው ባይገልጹትም ኢሳያስ መርህ ላይ የተመሰረተና በህግ የታሰረ ኝኙነት ሳይሆን ፍላጎታቸው ዘወትር “ኢትዮጵያ የጋራ ኤርትራ የግል” የሚል ዝርፊያ ላይ የተመሰረተ ኝኙነት ስለመሆኑ በተለያዩ ጊዜያት ለጉዳዩ አግባብ የሆኑ ወገኖች በተደጋጋሚ መግለጻቸው የሚዘነጋ አይደለም።
ኢሳያስ የሰሜኑን ጦርነት ተክትሎ እንዴት ጦራቸውን በትግራይ እንዳዘለቁ፣ ያስደረሱትን ጉዳት ከዘረዘሩ በሁውላ “ኢሳያስ በትግራይ ክልል ያለው ግጭት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቀጥል እና ኢትዮጵያ እንድትደማ ፍላጎት እንዳላቸው ግልጽ ሆነ” ሲሉ ለምን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ለማፍረስ መንቀሳቀስ እነደጀመሩ አብራተዋል።
ኢሳያስ በኢትዮጵያ አማራ ክልል ውስጥ ሚሊሻዎችን ማደራጀታቸውን፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሰላም ስምምነቱ ያልተደሰቱ ትህነግ ውስጥ ካሉ አካላት ጋር በትብብር እየሰሩ መሆናቸውን አትተዋል።የኢሳያስን አካሄድም ተንኮለኛና አደገኛ ሲሉንገልሸውታል። በዚሁ ሴራቸው የፕሪቶሪያን የሰላም ስምምነት ለመቀልበስ እየተጉ መሆናቸውንም ዓለም እንዲሰማ አድርገዋል።
የሱዳን በእርስ በርስ ጦርነት፣በምስራቅ ሶማሊያ ከአስርተ ዓመታት በላይ በጦርነት ውስጥ ወድቃ እንደገና ለማገገም ትግል እየተደረገ መሆኑን፣ በሳህል ዙሪያ ጽንፈኛ ቡድኖች እየበዙ እንደሆነ፣ ያነሱት ዶክተር ሙላቱ ዳግም ኢሳያስ እየጠመቁት ያለው ጦርነት ዳግም ትግራይ ክልል ከተከሰተ ሊደርስ የሚችለው አደጋ ከዚህ አንፃር መገምገም እንዳለበት ለሚገባቸው ወገኖች በዝርዝር ገልጸዋል።
ከሳህል እስከ አፍሪካ ቀንድ ድረስ ያለው የጥፋትና የትርምስ ቀለበት፣ እንደ አልሸባብ እና ISIL (ISIS) ያሉ ቡድኖችን በማበረታታት አዳዲስ የሽብር መሸሸጊያ ቦታዎችን በመፍጠር እና በቀይ ባህር በኩል ያለውን ዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ እንደሚያውክ ዶክተር ሙላቱ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ሁሉ አስታውቀዋል። እሳቸው ባይገልሹትም ሻዕቢያ አልሸባብን በማሰልጠን፣ በማደራጀትና በማስታጠቅ በአሸባሪነት መፈረጁ የሚታወስ ነው።
በምስራቅ አፍሪቃ ቀንድ አዲስ ግጭት ቢከሰት የሚያስከትለው መዘዝ በአፍሪካ ድንበሮች ላይ ብቻ የሚያቆም እንዳልሆነ ከላይ በተገለጸው የቀውስ ቀበቶና አክተሮች ዝርዝር ያስረዱት ዶክተር ሙላቱ፣ ብውጤቱም የስደተኞች ማዕበል ወደ አውሮፓና ሌሎች አገራት እንደሚፈስ ገልጸዋል።በሌላም በኩል ትርምሱ ቀድሞውንም ደካማ የሆኑትን አገራት ያናጋቸዋል።ጽንፈኛ አስተሳሰቦች ለም መሬት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። እነዚሁ ጽንፈኛ ኃይሎች መዳረሻቸው መካከለኛው ምስራቅ ድረስ እንደሚዘረጋ አስጠንቀቀዋል። ዋሽንግተን፣ቤጂንግ፣ ብራሰልስ(የአውሮፓ ህብረት)ያሉ ዓለም ዓቀፍ ህብረቶችና አገራት ሁሉም በአፍሪቃ ቀንድ በሚከሰተውና በሚሆነው ነገር ድርሻ ሊኖራቸው እንደሚገባ አመልክተዋል።የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት የጋራ ፍላጎት እንደሆነም አጽንኦት ሰጥተዋል።
“ዓለም መስራት አለባት” ሲሉ ማስጠንቀቂያቸውን ያጎሉት የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ፣ ለሰላም ጽኑ አቋም ያላቸውና ሰላም የሚመኙ ወገኖች ኢሳያስ አፉወርቂ ላይ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ሊያሳድሩ እንደሚገባ አስታውቀዋል። የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት መከላከል እንደሚገባቸው ገልሸዋል። ክልላዊ ትብብር በንግድ፣ በመሰረተ ልማት እና በአስተዳደር ላይ በሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ማበረታታት አለበት። ይህ የአፍሪካ ችግር ብቻ አይደለም። ዓለም አቀፋዊ ፈተና ነው።ሲሉም የኢሳያስን የጦርነት መንገድና መዘዙን አስረድተዋል።
የአፍሪቃ ቀንድ ወደ ትርምስ ከተለወጠ የሚያመጣው ውጤት ሁሉም ቦታ እንደሚደርስ፣ ነገር ግን ሰላም ስር ከሰደደ ቀጣናው ለሁሉም አመቺ ድልድይ ሊሆን እንደሚችል ያስገነዘቡት ዶክተር ሙላቱ፣ ቀጠናው አህጉራትን የሚያስተሳስር፣ ንግድን የሚያበረታታ በመሆኑ ሁሉም አካላት እርምጃ ለመውሰድ ጊዜው አሁን መሆኑን አስታውቀዋል።
አልጀዚራ ያተመውን የእንግሊዝኛውን ጽሁፍ እዚ ላይ ያንብቡ