የፌደራል ፖሊስ “በሽብር ወንጀል ጉዳይ” ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን አምስት የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሰራተኞችን፤ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት አቀረበ። ጉዳዩ የቀረበለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ፖሊስ በጠየቀው የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
የፌደራል ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮውን የጠየቀው፤ በስምንት ተጠርጣሪዎች ላይ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ስራ “በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በስፋት ለማጣራት” በሚል ነው። ከስምንቱ ተጠርጣሪዎች ውስጥ ባለፈው ሳምንት እሁድ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨ ዝግጅት ላይ “የሀሰት ታሪኳ” ቀርቧል የተባለው ብርቱካን ተመስገን ትገኝበታለች።
የኢቢኤስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የፍርድ ሂደቱ ሲጠርናቀቅ ” ተዋርደናል” በማለት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ወደ ጎን በመተው በተጠናና ዝግጅት በተደረገበት በዚህ ተግባር የተሳተፉትን ሰራተኞች እንደሚቀጡ ገልጸዋል። ድርጊቱንም ህዝን ከህዝብ የሚያጋጭ አደገኛና አስፈሪ ሲሉ ገልጸውታል።