የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ድርጅቶች ያለ መስሪያ ቤቱ “ግልጽ ፍቃድ”፤ ንብረት የማስተላለፍ፣ የማስወገድ እና የመሸጥ ድርጊቶችን እንዳያከናውኑ ከለከለ። መስሪያ ቤቱ የሰጠውን “ጥብቅ ማሳሰቢያ” በመተላለፍ በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ላይ “ተገቢውን እርምጃ” እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) ዋና ቢሮ ሰራተኞች ከዛሬ ጀምሮ በቤታቸው እንዲቆዩ ትእዛዝ መተላለፉን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል የአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት አጀንሲን እየመሩ የሚገኙት “ፅንፈኛ የዘራፊዎች ቡድን ናቸው፤ ለማባረር ውሳኔ እናሳልፋለን” ብለው ከተናገሩ ከሰዓታት በኋላ ነው ሰራተኞቹ ዛሬ ወደ ቢሮ እንዳይመጡ ትዕዛዝ የተሰጣቸው፡፡
አዲሱ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ ኃላፊነትን ደርበው መረከባቸውም ታውቋል፡፡
በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር የመንግስት ተቋማትን ሪፎርም ለማድረግ ስልጣን የተሰጣቸው ቱጃሩ ኤለን መስክ ከውሳኔው በስተጀርባ ቁልፍ ሚና እንዳቸውም እየተገለፀ ይገኛል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ የዩ.ኤስ.ኤይድ ዋና ዓላማ “ለሌሎች ሀገራት እርዳታ መስጠት ሳይሆን የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም ለማሳካት አጋዥ ሚና መጫወት ነው” ብለዋል፡፡
ድርጅቱ ለአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት እና ብሄራዊ ጥቅም መሳካት የሀገሪቱ አንድ በመቶ በጀትን እየተጠቀመ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎች በትራምፕ አስተዳደር ተቀባይነት እንደሌላቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ተናግረዋል፡፡
አሁን ድርጅቱን እየመራ ያለው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዩ.ኤስ.ኤይድን በፌደራል ተቋማትንና በቢሮዎች ላይ ለውጥ ለማድረግ የሚመለከታቸው አካላት ኮንግረስንና ሌሎች ህጋዊ አካላትን በማማከር እንደሚወስን አስታውቋል፡፡
በአውሮፓውያኑ 1961 በፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ የተመሰረተው ዩ.ኤስ.ኤይድ ለሰብዓዊ እርደታ፣ ድህነት ቅነሳ፣ ለበሽታ መከላከል፣ ለተፈጥሮ አደጋ ጊዜ ስራዎች ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ተቋም እንደነበር የሚታወስ መሆኑን ኤፒ ኒውስ እና ሲኤንኤን ዘግበዋል፡፡
ከዩ.ኤስ.ኤይድ ገንዘብ የሚያገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ንብረቶቻቸውን እንዳይሸጡ እና እንዳይስተላልፉ ክልከላ ተጣለባቸው
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ድርጅቶች ያለ መስሪያ ቤቱ “ግልጽ ፍቃድ”፤ ንብረት የማስተላለፍ፣ የማስወገድ እና የመሸጥ ድርጊቶችን እንዳያከናውኑ ከለከለ። መስሪያ ቤቱ የሰጠውን “ጥብቅ ማሳሰቢያ” በመተላለፍ በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ላይ “ተገቢውን እርምጃ” እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማሳሰቢያውን እና ማስጠንቀቂያውን ያስተላለፈው፤ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 27፤ 2017 ባወጣው “አስቸኳይ መግለጫ” ነው። መስሪያ ቤቱ መግለጫውን ያወጣው፤ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ስራቸውን ለሚከታተላቸው እና ለሚቆጣጠራቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሙሉ ነው።
ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቱ በዚሁ መግለጫው፤ ከሰሞኑ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በኩል “የእርዳታ ማቆም ውሳኔ” መተላለፉን መረዳት እንደቻለ ጠቅሷል። “ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ” እንደሚገኝ የገለጸው ባለስልጣኑ፤ “ዝርዝር ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ” በቀጣይ ባሉት ጊዜያት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች “አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል” እንደሚያከናውን አስታውቋል።
እስከዚያው ጊዜ ድረስ ግን ከUSAID የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፤ ያላቸውን ንብረት “ማስተላለፍ”፣ “ማስወገድ” እና “መሸጥ” እንደማይችሉ ባለስልጣኑ ገልጿል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ከመደበኛ ወይም ፕሮጀክት ስራዎቻቸው ጋር ተያያዥ ከሆኑ ጉዳዮች ውጭ፤ ሃብት እና ገንዘባቸውን “በማናቸውም መልኩ” ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑንም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)