” ኢትዮጵያ የባህር በር አያስፈልጋትም” በሚል አገራቸው ላይ ፈርደው የሚጮሁ “ኢትዮጵያዊ” ነን የሚሉና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ከሻዕቢያ ጋር ያኮረፉ አክቲቪስቶች ዜናው አስደንግጧቸዋል። የሻዕቢያ ቁማር አስቀድሞ የታወቀ በመሆኑ መንግስት ውጥረቱን እንዳስተነፈሰው ተሰምቷል።
በርክታ የኤርትራ አክቲቪስቶችና ተከፋዮች ከተኙበት ተነስተው ሲያቀጣጥሉት የከረሙት ሁከት መክሸፉ ተመልክቷል። ዓላማው ትህነግ ታጣቂዎቹን በወልቃይት በኩል ሲያዘምት የጎጃም ፋኖ በያለበት እንዲተኩስ በማድረግ መከላከያ ትግራይ ገብቶ አገር እንዲተራመስ ነበር።
የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ የተወጠነውና ” ቁማር” የተባለው የጥፋት ወጥመድ መከላከያ በህግ ማስከበር ስም እየተንደረደርን ወደ ትግራይ እንዲገባ በማስቻል፣ ካፈነገጠው ኃይል ጋር ጦርነት ሲጀመር ከትህነግ ታጣቂዎች ጋር እንዲመሳሰሉ አስቀድሞ መለያ ያለበሳቸውን ታጣቂዎቹን በማሰማራት ማተራመስ ነበር።
ዛሬ የትግራይ ፕሬዚዳንት እንደሆኑ የተሰማው ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ” መከላከያ ወደ ትግራይ እንደማይገባ ተነገሮኛል። የተፈጠረውን ችግር እንፈታዋለን” ሲሉ ቀደም ሲል ጀመሮ ከመንግስት ወገን የነበረውን አቋም በይፋ ማስታወቃቸውን ተከትሎ “የሻዕቢያ ቁማር ከሸፈ” የሚል ዜና ተሰምቷል።
በዚሁ ስሌት የትግራይ ክልል በአጅ አዙር ጦርነት የዕልቂት ሜዳ እንዲሆን በማድረግ ኢትዮጵያን ሰላም ለማንሳት የተወጠነው ሴራ ሲከሽፍ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ኢትዮጵያ አሁንም ዓይኗ ቀይ ባህር ላይ የመሆኑ ጉዳይ ነው።
በሌላ ዜና ከትግራይ በኩል የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ነው። ጦርነት ያሰጋቸው የትግራይ ነዋሪዎችን ስጋት ብተከትሎ በርካታ ቁጥት ያላቸው ታጣቂዎች እና አመራሮች ከቡድኑ እየወጡ መሆኑን የሚገልጹ ዜናዎች እየተሰሙ ነው።
በተለይም በደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ሰሜን ምስራቅ ትግራይ አካባቢ ከተሰማራው የታጣቂው አሃድ በርካታ ቁጥር ተቃውሞ በማሰማት ታጣቂውን ትተው እየወጡ እንደሆነ ስፍርና አቅጣጫ እየገለጹ፣ ወታደሮቹ ያሉበትን ክፍል ስም እየጠቀሱ ነው ዜናውን እያሰራጩ ያሉት። ይህ ውሳኔ በአመራሮች ዘንዳ ስጋት መፍጠሩም ታውቋል።
አርሚ 44 ኮር አንድ የሚሰኘው ማንጁር ክፍለ ጦር በአዲ ጉደም ከተማ በሲቪሎች ላይ ተኩሶ ሰው በመግደሉ እና በርካቶችን በማቁሰሉ በርካታ ታጣቂዎች ወደ “ህዝባችን አንተኩስም” በማለት በተደራጀ መልኩ ከአርሚው እንደወጡ እነዚሁ የክልሉ ምስክሮች አስታውቀዋል።
እንደ ምስክሮቹና ምስክሮቹን ጠቅሰው መረጃውን እንዳሰራጩት ከሆነ፣ “ህዝባችን ላይ አንተኩስም” በሚል በአንድ ቀን ብቻ ከአርሚ 44 ኮር 1 ማእበል ክፍለጦር (የክፍለ ጦሩን መሪ ጨምሮ)፤ ኮር 1 ማንጁር ክፍለ ጦር፣ ኮር 3 ሃኽፈን ክ/ር (የክፍለ ጦሩን መሪ ጨምሮ) ከ 500 በላይ ታጣቂዎች ታጣቂ ቡድኑን ጥለው እንደወጡ ዘገባዎች ያስረድሉ። ይሁን እንጂ ዜናው በክፍለ ጦሩ አልተረጋገጠም።
“አፈንጋጭ” የተባለው የትህነግ ቡድን ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ መግባቱም ተመልክቷል። እርስ በርስ መካሰስ መጀመሩም ተሰምቷል። ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ ህዝቡን ሰብስቦ ለማወያየት እና ለማለሳለስ ሙከራ እየተደረገ ነው። አንዳንድ የበታች አመራሮች ሰራዊቱ ወደ ዚህ ውሳኔ የገባው በአምራሩ ጥፋት በመሆኑ ማስተካከል እንደሚከብዳቸው ለአለቆች መናግራቸውን ተሰምቷል።
መንግስት አሁን ላስይ ጣልቃ የሚገባበት አስፈላጊ ጉዳይ ባለመኖሩ በርቀት ክትትልና ድጋፍ እያደረገ ዋና ዓላማው የባህር በርና የቀይ ባህር ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተሰምቷል።