ሳዑዲ አረቢያ የፍልስጤም መንግስት እስካልተፈጠረ ድረስ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት እንደማትፈጥር አቋሟን አረጋግጣለች።
ይህ አቋም “ጽኑ እና የማይናወጥ ነው” ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከትራምፕ እና ከኔታንያሁ ጋዜጣዊ መግለጫ በኋላ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ዩናይትድ ስቴትስ “ጋዛን ጠቅልላ ለመያዝ” እንደምትሻ ትራምፕ አሳውቀው ነበር፡፡
ትራምፕ፤ ጋዛን “ከቦምብ በማፅዳት እና ምጣኔ ሀብቷን በማሳደግ” የፍልስጤም አስተዳደርን በመካከለኛው ምስራቅ ልዩ ሥፍራ እንደሚያደርጓትም ተናግረዋል በመግለጫቸው ።
የሳውዲ አረቢያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አክሎም ይህ “የድርድር ጉዳይ አይደለም” ሲል ለፍልስጤማውያን መንግስት የመሆን “ህጋዊ መብታቸው” ካልተሰጣቸው “ዘላቂ ሰላም” መፍጠር አይቻልም ብሏል።
ቀደም ሲል በዋይት ሀውስ የዩኤስ ፕሬዝዳንት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በትራምፕ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን የተመዘገቡ ስኬቶችን ገልጸው የአብርሃም ስምምነት መፈረምን ጨምሮ በእስራኤል እና በበርካታ የአረብ ሀገራት መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መፈጠሩን አስታውቀዋል።
በእስራኤል እና በሳውዲ አረቢያ መካከል ያለውን ግንኙነት መደበኛ ለማድረግ ይህንን ጥረት ለማደስ ተስፋ እንዳላቸው ትራምፕ ተናግረዋል።
ግብፅ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ ኳታር፣ የፍልስጤም አስተዳደር እና የአረብ ሊግ ቅዳሜ ዕለት በሰጡት መግለጫ እንዲህ ያለው እርምጃ “የአካባቢውን መረጋጋት አደጋ ላይ ይጥላል” ብለዋል።
ጋዛን እገነባታለሁ ያሉት ትራምፕ ፍልስጤማዊያን እንዲመለሱ ይፈቅድላቸው እንደሆነ ተጠይቀው “የዓለም ሕዝብ” በሙሉ የሚኖርበት ቦታ ይሆናል ብለዋል።
በተጨማሪም ጋዛን ሲቆጣጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ይሳተፋሉ ወይ ተብለው ሲጠየቁ “አስፈላጊውን እናደርጋለን” ብለዋል።
ትራምፕ ያቀረቡት ሐሳብ አሜሪካ በእስራኤል ፍልስጤም ጉዳይ አንፀባርቃው የማታውቀው እና ሥር ነቀል የሆነ ለውጥ ያሳየ ነው ተብሏል።
በአለም አቀፍ ህግ ህዝብን በግዳጅ ለማዘዋወር መሞከር በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ፍልስጤማውያንም ሆኑ የአረብ ሀገራት ይህንን ፍልስጤማውያንን የማባረር እና ከመሬታቸው ለማፅዳት ከቀረበ ግልፅ ሐሳብ በቀር ሌላ ትርጉም አይሰጡትም።
ለዚህም ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ግብፅ እና ዮርዳኖስ ፍልስጤማውያንን ከጋዛ “ሊወስዱ” እንደሚችሉ ሲጠቁሙ የአረብ መሪዎች ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ እየጨመረ የመጣውን ሐሳቡን ውድቅ ያደረጉት ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security