ሀገራችን ወደብ አልባ መሆኗ ከከነከናቸው ቀዳሚዎች መካከል አንዱ ናቸው።
ጦር ሰብቀን ወደብ እናግኝ ግን አላሉም። በጊዜው የነበረው መንግሥት አልባሌ ሥም እየለጠፈ ቢያሸማቅቃቸውም ካፓርቲያቸው ጋር ሆነው 150 ሺህ ፊርማ አሰባስበዋል።
እኝህ ሰው ፕሮፌሰር አድማሱ ገበየሁ ይባላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሁንም እያገለገሉ ይገኛሉ።
ሕወሓት ኤርትራ ስትገነጠል በአሰብ ጉዳይ መደራደር ይችል ነበር ይላሉ ፕሮፌሰር አድማሱ በቁጭት።
በጊዜው ኤርትራ አጥብቃ የኔ ነው የምትለው ነገር እንዳልነበራት አንስተው፤ ኢትዮጵያም ወደ ኋላ የምታፈገፍግበት ምክንያት አልነበራትም በማለት ይገልጻሉ።
ጉዳዩን የተለያዩ ኮንፍረንሶችን አዘጋጅቶ ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታውን ሚዛን ውስጥ አስገብቶ መከራከር ይቻል ነበር ሲሉም ነው የሚያስረዱት።
እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ነበርኩ ያሉት ፕሮፌሰር አድማሱ፤ በወቅቱ ፓርቲያቸው ኢዲአፓ መድኅን እንደነበርና አንዱ አጀንዳው የአሰብ ጉዳይ እንደነበር ይገልጻሉ።
የወደብ ጉዳይ ተሸፋፍኖ ኢትዮጵያ ወደብ እንድታጣ የተደረገበትና በታሪኳ በር ተዘግቶባት እንድትቀር ያደረገ ሁኔታ መሆኑን ጠቅሰው፤ የአሰብን ጉዳይ በጉልበት ሳይሆን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት መሞከራቸውን ያነሳሉ።
በመነጋገርና በመወያየት እልባት ሊገኝለት ይችላል የሚል እምነት ስላደረብን ፖለቲካዊ አጀንዳ አድርገን መስቀል አደባባይ ሁለት ጊዜ ሕዝባዊ ሰልፍ አካሂደናል በማለት ይናገራሉ።
ከ150 ሺህ በላይ የተረጋገጠ አድራሻ ያላቸውን ሰዎች ፊርማ ማሰባሰባቸውን እና የሰነዱን ቅጂዎች ለአፍሪካ ኅብረት እና ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማስረከባቸውንም ነው የሚያስረዱት።
አሁን በኤርትራ የሚገኙ ወደቦችን የመጠቀም ዕድልን በተመለከተም ሲገልጹ፤ አሰብንም ሆነ ምፅዋን ወደብን ለመጠቀም የሚፈልግ ሌላ ጎረቤት ሀገር የላቸውም።
ወደቡን በመጠቀም እድገታቸውን ለማፋጠን ባለመምረጥ ምክንያታዊ ያልሆነ አቋም መያዛቸው ይገርመኛል ይላሉ።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ትርፋማ የልማት ድርጅቶቿ ውስጥ ድርሻ እንዲኖራቸው በማድረግ ጭምር በሰጥቶ መቀበል መርሕ በጋራ ተጠቃሚ እንሁን የሚል ጥያቄ እያቀረበች ነው ሲሉም ገልጸዋል።
የኤርትራ መንግሥት ይህን ዕድል ገፍቶ ከግብፅም ሆነ ከሌሎች ወገኖች ጋር ከወገነ በአንደኛ ደረጃ እየበደለ ያለው የራሱን ሕዝብ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ታሪካችንን ከተመለከትን ተለያይተን የኖርነው ትንሽ ጊዜ ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ አንድ ሀገር ሆነን መቀጠል ባንችልም እንኳን እንደ ጎረቤት ሀገር ከየትኛውም ጎረቤት ሀገር በላይ ለእኛ የሚቀርቡ ናቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያን ጥቅም በተመለከተ አብረን መቆም አለብን ሲሉም መክረዋል።
ጋዜጣ_ፕላስ
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring