ኢትዮጵያን ጨምሮ ሶስት የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ ጋር በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት መስማማታቸው ተገለጸ። ሀገራቱ በማዕከላዊ ባንኮቻቸው በኩል ገንዘቦችን በመለዋዋጥ በራሳቸው ገንዘብ ለመገበያየት ነው የተስማሙት።
ሞስኮ በብሪክስ በኩል አዲስ የመገበያያ ገንዘብ ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዷን ተከትሎ ዶናልድ ትራምፕ የ100 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ ገቢራዊ እንደሚያደርጉ ዝተዋል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከናይጄሪያ እና ቱኒዝያ ከሩሲያ ጋር በሀገር ውስጥ ገንዘብ ለመገበያየት ስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሏል።
የዩክሬኑን ጦርነትን ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ከዶላር ውጭ የሆነ ግብይት ለመፈጸም ስምምነቶችን እያደረገች የምትገኝው ሞስኮ ተጨማሪ ሶስት የአፍሪካ ሀገራትን አካታለች፡፡
ከክሪምሊን የወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው ይህን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር በሀገር ውስጥ ገንዘብ ለመገበያየት ስምምነት ላይ የደረሱ ሀገራት ቁጥር 40 ደርሷል፡፡
እንደ አልጄሪያ፣ ግብፅ፣ ሞሮኮ እና ደቡብ አፍሪካ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በመስከረም 2023 በሩሲያ መንግስት የጸደቀው የመጀመሪያው ዝርዝር ውስጥ ነበሩ።
የአርጀንቲና፣ የካምቦዲያ፣ የላኦስ፣ የሜክሲኮ፣ የናይጄሪያ፣ የቱኒዚያ እና የኢትዮጵያ የንግድ ተወካዮች በመገበያያ ገንዘብ ንግድ እንዲሰማሩ አዲስ ፈቃድ አግኝተዋል፡፡
የሩሲያ መንግስት መመሪያው የሩስያ ኢኮኖሚን በመገበያያ ገንዘብ የሚከፍለውን ፍላጎት ለማሟላት እና ወዳጃዊ እና ገለልተኛ መንግስታት ብሔራዊ ገንዘቦችን በቀጥታ በመለዋወጥ የስርዓቱን ውጤታማነት እንደሚያሳድግ አስታውቋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ሀገራቱ ከሩሲያ ጋር በሚፈጽሙት ግብይት የሚያጋጥማቸውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለመቅረፍ እና የተሸለ የንግድ ትስስር ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል፡፡
ስፑትኒክ በዘገባው ጦርነቱን ተከትሎ በምዕራባውን ሀገራት እየተጠናከረ የሚገኘውን ማዕቀብ ጫና ለመቋቋም የሩሲያ መንግስት አማራጭ የመገበያያ መንገዶችን በማፈላለግ ላይ ይገኛል፡፡
የሀገሪቱ መንግስት በስዊፍት አለም አቀፍ የገንዘብ ማስተላለፍያ መንገድ ላይ ማዕቀብ ከተጣለበት በኋላ ጠንካራ የኢኮኖሚ እና ዲፕሎማሲያዊ አጋር እንደሆኑ ከሚነገርላቸው ቻይና እና ህንድ ጋር የሚፈጽመውን ግብይት በራሳቸው ገንዘብ ለማድረግ መስማማቱ ይታወሳል፡፡
ከዚህ ባለፈም የብሪክስ አባል ሀገራት ጠንካራ የፋይናንስ ተቋም እና ነጻ የግብይት ሰንሰለት ለመፍጠር ባስቀመጠው ዕቅድ የራሱን የመገበያያ ገንዘብ ማስተዋወቁ ይታወሳል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህን ገንዘብ ተግባራዊ ማድረግ እና ዶላርን ከዋና የመገበያያ ገንዘብነት ለማስወጣት የሚደረግ ጥረት በሀገራት ላይ ማዕቀብ እና የ100 በመቶ ታሪፍ ጭማሪን ተግባራዊ እንደሚያስደርግ ዝተዋል፡፡
ጋዜጣ_ፕላስ
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring