ሰሞኑን በፈንታሌ ተራራ ስለተገኘው ሚቴን ጋዝ ባለሙያ ጠይቆ መረጃ ማድረሱ ይታወሳል።
በጉዳዩ ላይ ሐሳብ የሰጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ተመራማሪው ኤልያስ ሌዊ (ዶ/ር)፥ ከሳተላይት መረጃዎች የተገኘውን የሚቴን ጋዝ ምንነት በተመለከተ መደመደሚያ ላይ ለመድረስ ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያስፈልጉ ጠቅሰዋል።
መረጃውን ተከትሎም “ለምን በቀላሉ ናሙና ወስዶ ማረጋገጥ አልተቻለም?” የሚለው ጉዳይ በማኅበራዊ ሚዲያ ተከታዮቻችንም የተነሣ በመሆኑ፤ በዚሁ መሠረት ይህ ዘገባ የባለሙያን ሐሳብ ግብዓት በማድረግ ተዘጋጅቷል።
በዛሬው መረጃችን ይህን የተከታዮቻችንን ጥያቄ የሚመልሱ ሁለት ባለሙያዎችን ነው ያነጋገርነው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦሎጂ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ገዛኸኝ ይርጉ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት ከሰጡን ባለሙያዎች አንዱ ናቸው።
ፕሮፌሰር ገዛኸኝ ከሳተላይት ምሥሎች በተወሰደው መረጃ መሠረት ከፍተኛ መጠን ያለው ሚቴን ጋዝ መገኘቱን አረጋግጠው፤ ሁኔታው ሊከሰት የሚችልባቸውን ዕድሎች ሲገልጹም ከጥልቅ አለት ውስጥ የነበረ ጋዝ ገፍቶ ወጥቶ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ጋዙ ይገኝበታል ተብሎ ከሚታመነው ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ እና በቅርቡ ምልክት ከታየበት ወሎ አካባቢ ውስጥ ለውስጥ የመጣ ሊሆን እንደሚችል እና የዚህን ሁሉ መላምት መደምደሚያ ለማግኘት ሰፊ ጥናት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የጋዙን ትክክለኛነት እና መጠን ለማወቅ ለምን አልተቻለም ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ፕሮፌሰር ገዛኽኝ፥ የአቅም እና የዝግጅት ችግር፣ አሁን ቦታው ላይ ያለው የርዕደ መሬት ሁኔታ እና የአካባቢው የሰላም ሁኔታ እክል እንደፈጠሩ ነግረውናል።
የአቅም እና የዝግጁነቱን ጉዳይ ከሌሎች አካላት ትብብር በመጠየቅ መፍታት የሚቻል ቢሆንም፤ የርዕደ መሬቱ ክስተት ባልታሰበ ሁኔታ ወደ እሳተ ገሞራ የመቀየር ዕድሉ ሰፊ ሊሆን እንደሚችል ገልጸው፣ ናሙና ወስዶ ለመመርመር አላስቻለም ብለዋል።
በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የጂኦዴሲ እና ጂኦዳይናሚክስ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ናትናኤል አገኘሁስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን አሉ?
በአካባቢው የተገኘው ጋዝ ከፍተኛ ስለመሆኑ የሳተላይት ምሥሎቹ ያሳዩት መረጃ ትክክል ነው ይላሉ አቶ ናትናኤል። ከሳተላይት ከተገኘው መረጃ ባሻገር ናሙና ወስዶ ምንነቱን እና መጠኑን ማሳየት ያልተቻለው ግን ክስተቱ አዲስ በመሆኑ እንዲሁም ቀድሞ የተዋቀረ የባለሙያዎች ቡድን እና የመሣሪያ ዝግጅት ስላልነበረ እንደሆነ ገልጸዋል።
የጋዙ መታየት ከምን የመጣ እንደሆነ ለጠየቅናቸውም፥ ቀድሞ የተጠቀሱት ምክንያቶች እንዳሉ ሆነው፣ ሚቴን ራሱ በአካባቢው ጥልቅ ከርሰ ምድር ውስጥ ኖሮ ለርዕደ መሬቱ እና ለእሳተ ገሞራው መከሰት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተናገረዋል።
ርዕደ መሬቱ መከሰት ከጀመረ የቆየ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ናትናኤል፥ ኢንትሰቲትዩቱ እንደ አደጋ ስጋት አመራር ካሉ ሌሎች የመንግሥት አካላት ጋር በመሆን ሊከሰት ስለሚችለው እሳተ ገሞራ ክትትል እያደረገ እና ተከታታይ መረጃዎችን እያደረጀ እንደሆነ ተናግረዋል።
የሚቴን ጋዙ ክስተት ግን ያልታሰበ እና ድንገተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የባለሙያም ሆነ የተቋም ዝግጁነት ስላልነበረ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያልተቻለበት አንዱ ምክንያት ይህ እንደሆነ አውስተዋል።
በአካባቢው እየተከሰተ ያለው ርዕደ መሬትም ለአደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ በአካባቢው ደርሶ ናሙና ለመውሰድ አዳጋች እንዳረገው የገለጹት ሥራ አስፈፃሚው፤ የድሮን ምሥል ለመውሰድ እንኳን ተሞክሮ ያልተሳካ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የአካባቢው ከርሰ ምድር ላይ ቀድሞ የተቀመረ መረጃ ባለመኖሩ አሁን የታየውን ሚቴን ጋዝ ሁኔታ ቀላል ናሙና ወስዶ ድምዳሜ ላይ ከመድረስ ጥልቅ ጥናት እንደሚያፈልግ እና ለዚህም በዘርፉ ሰፊ ልምድ ካላቸው እንደ የካናዳ ግሪንሃውስ ጋዝ ክትትል ኩባንያ (GHGSat) ጋር እየተናጋገሩ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሺያል ኢንስቲትዩት የጋራ መደምደሚያ ምንድን ነው?
ሁለቱም ባለሙያዎች ከሳተላይት በተገኘው መረጃ መሠረት እየወጣ ያለው ሚቴን ጋዝ ከፍተኛ መጠን ያለው መሆኑን ይስማሙበታል። ነገር ግን የወጣውን ጋዝ አስመልክቶ ለኅብረተሰቡ መረጃ ለመስጠት ጥልቅ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል ይላሉ።
በዚህም መሠረት ሁለቱም አካላት ባለሙያዎችን በማደራጀት ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር እየሠሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በተለይም በቀጣይነት እየተከሰተ ያለው ርዕደ መሬት ከፍተኛ የሆነ እሳተ ገሞራ ሊፈጥር ስለሚችል ጥንቃቄውን ማስቀደም እና በአካባቢው ላይ ሊከሰት የሚችለውን አደጋ መቀነስ ቅድሚያ ትኩረት የተሰጠው እንደሆነ ተናግረዋል።
መንግሥትም ርዕደ መሬቱን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለው እሳተ ገሞራ የሚፈጥረውን አደጋ ለመቀነስ እና ስፋቱንም ለማጥናት እንቅስቃሴ መጀመሩን የሚጠቅሱት ባለሙያዎቹ፣ ለዚህ አዲስ ክስተት ምላሽ ለመስጠትም እንቅስቃሴ የተጀመረው ወዲያው እንደሆነ ገልጸዋል።
በተለይ አቶ ናትናኤል እንዳሉት፣ ከአካባቢው መልክዓ ምድር ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን ሁኔታ በቅርበት ለማጥናት መሣሪያዎችን በአካባቢው የመትከል እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
አካባቢውን ከሰዎች እንቅስቃሴ ነፃ በማድረግ የጥናት አካባቢ ለማድረግም እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል።
“ይህ አጋጣሚ ግን በቀጣይነት ትኩረት አድርገን እንድንሠራ አቅም ይሆነናል” የሚሉት አቶ ናትናኤል፣ መንግሥትም በዘርፉ ላይ ቀጣይነት ያለው ጥናት እንዲደረግ እና ቅድመ ዝግጅቶችን ለማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ እንዲሰጥ እንዲሁም ሚዲያው ተከከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እንዲሠራ ጠይቀዋል።
በለሚ ታደሰ. ኢቢሲ ዶትስሪም
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring