የኢትዮጵያና ኬንያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ በሚንቀሳቀሰው የሸኔ ታጣቂ ላይ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ማካሄድ መጀመራቸውን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የኬንያ ብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ኑረዲን ሞሐመድ ሐጂ እንዲሁም የሁለቱ ሀገራት የመከላከያ እና የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ምክክር አድርገዋል።
በጋራ ባካሄዱት መድረክ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በቀጣናዊ የጸጥታ እና ደኅንነት ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የተፈራረሟቸውን ስምምነቶች ተግባራዊ ለማድረግ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ማካሄድ ተጀምሯል፡፡
በሁለቱ ሀገራት ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉትን ሽብርተኝነት፣ የኮንትሮባንድ ንግድ፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች እና የመሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል ተግባራዊ መሆን የጀመረው የተቀናጀ ኦፕሬሽን በዋናነት በእነዚህ እንቅስቃሴዎች የሚሳተፈውን የሸኔ ታጣቂ ከሁለቱ ሀገራት ድንበሮች አካባቢ ለማስወገድ የሚረዳ እንደሆነ መረጃው አመልክቷል፡፡
በዚህም መሰረት የሁለቱ ሀገራት የደኅንነትና የጸጥታ አካላት በየድንበራቸው ውስጥ በሚገኙ የቡድኑ ካምፖች ላይ የተቀናጀ ኦፕሬሽኖች እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
ጉዳዩን አስመልክቶ የኬንያ ብሔራዊ የፖሊስ አገልግሎት በበኩሉ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የሸኔ ቡድን በሀገሪቱ የድንበር አካባቢ በመንቀሳቀስ ድንበር ተሻጋሪ በሆኑ ወንጀሎች ላይ ይሳተፋል፡፡
ቡድኑ በሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ፣ የሰዎችና የማዕድን ንግድ እንዲሁም የጎሳ ግጭት በመቀስቀስ በሚያደርገው እንቅስቃሴ የሀገሪቱ የብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ሆኖ ቆይቷል፡፡
በዚህም የተነሳ የኅብረተሰቡን ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ መጠነ ሰፊ ኦፕሬሽን መካሄድ ጀምሯል፡፡ እስካሁን በተከናወኑ ኦፕሬሽኖችም በታጣቂ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት ደርሷል፡፡
የተጀመረው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያረጋገጠው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መረጃ፤ የሸኔ ታጣቂ ቡድን የቀረበለትን የሰላም ጥሪ በመርገጥ በራሱ ላይ ጥፋት ቢያውጅም፤ አሁንም የሰላም መንገዱ ዝግ አለመሆኑን ጠቁሟል፡፡
ቀሪዎቹ የቡድኑ አባላትም የጥፋት መንገዱን በመተው የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ ጥሪ መቅረቡን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን የላከው መረጃ አስታውቋል፡፡
ጥር 27 ቀን 2017 ዓም (ኢ ፕ ድ)
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security