የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ዶክተር አንዷለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሠራት ባለባቸው ተግባራት ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
ዩኒቨርሲቲው የዶክተር አንዷለም ዳኘን ህልፈት ተከትሎ መሠራት ባለባቸው ሥራዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በተለይ ቤተሰቦቹ ሊደገፉ በሚችሉባቸው እና በሕይዎት ዘመናቸው ያከናወኗቸው ልዩ ሙያዊ አስተዋጽኦዎችን መዘከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡
ዶክተር አንዷለም የተሰጣቸውን ጸጋ ሳይሰስቱ በመጠቀም ለበርካቶች የዘርፉ ባለሙያዎች እና በሙያው ላገለገሏቸው በርካታ ህሙማን የቅን አገልጋይነት ተምሳሌት የነበሩ እንቁ ባለሙያ ነበሩ።
ዶክተር አንዷለም ዳኘ ገና በ37 ዓመታቸው ሕይወታቸውን ያጡ ናቸው። ህጻናት ልጆችን ትተው ያለፍ እና ቤትም ሆነ ሌላ ንብረት የሌላቸው ናቸው።
የቀረበላቸውን በርካታ ዓለም አቀፍ የሥራ ቅጥር ግብዣዎች ባለመቀበል ወገናቸውን ለማገልገል የቆረጡ ነበሩ። በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በቀዶ ጥገና ክፍል የነበራቸውን ልዩ አበርክቶ እና የቀዶ ጥገና ክፍሉን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሻሻል እየጣሩ የነበረ እና እውን ለማድረግ ጫፍ ላይ ደርሰው ያለፍ ናቸው።
ከሁሉም በላይ ደግሞ የነበረውን ሙያዊ አቅም ተጠቅመው ራሳቸውን ለተገልጋዮች በቅንነት ሰጥተው ያለፍ ታላቅ ባለሙያ እንደነበሩ የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ተማሪዎቻቸው እና አገልግሎቱን ያገኙ ደምበኞቻቸው የሚመሰክሩላቸው ድንቅ ሐኪም የነበሩ መኾኑን ዩኒቨርሲቲው በጥልቀት አይቷል፡፡
በመኾኑም የዶክተር አንዷለም ልጆች ለከፍተኛ ትምህርት ሲደርሱ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በነጻ እንዲማሩ፤ ባለቤታቸው ከትምህርት ዝግጅት አንጻር በሲቪል ምህንድስና ሁለተኛ ዲግሪ ያላት እና ጥሩ ዓቅም ያላቸው በመኾናቸው በዩኒቨርሲቲው የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሲቪል ምህንድስና ትምህርት ክፍል የሚቀጠሩበት ኹኔታ እንዲመቻች፤ ዶክተር እንዷለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና የሠሩት እርሳቸው ናቸው።
ክፍሉን እስከ ህልፈታቸው ድረስ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ የነበረ በመኾኑ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በስማቸው ዶክተር አንዷለም ዳኘ ቀዶ ጥገና ዋርድ ተብሎ እንዲሰየም ተወስኗል።
የአንዷለምን የአገልጋይነት ጥግ እንዲሁም ለሙያው የተሰጠ ተምሳሌታዊነትን በቋሚነት ለመዘከር እና ማስተማሪያ እንዲሆን በጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ሃውልት እንዲቆምላቸው፤ በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ School of Medicine ውስጥ በስማቸው BDU Talent Scholarship እንዲቋቋም ተወስኗል።
ለ40ኛ ቀናቸው መታሰቢያ የሚደርስ ስለ ዶክተር አንዷለም የሕይወት ታሪክ የሚዳስስ መጣጥፍ እንዲዘጋጅ ተወስኗል።
ይህ ውሳኔም በዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ይሁንታን አግኝቶ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
ተግባሩን ለማሳለጥ በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ በኩል የሚሠሩ ዝርዝር ሥራዎችን የሚከታተል የሥራ ባልደረቦቻቸውን ያቀፈ ኮሚቴም ተቋቁሟል፡፡
በመጨረሻም የአንዷለም ዳኘን(ዶ.ር) የግፍ ግድያ አስመልክቶ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እንደ ተቋም ፍትሕን አጥብቆ የሚሻ ሲሆን ክስተቱ የአንድ ጊዜ አጋጣሚ ብቻም ሳይሆን ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ ያጣውን በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ አገልግሎት ኀላፊ አድነው በለጠን ጨምሮ እየተደጋገመ የመጣ እና ለሕብረተሰቡ አገልጋይ የሆኑ እንቁ ሃኪሞቻችንን ደህንነት እንዲሁም የማሕበረሰቡን የጤና አገልግሎት በእጅጉ እየተፈታተነ ያለ አሳሳቢ ጉዳይ በመሆኑ የሚመለከታቸው አካላት በጉዳዩ ላይ ተገቢውን እና ጥልቅ ምርመራ አድርገው በግድያው ላይ እጃቸው ያለበትን አካላት በአፋጣኝ ለሕግ እንዲቀርቡ ተጠይቋል።
ይህ ጉዳይ በቋሚነት መፍትሔ በሚያገኝበት መንገድ ላይ ዩኒቨርሲቲው በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶች እንደሚደረግም ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
Via አሚኮ
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring