በአዋሽ ፈንታሌ ከጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የወጣው የሚቲን ጋዝ መጠን እየጨመረ መሆኑንና ይህም እሳተ ገሞራ ሊያስከትል እንደሚችል ጤናዓለም አየነው (ፕ/ር) ገለጹ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነምድር መምህር ጤናዓለም አየነው (ፕ/ር) ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ላለፉት ሁለት ወራት በኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ዙሪያ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ የሚታወስ ነው።
የመሬት መንቀጥቀጥ እና የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ የተያያዙ ናቸው ያሉት ፕሮፌሰር ጤናዓለም፤ በኢትዮጵያ አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ እስካሁን ባለው መረጃ መሰረት ፍንዳታ ከመከሰቱ በፊት የሚፈጠሩ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ነው ብለዋል።
በአብዛኛው ሙቅ ውሃ ከመሬት አየገነፈለ የሚወጣ ሲሆን፤ አልፎ አልፎ ደግሞ አሁን በአዋሽ ፈንታሌ እንደተከሰተው የሚተኑ ጋዞች እንደሚወጡ አስታውቀዋል።
በአዋሽ ፈንታሌ ከጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚቲን ጋዝ እየወጣ መሆኑን ገልጸው፤ የሚወጣው የጋዝ መጠን ከጊዜ ወደ ጌዜ እየጨመረ መሆኑን አመላክተዋል።
የሚቲን ጋዝ የሚከሰተው ከመሬት ውስጥ የቀለጠው አለት ከውሃ ጋር ሲገናኝ፣ ጥልቅ ከሆነ ቦታ የኬሚካል እንቅስቃሴ/ሪአክሽን/ ሲኖር እና በሌሎች መንገዶች መሆኑን አስረድተዋል።
የሚቲን ጋዝ ከእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ጋር ተያይዞ ከሚወጡ የጋዝ አይነቶች አንዱ መሆኑን አስታውቀዋል።
የሚቲን ጋዙ እየጨመረ መምጣት የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ሊያስክትል እንደሚችል አመላክተው፤ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በአካባቢው አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ካላት የኢነርጂ ሀብት አንዱ ከመሬት ውስጥ የሚወጣ የሙቀት ሀይል ቢሆንም የሚቲን ጋዝ መውጣት ጥሩ አጋጣሚ አለመሆኑን ተናግረዋል።
ሚቲን ጋዙ የአየርን የሙቀት መጠን የሚጨምር በመሆኑ በኢትዮጵያ የተከሰተው መጠኑ ከፍ እያለ ከሄደ በአካባቢ፣ በእጽዋትና እንስሳት ላይ ጉዳት ያስከትላል ብለዋል።
አካባቢን የሚበክሉ ጋዞች ሲከሰቱ በጥልቀት በመመራመር እና ሂደቱን በመከታተል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ጥንቃቄ መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ሚቲን ጋዙ በሂደት ወደእሳተ ገሞራ የሚቀየር ከሆነ በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎችን ከአካባቢው የማራቅ ስራን መስራት ይገባል ብለዋል።
የሚቲን ጋዙ በወጣበት አካባቢ የምርምር ማዕከል በማቋቋም የዘርፉ ባለሙያዎች ምርምር በማድረግ የሚያገኙትን ውጤት ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሊያሳውቁ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በሄለን ወንድምነው ጋዜጣ_ፕላስ
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring