ብርቱካን:- ለትወና ተመርጨ እንጂ እኔ የተከበረ ትዳር ያለኝ ሴት ነኝ አግብቼ ከባለቤተ የወለድኩት ልጅ ነዉ ጫካ ዉስጥ ተድፈሬ የወለድኩት ነዉ ያልኩት በሙሉ ዉሼት ነዉ። ከፋና ዶክመንተሪ የተወሰደ
ሰሞኑን መነጋገሪ የሆነ ቃለ ምልልስ ከኤቢኤስ ጋር አድርጋ የነበርችው ብርቱካን፣ በራሷ፣ በቤተሰቦቿ፣ በባለቤቷ ወዘተ አንደበት እውነቱን ለህዝብ “ይቅርታ” ሲሉ አስታወቁ።
በኢቢኤስ የተሰራው ሁሉ “ድራማ ነው” ያለችው ብርቱካን “እናቴ አልሞተችም፣ ባለትዳር ነኝ፣ ልጄን የወለድኩት ከባለቤቴ ነው። አልተደፈርኩም። ከባለቤቴ ሌላ አላውቅም … ” ስትል ዕውነቱን አስታውቃለች።
“በግልጽ ነው የምነግርሽ መንግስት ቢለቅሽ አማራ አይለቁሽም፣ ስልክሽን ዝጊ፣ አስበሽ ወስኒ። የምትደበቂ ከሆነ እረዳሻለሁ። ፋኖዎች ወደ ሚቆጣጠሩት ቦታ ሂጂ” ስትል መዓዛ መኮንን ለእህቷ ስትነግራ ኢቲቪ ባዘጋጀው ዶክመንታሪ ላይ በስልክ ሲወያዩ ይደመጣል። ልጅን ይዘሽ መደበቅ ነው የሚያዋጥሽ፣ ገበናችን የእኛ ነው ወዘተ በማለት መዓዛ አጠንክራ ስታወራ ይሰማል።
ድርሰቱ ተዘጋጅቶ፣ ልምምድ ተደርጎ የተሰራው ድራማ የሚያስቀው ብርቱካን ስትተውን የኢቢኤስ ሰዎች ተነስተው አቅፈዋት ሲያለቅሱ መታየቱ ነው። በሶስት ወራት ዝግጅትና ጥናት የተሰራው በራሳቸው በጋዜጠኞቹ አስተማሪነት ልምምድ እየተሰጠ መሆኑን ፊልሙ አጋልጧል።
እባክዎ የዩቲዩብ ገጻችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ። በቅርቡ ቋሚ ፕሮግራም ስለምንጀመር ለመከታተል እንዲመችዎ!!