– ሪፎርሞች የኢትዮጵያን ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻነት ማሳደጋቸው ተገለጸ
ባለፉት ዓመታት ገቢራዊ የተደረጉ አይነተ ብዙ መንግስታዊ ሪፎርሞች የተንዛዙ አሰራሮችን በማስቀረት ኢትዮጵያ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን ማስቻላቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም አዘጋጅነት በሚቀርበው ”ኢትዮጵያ ኢን ፎከስ” በተሰኘው ፕሮግራም ላይ ቆይታ አድርገዋል።
ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ የንግድ ስራ ምቹነትን ለማሻሻል እና ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለመፍጠር እየተከናወኑ ያሉ የሪፎርም ስራዎች አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በዋናነት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
መንግስት ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የተለያዩ ሪፎርሞችን እየተገበረ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
የውጭ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በአንድ መስኮት አገልግሎት ሁሉንም ጉዳያቸውን እንደሚጨርሱና ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታን መፍጠሩን ተናግረዋል።
ባለሀብቶቹ የባንክ፣ የኢንቨስትመንት ቪዛን፣ ፈቃድ ማግኘት እና የተለያዩ ግልጋሎቶችን አንድ ቦታ ማግኘታቸው ቀልጣፋ መስተንግዶ ለመስጠት ማስቻሉን ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፈረንጆቹ በ2018 የንግድ ስራ ምቹነት ማሻሻያ ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል።
በፕሮጀክቱ ከተቀመጡ 100 የሪፎርም አይነቶች መካከል መንግስት ከ80 በላይ የሚሆኑትን መተግበሩን ጠቁመዋል።
የኢንቨስትመንት ፈቃድ አሰጣጥን ማሻሻያ፣ ዲጂታል አሰራርን ማስፋት፣ የህግ ማዕቀፎችን ማሻሻል እና ለንግድ ስራው ማነቆ የሆኑ የአሰራር መንዛዛቶችን ለማስቀረት በርካታ ሪፎርሞች መደረጋቸውን ገልጸዋል።
ሪፎርሞቹ መንግስት ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለመፍጠር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል ኮሚሽነሩ።
የመሬት እና መሰረተ ልማት አቅርቦትን ጨምሮ ባለሀብቶች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ መስጠት መቻሉን አንስተዋል።
ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ኢነርጂ፣ ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ቱሪዝም ኢንቨስተሮች በስፋት ከተሰማሩባቸው መስኮች መካከል ይጠቀሳሉ ነው ያሉት።
መንግስት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የማጠናከር እና አዳዲስ መደረሻዎችን የመፍጠር እንዲሁም ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በተለያዩ መስኮች እንዲሰማሩ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የንግድ ስራ ምቹነት እና የኢንቨስትመንት ሳቢነትን ለማሻሻል የተከናወኑ ስራዎች ኢትዮጵያ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ አድርጓታል ነው ያሉት።
መንግስት የውጭ ባለሀብቶች የሚያገኙትን አገልግሎት ለማሳለጥ እያደረገ ያለውን ድጋፍና እና የኢንቨስትመንት ምቹነት ለማሳደግ እያከናወነ ያለውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security