በግብፅ እና በእስራኤል መካከል ትልቅ ጦርነት በማንኛውም ሰአት ሊፈነዳ ይችላል ሲሉ የእስራኤል አምባሳደር ተናገሩ
ግብፅ በሲና በረሃ የጦር ሰፈሮች የገነባች ሲሆን፣ እነዚህ ጦር ሰፈሮቿ ለወታደራዊ ማጥቃት ብቻ የሚያገለግሉ እንጂ ለመከላከል አላማ የተገነቡ አይደሉም።
በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ግብፅ የሰላም ስምምነቱን በእጅጉ እየጣሰች ነው ብለዋል። በቅርቡ በግብፅ ላይ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ በዛሬው እለት ዝተዋል።
አክለው የተናገሩት በአሜሪካ የእስራኤል አምባሳደር ዬቺኤል ሊተር ግብፅ ኢንተርኔቱን እና ሶሻል ሚዲያውን በግብፅ ጦር ምስሎች አጥለቅልቃው እየተመለከትን ነው ሲሉ ከሰዋል።
በግብፅ በኩል ያልተለመደ የተባለለት ሰሞንኛ ክስተት የተስተዋለው በተለይም የግብፅ ፓራትሮፐር ብርጌዶች በኦክቶበር 7 ሐማስ ጥቅም ላይ ያዋለውን አይነት የአውሮፕላን ዝላዮች እና ኦፕሬሽኖችን ጨምሮ የተቀናጀ ነው የተባለለትን የወታደራዊ ስልጠና ልምምዶችን የሚያካሂዱበት ተንቀሳቃሽ ምስል በስፋት መዳረሱን ተከትሎ ነው።
ይህ ፍጥጫ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አኳያ የተያያዘ ውጤት የሚከስት ነው የሚሆነው። ግብፅ እና እስራኤል መሰል ፍጥጫዎችን ሲያስተናግዱ የካይሮ የመውጫ በር ከኢትዮጵያ ጉዳይ ጋር የተሰናሰለ ገቢር ተከትሎ ሲፈጠር ከድሮ እስከ ዘንድሮ ድረስ ሳይለወጥ የዘለቀ ሐቅ በመሆኑ። አሁን ላይ ሁኔታዎች ለግብፅ ከተለመደው ይበልጥ በተወሳሰበ ሁኔታ ውስጥ መግባቷ ግልፅ ሆኗል። ይኸውም የጋዛ ካርድ፣ የዓባይ ውሃ ካርድ፣ የአረብ ሀገራት ካርድ፣ የእስራኤልና አጋሮቿ የዲፕሎማሲ ጫና ካርድ፣ እንዲሁም የእርዳታ ካርዶች ከአረብ ሀገራት እና ከአሜሪካ መራሹ የምዕራባዊ ሀገራት በኩል እያካለቧት ነው የምትገኘው።
ይሁንና የፕሬዝደንት ትራምፕን አዝማሚያ ለታዘበው የሰሞኑ የሲናይ በረሃ ወታደራዊ ፍጥጫ በዓባይ ውሃ ዙሪያ ኢትዮጵያ ላይ ለሚደቅነው የጫና ወጥመድ ሀገራዊ ዝግጁነት እንደሚጠይቀን የሚያሳስብ ይሆናል።
Via EslemanAbay