የኤርትራ መንግስት “አፈንጋጭ” ከተባሉት የትህነግ ኃይሎች ጋር በማበር መንቀሳቀሱና በመላው ኤርትራ ክተት ማወጁን ተከትሎ በሁለቱ አጋራት መካከል ጦርነት እንደሚቀሰቀስ በስፋት እየተዘገበ ነው። ሮይተርስ ስማቸውን ያልጠቀሳቸውን ሁለት የትግራይ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ወደ ኤርትራ ማስጠጋቷንም ሪፖርት አድርጓል።
ይህንኑ አስመልክቶ ኢትዮሪቪው ያነጋገራቸው የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ” አንድ ነገር ላረጋግጥ እወዳለሁ። ኢርትዮጵያ ኤርትራ ላይ አንድም ጥይት አትተኩስም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“እንደውም አሉ” ባለስልጣኑ “እንደውም ከቀድሞው በበለጠ ከኤርትራ ህዝብ ጋር ቤተሰባዊ ኝኙነትን የማስፋት ዕቅድ ነው ያለን። ይህንኑ ዕቅዳችንን በህግ አስደግፈን አስተማማኝ የማድረግ ፍላጎት ነው ያለን” ብለዋል። አክለውም ማንም በዚህ ጉዳይ ስጋት እሊገባው እንደማይገባ አመልክተዋል።
በኢትዮጵይ በኩል በትጥቅ ራስን የመቻልና ውታደራዊ አቅምን የማዘመን ስራ በስፋት እየተሰራ መሆኑን መንግስት ራሱ ይፋ እያደርገ መሆኑ ከሰጡት ቃል ጋር እንደሚጋጭ ተጠይቀው ” ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ናጥ የሚመጥናት የመከላከያ ኃይል ያስፈልጋታል። አሁን ላይ ያለው ጅማሬ ነው፤ ይህንንም ማረጋገጥ እችላለሁ፤ ኢትዮጵያ አሁን ካላት በላይ ዘመናዊና ሰፊ ኃይል ትገነባለች። ይህን የምናደርገው ለውጊያ ሳይሆን ራሳችንን በብቃት ለመከላከልና ለሚደፍረን አጭርና ፈጣን ምላሽ ለመስጥት ነው” ብለውዋል።
በኤርትራ ክተት መታወጁንና የጦርነት ስጋት እንዳለ እንደማንም ሰው በሚዲያ እንደሰሙ የገለጹት ባለስልጣኑ “ኢትዮጵያ የጦርነት ፍላጎቱ ስለሌላት፣ ከኤርትራም በኩል ጦርነት የከሰታል የሚል ስጋት ስለማይገባት ትኩረቷ ሁሉ ዋና አጀንዳዋ ላይ ነው” ሲሉ ኤርትራን እንደ ስጋት እንደማይመከቷት ጠቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በመጨረሻ የምክር ቤት ንግግራቸው አሁን ላይ ኢትዮጵያን ሊወር የሚችል አንድም አገር እንደሌለ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ስለ ባህር በር ወቅታዊ አስፈላጊነት ሲናገሩ “ጦርነትት አንሻም” በማለት ነበር። ጦርነት ገዳይና አውዳሚ መሆኑን ጠቁመው ከነኩን በአግባቡ ምላሽ መስጠት የሚችል ዝግጅት እንዳለ በገሃድ ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
ለኢትዮሪቪው አስተያይታቸውን የሰጡት ከፍተኛ ባለስልጣን ኢትዮጵያ የባህር በር ይገባኛል ጥያቄ ማንሳቷ ስጋት ሊሆን እንደማይችል አመልክተው፣ ስጋት የሚሆንባቸው አካላት ቢኖሩም ጥያቄው ፍትሃዊና አንገብጋቢ በመሆኑ በዓለም የድርድርና የንግድ ህግ ምላሽ እስኪያገኝ ኢትዮጵያ እንደማትተኛ ማረርጋገጭ ሰጥተዋል።
ልክ ባለስልጣኑ እንዳሉት ሁሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው በትግራይ አንዳንድ ስፍራዎች የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ትግራይን ለቆ መውጣቱን ማስታወቃቸው ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር መዋጋት እንደማትፈልግ ማሳያ ተደርጎ እንደሚወሰድ የገለጹ አሉ።
የፌደራል መንግስት አሁን ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት ብሎ ትግራይ እንደማይገባ ተነግሮኛል” ሲሉ የቀድሞ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ማናገራቸው ከላይ የተባለውን የሚያጸና ሆኗል።
የአገር መከላከያ በትህነግ መካከል በተፈጠረው ልዩነት መካከል ጣልቃ የመግባት ዕቅድም እንደሌለው የሚናገሩ ወገኖች፣ የትግራይ ሕዝብ ጦርነት “በቃኝ” ከማለቱ ጋር ተዳምሮ ፕሬዚዳንት ኢሳያስና አቶ አንዳርጋቸው በውክልና የሚመሩዋቸው ሚዲያዎች ምኞት የሚሳካ እንደማይሆን ከወዲሁ እየተገለጸ ነው።
የጎጃም ፋኖን በውልቃይትና ጠገዴ ጉዳይ ከትህነግ ጋር አብሮ እንዲቆም ተደርጎ በአማራ ክልል ከተለኮሰው ጦርነት ጋር በማቀናጀት የአገር መከላከያን ኃይል ለመለጠጥ የሚደረገው ዝግጅትና፣ ወደ ወልቃይት ጥቃት ለመስንዘር የተያዘው ዕቅድ አስቀድሞ የታወቀ በመሆኑ በቂ ዝግጅት እንደተደረገለት የወልቃይትን ጉዳይ እየተከታተሉ የሚዘገቡ ደጋግመው እየገለጹ ነው።
ይህ በአንዲህ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አቶ ጌታቸው ጊዜያዊ አስተዳደሩ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የተመሰረተ ግልጽ ኃላፊነትና ህጋዊ ቅቡልነት ያለው አስተዳደር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ ህጋዊ ተቀባይነት ያጣ አንድ የህወሃት ቡድን ከተወሰኑ የታጣቂ መሪዎች ጋር በመተባበር በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ስልጣን በኃይል ለመንጠቅ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስን ጨምሮ የታጣቂዎች ትጥቅ የመፍታት ሂደት በአግባቡ ተግባራዊ አለመደረጉንም አንስተዋል፡፡
ለተግባራዊነቱ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የፌደራል መንግስቱን ስንወቅስ ነበር ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፤ ዋነኛው ምክንያት ግን የሕወሓት አመራሮች የሚፈጥሩት ያልተገባ ቀመር ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡
ቡድኑ ለሚያደርገው ያልተገባ እንቅስቅሴ የተወሰኑ ታጣቂዎችን እንደሚጠቀም በመግለጽም ፤ ቡድኑ የመላው ህዝብ ቅቡልነት የሌለው በመሆኑ ዓለም አቀፉ ማህበረሰቡ ጉዳዩን በትኩረት ሊመለከተው እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የፕሪቶርያው ስምምነት በአግባቡ ሊተገበር እንደሚገባ እና ከዚያ ውጪ የሚደረጉ ሕገ ወጥ ተግባራት ክልሉን የሚያተራምሱ መሆናቸውን መረዳት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስና ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም የተጀመረው ጥረት በዚሁ ቡድን መስተጓጎሉን ገልጸዋል።

የፌዴራል መንግስት የተፈጠረውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ ስድስት ነጥቦችን አንስተው አፍንጋጩ ኃይል ከኤርትራ ጋር በመሆን ክልሉን ለማተራመስና ለማሸበር እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ይህን ሴረኛና አተራማሽ ኃይል “ተው፣ በቃህ” ሊባል እንደሚገባ አሳስበዋል። በንግግራቸው ዲፕሎማቶቹ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለማስቀጠል እንቅፋት የሆነውን አፈንጋጭ ኃይል እንዲያወግዙ ጠይቀዋል።
መንግስት በይፋ ለመጀመሪያ ጊዜ አቋሙን በገለጸበት በዚህ መግለጫ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ደጋግመው ያነሱት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን ያልቻለው በዚሁ አፈንጋጭ ኃይል ሳቢያ መሆኑን ዓለም እንዲረዳው ነበር። አቶ ጌታቸው ቀደም ብለው “እንቅፋቶቹ እኛው ነበርን” ሲሉ ምስክርነት ሰጥተዋል።
በተመሳሳይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ኅበረቱ ጉዳዩ እንዳሳሰበውና ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ አክለውም እዛና እዚህ በመመላለስ ጥረታቸውን እንደሚገፉበት ቃል እግብተዋል።
የአሜሪካና የአውሮፓ አገራት የጋራ መግለጫ
የአሜሪካ፣ የዩናይትድ ኪንግደም፣ የኒውዚላንድ፣ የጃፓን፣ የኖርዌይ፣ የቤልጂየም፣ የቡልጋሪያ፣ የቼክ ሪፐብሊክ፣ የዴንማርክ፣ ጀርመን፣ አየርላንድ፣ ግሪክ፣ ስፔን፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ሉክሰምበርግ፣ ሃንጋሪ፣ ኔዘርላንድስ፣ ኦስትሪያ፣ ፖርቱጋል፣ ሮማኒያ፣ ስሎቬንያ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን ኤምባሲዎች እና የአውሮፓ ህብረት ልኡክ በኢትዮጵያ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።
በዚህም መግለጫቸው ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያሉ ለውጦችን / ሁኔታዎችን እና እየተባባሰ ያለውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
” እ.ኤ.አ. ህዳር 2022 ለተፈጸመው የግጭት ማቆም ስምምነት ሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ ደግመን አጽንኦት እንሰጣለን ” ብለዋል። ይህ ስምምነት የመሳሪያ ድምጽ ጸጥ እንዳደረገም አመልክተዋል። በፍጹም ወደ ሁከት ፣ ግጭት ፣ ጦርነት መመለስ እንደማይገባም አስገንዝበዋል።
ሁሉም ወገኖች ተባብሰው አስቸኳይ ውይይት በማድረግ ውጥረቱን በማርገብ ስምምነቱን እንዲጠብቁ አጥብቀው አሳስበዋል። ማንኛውም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸዋል።