– ለጅቡቲ፣ ለኬኒያና ለሱዳን ኃይል እየቀረበ ነው፣
– ለጎረቤት ሀገራት እየቀረበ ያለው ኃይል ከሚመነጨው ከ10 በመቶ በታች ድርሻ ያለው ነው፣
– ከ30 በመቶ በላይ ገቢ እየሸፈነና ለቀጠናዊ ትስስር አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው፣
የሀገሪቱን ዕድገት የሚመጥን የኃይል መሰረተ ልማት ግንባታ በመከናወን ላይ መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገቱን የሚመጥን የኃይል መሰረተ ልማቶችን ግንባታ እያካሄደ መሆኑን የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር ገለጹ።
በአሁኑ ወቅት ኤሌክትሪክ ኃይል ኢኮኖሚያዊ እድገትንም ሆነ ማህበራዊ ልማት ፈጽሞ ማሰብ የማይቻልበት ጊዜ ሆኗል።
ተቋሙም ይህን ታሳቢ ያደረጉ የኃይል መሰረተ ልማቶችን ግንባታ በመላ ሀገሪቱ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አሁን ላይ ያለውን ሀገራዊ ኃይል የማመንጨት አቅም ከእጥፍ በላይ ለማሳደግ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ አምስት የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ በመከናወን ላይ ናቸው ብለዋል።
የኃይል ፍላጎት ባለባቸው አካባቢዎች የማከፋፈያ ጣቢያዎች የማስፋፊያና የማዘመን ሥራ ከማከናወን ጎን ለጎን ተደራሽነቱንና ፍትሐዊነቱን የሚያሰፉ አዳዲስ የማከፋፈያ ጣቢያዎችንና ማስተላለፊያ መስመሮችን እየገነባ እንደሆነም ተናግረዋል።
የሚገነቡ የማከፋፈያ ጣቢያዎችና የማስተላለፊያ መስመሮች እስከ አሁን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያልነበሩትን አካባቢዎች ተደራሽ ማድረግን ትኩረት ያደረጉ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የኃይል ተደራሽነት ሽፋኑን አሁን ካለበት 54 በመቶ ወደ 78 በመቶ ለማድረስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አቶ ሞገስ ገልፀዋል።
ከዋናው ግሪድ ኃይል የማያገኙ አካባቢዎችም ኦፍ ግሪድ በሆነ ወይም ከግሪድ ጋር ባልተገናኘ መንገድ ኃይል የሚያገኙበትን መንገድ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።
የሀገር ውስጥ የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገርም በቀጠናው የሚገኙ የጎረቤት ሀገራትን በኃይል ለማስተሳሰር በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
በዚህም ለጅቡቲ፣ ለኬኒያና ለሱዳን ኃይል እየቀረበ መሆኑንና በቅርቡም ለታንዛኒያ ማቅረብ እንደሚጀመር ጠቁመዋል።
እንደ አቶ ሞገስ ገለጻ ለጎረቤት ሀገራት እየቀረበ ያለው ኃይል ከሚመነጨው ከ10 በመቶ በታች ድርሻ ቢኖረውም የተቋሙን ከ30 በመቶ በላይ ገቢ እየሸፈነና ለቀጠናዊ ትስስር አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል።
እየተገነቡ ያሉ የኃይል መሰረተ ልማቶች የአፍሪካ ህብረት በአጀንዳ 2063 የቀረፀውን አህጉሩን በመሰረተ ልማት የማስተሳሰር ዕቅድ ለማሳካት ጉልህ ድርሻ እንደሚያበረክቱ ማብራራታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ተቋሙ በአሁኑ ወቅት በኦፕሬሽን ላይ ብቻ የሚገኙ 194 የማከፋፈያ ጣቢያዎች፣ 20 ሺ 673 ኪሎ ሜትር የማስተላለፊያ መስመሮች እና 17 የማመንጫ ጣቢያዎችን ያስተዳድራል ብለዋል።
መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓም (ኢ ፕ ድ)
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring