የዛሬው ፕሬዚዳንት ታዬ አቅጸስላሴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ዘመን ” ግብጽ ወደ ሶማሊያ የምታስገባው መሳሪያ ጉዳይ ያሳስበናል” በማለት ዞሮ አልሸባብ እጅ እንዳይገባ ስጋታቸውን ገልጸው አስጠንቀቀው ነበር። ሲያስጠነቅቁም ” … ሶማሊያ አካባቢውን ለማተራመስ ከሚጥሩ አካላት ጋር የምታደርገው እንቅስቃሴ በአዘቦት የሚታለፍ ነገር አይደለም፣ ስለሆነም ሶማሊያ ይህንን ልታቆም ይገባል” በሚል ዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ነበር።
አሁን ላይ የሚወጡ መረጃዎች ይህንኑ ስጋትና ማስጠንቀቂያ የሚያጎሉ እየሆኑ ነው። ኢትዮጵያ፣ አሜሪካና እስራኤል በህብረት እርምጃ እየወሰዱበት ያለው “አልሸባብ ከባድ መሳሪያዎችን እንዴት ታጠቀ? ማን አስገባለት? አልሸባብ ሃይሉን አጠናክሮ ግዛቱን ሲያሰፋና ቪላ ፓርክን በቅርብ እቀት ሲከብ ሶማሊያን ከጥቃት ለመታደግ ቀዳሚ ነን ሲሉ የነበሩት ግብጽና ኤርትራ የት ደረሱ?” የሚሉት ጥያቄዎች ከተራ ስጋት ወደ ስትራቴጂካል ውሳኔ እንዲያመራ አስችሏል።
ከላይ የተገለጸው የደህንነት ስጋት እንዳለ ሆኖ በሃማስና እራኤል መካከል የተከሰተውን የከፋ ጦርነት ተከትሎ ከግብጽ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት አጉልተው የሚያዩ፣ ሁሉም ሲደመር ኢትዮጵያን በሚጠቅም መልኩ የዓለም ጫና ፈጣሪ አገራት አቋም መያዛቸውን በማስረጃ እየጠቆሙ ነው። አንዳንድ የአሜሪካ ባለስልጣናትም በግል ገጾቻቸው ምልክት እየሰጡ ነው። በመንግስትም ደረጃ ያልተጠበቀ ውሳኔ እየተወሰነ ነው።
” … እኔ የማንቂያ ደወል ደዋይ ላለመሆን እየሞከርኩ ነው፣ ነገር ግን ባለፉት 16 ወራት ውስጥ ብዙ የተከሰቱ ነገሮች አሉ። ከዚህ ቀደም በጭራሽ አይሆኑም የምላቸው ጉዳዮች እውን ሊሆኑ እንደሚችሉ አምኛለሁ። እናም በካይሮና በኢየሩሳሌም መካከል ያለው ውጥረት በጣም ትክክለኛ ናቸው፡” ሲል የፎሪን ፖሊሲ አምደኛ Steven A. Cook, “ሙጫው ሞሳድ ወይም በሞሳድ ሻርኮች” የአካሄዱን ቅደም ተከተል ስላላቸው እውቅና ጠቀስ አድርጎ ያልፋል።
ፎሪን ፖሊሲ በፈብሩዋሪ 27 ቀን 2025 ልክ የዛሬ ወር “Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack” የእስራኤልና ግብጽ የሰላም አግባብ እየተፈረከሰ መሆኑ አንስቶ ባሰፈረው ትንተና መሰረት ነበር ይህን ርዕስ የሰጠው።
የጋዛውን ጦርነት ተከትሎ እየተገዘገዘ የሄደው የሁለቱ አገራት ወዳጅነት፣ በአሜሪካ ቁልፍ እርምጃዎች እየታጀበ ዛሬ ላይ ደርሷል። ግብጽም የአረቡን ዓለም እንድትደልል ታስቦ ሲሰጣት የነበረ የጦር በጀትና እግዛ እንዲቀንስ ብቻ ሳይሆን ጭራሹኑ እንዲቆም አሜሪካ መወሰኗ የግንኙነቱ መፈርከስ ዋና ማሳያ መሆኑን የተየያዩ ተንታኞች ይገልጻሉ።
ይህን ዜና ከማንም በላይ ቀልቧን ሰብስባ የምትከታተለው ኢትዮጵያና በቤሄራዊ ጥቅማቸው ከቶውንም የማይደራደሩ ዜጎቿ ” ጊዜ ደጉ ብዙ ያሳየናል” በሚል ነጥቦችን እየገጣጠሙ ትልቁን ስዕል እያዩ ነው።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኢትዮጲያ ዲፕሎማት ለኢትዮሪቪው እንዳሉት ከሆነ ኢትዮጵያ በዝምታ አጋጣሚውን ለመጠቀም እየሰራች ነው። ይህንኑ የሚመሰክሩ መረጃዎችም እየታይዩና እየተሰሙ ነው።
ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር መመለስ የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን አስታውቃ በይፋ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ስትጀምር በግብጽ መሪነት ኤርትራና ሶማሊያ ህብረት ፈጥረው የኢትዮጵያን እንቅስቃሴ ለማስቆም አብረው እንደሚሰሩ በግልጽ አውጀው ነበር።
አሰብን በሰጥቶ መቀበል መርህ እንድታጋራ የተጠየቁት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸውም ሳያንስ የኢትዮጵያ ” ለምን ከሶማሊ ላንድ ጋር መግባቢያ ሰነድ ፈረመች” በሚል ለማደናቀፍ የሄዱበት ርቀትና የግብጽን አጀንዳ ተሸክመው የከፈቱት ዘመቻ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስቆጥቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጠው የፕሬዚዳንት ኢሳያስን ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ደግፈው በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያሟሙቁትንም ታዝቧል።
በዚህ መካከል ኢትዮጵያ የሞቃዲሾውን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼኸን ከገቡበት ቅዠት ቀስቀሳ፣ በአንካራ ስምምነት ሸብባ ከግብጽና ኤርትራ መንጋጋ መፈልቀቋ በታላቅ ድልነቱ የተመዘገብ ሲሆን፣ ለጊዜው ብዙ መረጃ ያልወጣበት “ሰበር ዜና ” ኢትዮሪቪው ሰምታለች።
አሁን ላይ የሰላም ስምምነቱ እንዳልተመቸው ገልጾ ዳግም መሳሪያ እንደሚያነሳ እያስፈራራ ያለው የኦብነግ አንድ ክንፍ አመራር ለኢትዮሪቪው ” ዜናው ባይመችም እውነት ነው። ሼኽ ሃሰን ሁለት ጊዜ የካይሮን የስብሰባ ጥሪ ውድቅ አድርገዋል” ሲሉ በቂ መረጃ እንዳላቸው ጠቅሰው ተናግረዋል።
በድርጅታቸው ጉዳይ ለኢትዮሪቪው መረጃ ሲሰጡ እንዳሉት ከሆነ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ ግብጽ ሁለት ጊዜ ጠርታቸው ጥሪውን
ሳይቀበሉት ቀርተዋል። ምክንያቱ ደግሞ ግብጽና ኤርትራን ማመን ባለመቻላቸው ነው።ከአሜሪካና እስራኤል ጋር በመሆን በሶማሌ ነጻ ይዞታውን እያሰፋ ያለውን አልሸባብን ከፉኛ እየደበደበች ያለችው ኢትዮጵያ የፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህን ህልውና መታደጓ፣ በተቃራኒ አልሸባብ በየመን ሃውቲ አማጺያን አማካይነት በርካታ የጦር መሳሪያ ማግኘቱን ተለትሎ አንዳንድ መረጃዎች ከኢሳያስና አልሲሲ ጀርባ መሰማታቸው እንደምክንያት እንደሚቀርብ እኚሁ የኦብነግ አመራር ገልጸዋል።
ከትናት በስቲያ የግብጹ ኢንዲፐንደት ” ኤርትራና ግብጽ የቀይ ባህር ድንበረተኛ ያልሆኑ አገራት (ኢትዮጵያን ማለታቸው ነው) ወደ ቀይ ባህር እንዳይገቡ በጋራ ለመከላከል ተስማሙ” ሲል የሁለቱን አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።
ይህ ሶማሊያ እንድትጮህ ተደርጎ ለግብጽ ሲባል የተፈጠረ ህብረት፣ ሶማሊያን በመነጠል ኢትዮጵያ ዲፖላሲያዊና ፖለቲካዊ ድል ያገኘችበት ሆኖ ተመዝግቧል።
የኢትዮሪቪው ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከሰራችው የዲፕሎማሲ ስራ በተጨማሪ ሶማሊያ ከአሜሪካ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ተቀብላለች። ይህንኑም እየተገበረች ነው።
ይህን መረጃ አስመክክቶ ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ግን ኢትዮጵያ የሚያዋጣትን መንገድ እየተከተለች መሆኑንና ቀይባህር የመመለሷ ጉዳይ ምን አልባትም የወራት ዕድሜ እንደሚሆን አልሸሸጉም።
ዲፕሎማቱ ዝርዝር መረጃ ባይሰጡም አሜሪካ የየመን ሃውቲ አማጺያንን ልክ ለማስገባት ያመቻት ዘንዳ ለሶማሊላንድ ዕውቅና ሰጥታ በምትኩ በርበራ ወደ ጥግ የጦር ቤዝ ለመገንባት መወሰኗን የዜና አውታሮች ስምና ስልጣን ጠቅሰው ይፋ አድርገዋል። ይህ ውሳኔ ለኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ እየተገለጸ፣ በአናቱ እስራኤል በይፋ ኢትዮጵያን እንደምትደግፍ ማስታወቋ የዲፖሎማሲውን ድል አግዝፎታል።
ኤርትራና ግብጽ ካይሮ ላይ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር ድርሽ እንዳትል ለመከልከል መስማማታቸውን ሲያውጁ፣ በተመሳሳይ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከእስራኤል አቻቸው ቢኒያሚን ኔታንያሁ ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ፍሬ ጉዳይ ይፋ ሆኗል።
በስልክ ውይይቱ ወቅት “እስራኤል ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተዋሳኝ ለመሆን ለያዘችው ጥረት ያልተገደበ ድጋፍ ታደርጋለች!” ሲሉ ኔታንያሁ መናገራቸው ለግብጽና ኤርትራ ምህላና ማጣፊያ ሆኖ ተውስዷል። ጉዳዩን በጥንቃቄ የሚከታተሉ ” የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ዝም ብሎ የተንሳ እንዳልሆነ፣ ይልቁኑም አስቀድሞ ብዙ ርቀት የተኬደበት እንደሆነ አመላካች ነው” ሲሉ
አድናቆታቸውን እየሰጡ ነው።ሶማሊያን ከአድማው አስወጥታ በአሜሪካና እስራኤል ተጅባ ወደ ቀይ ባህር እየገሰገሰች ያለችውን ኢትዮጵያ “የባህር በር አያስፈልግሽም” በሚል የሚቃወሟትና ከሻዕቢያ ጎን ቆመው የሚያጠቋት የራሷ ዜጎች መኖራቸው የዚህ ቁልፍ ትግል ታሪካዊ ሳንካ ሆኖ የሚመዘገብ የክህደት ማማ እንደሆነ በርካቶች እየገለጹ ነው።
ኢንጂነር ይልቃል በገሃድ “ከሻዕቢያ ጋር ሆነን የኢትዮጵያን መንግስት ለማፍረስ እንሰራለን” ሲሉ ሻዕቢያ ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ሁሉ የኢትዮጵያን መከላከያ አፍርሶ አገሪቱን ለጎበዝ አለቃ አሳልፎ ለመጠት የጀመረውን የውክልና ጦርነት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።አቶ አንዳርጋቸውና እሳቸው የሚመሯቸው ሚዲያዎችም በተመሳሳይ ሻዕቢያን ደግፈው ኢትዮጵያ ላይ የሳይበር ታቸውን ከሳቡ ቆይቷል።
ሁሉም ሆኖ “እስራኤል ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተዋሳኝ ለመሆን ለያዘችው ጥረት ያልተገደበ ድጋፍ ታደርጋለች!” በሚል የተሰማው ዜና የነገሮች ሁሉ ማሰሪያ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ እየተገለጸ ነው።አሜሪካ፣ እስራኤልና ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ የጋራ ግብረሃይል እያደረጁ ሲሁን ይህም ጉዳይ ከዶናልድ ትራምፕ የሳዑዲ ጉዞ በሁውላ ይፋ ሊሆን እንደሚችል የኢትዮሪቪው የመረጃ ሰዎች ገልጸዋል።
ኤርትራን ወደ ድንጋይ ዘመን የቀየሯትና ሲያሻው ከአልሸባብ፣ ከየመን ሃውቲና ከእስራኤል ተጻራሪዎች ጋር መልካቸውን እየቀያየሩ የሚሰሩት ኢሳያስ አፉወርቂ ለአውሮፓ ህብረትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት “ኢትዮጵያ ልትወረን ነው” በሚል በተደጋጋሚ ድምጻቸውን ቢያሰሙም ህጋዊ ምላሽ ያላገኙት ከዚሁ የሽብር ተግባራቸው አንጻር እንደሆነ ባለፈው ሳምንት መዘገባችን አይዘነጋም።