ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለእንዲደረግ ከግብፅ መንግሥት ጥፍጥፍ ወርቆች፣ ጥሬ ገንዘብ እና መርሴዲስ ቤንዝ መኪና የተቀበሉት ሴናተር 11 ዓመት እስራት ተፈረደባቸው።
በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ ጉቦ የተቀበሉት የቀድሞው የኒው ጀርዚ ሴናተር ቦብ ሜኔንዴዝ የ11 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።
ቦብ ሜንዴዝ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ የተለያዩ ጥሬ ገንዘቦችን እና የዓይነት ጉቦ መቀባላቸው በመረጋገጡ ነው እስራቱ የተፈረደባቸው።
በከፍተኛ ደረጃ የአሜሪካን ሕዝብ ከወከለ እንደሳቸው ዓይነት ካለ ሰው በማይጠበቅ መልኩ ሌላ ሀገርን በመርዳት 16 ክሶች የቀረቡባቸው ሜንዴዝ፤ ይህም ቢያንስ 15 ዓመታት ሊያስፈርድባቸው እንደሚገባ ዐቃቤ ሕግ ክርክር አቅርቦ እንደነበር የቢቢሲ መረጃ ያመላክታል።
በተለይም ከግብፅ መንግሥት የተቀበሏቸው ጥፍጥፍ ወርቆች፣ ጥሬ ገንዘብ እና መርሴዲስ ቤንዝ መኪና ለወንጀላቸው ማረጋገጫ ተደርገው ለፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ሜንዴዝ በጠበቃቸው በኩል ቀለል ያለ የማኅበራዊ አገልግሎት ቅጣት እንዲጣልባቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ግን የ11 ዓመታት ጽኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
በተያያዘም ሜንዴዝን ከግብፅ መንግሥት ጋር በማገናኘት ወንጀል የተሳተፈ ዋኤል ሃና የተባለ ግብጻዊ-አሜሪካዊ ነጋዴም ከስምንት ዓመት በላይ እስራት እና የአንድ ነጥብ 25 ሚሊየን ዶላር ቅጣት ተወስኖባቸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring