የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለተከታታይ ወራት ያሠለጠናቸውን 33ኛ ዙር ምልምል የአድማ መከላከል ሠልጣኞችን በብር ሸለቆ መሠረታዊ የውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ማስመረቁን ተከትሎ ተመጋጋቢ በሆኑት የጸጥታ መዋቅሮቹ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ማደረጉ ተገልጸ።
ሰፊ ቁጥር ያለው የአድማ ብተና ፖሊስ አደረጅቶ በተለያዩ ከተማዎች ያሰማራው ክልሉ አዲስ ሹመት መስጠቱን ይፋ ሲያደርግ እንዳለው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግስቴ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።
የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አረጋ ከበደ ኮሚሽነር ዘላለምን ብቻ ሳይሆን እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) የአማራ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም አቶ አስቻለ አላምሬ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አድርገው ሾመዋል። በይፋ አይገልጽ እንጂ እስከ በታች አመራር ድረስ ማጽዳት መደረጉ ተሰምቷል።
ክልሉን ለፖሊስ ኃይል የማስረከቡ ስራ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ማስታወቃቸው አይዘነጋም። የአገር መከላከያ ሰራዊት በተለያዩ ግንባሮች ተወጥሯል በሚል በቅንጅት ጥቃት ለመሰንዘር ታቅዶ የተጀመረው “ዘመቻ አንድነት” ይፋ በሆነ ማግስት አማራ ክልልን ለፖሊስ ለማስረከብ ስራ መጀመሩ በርካቶችን አስግወርሟል፡፡
በክልሉ የተለያዩ ከተማ አስተዳደር ሲደርሱ ልዩ አቀባበል የተደረገላቸው የአማራ አድማ በታኝ ኃይሎች በየስርቻው ያለውን ታጣቂ የመቃረም ስራ እንደሚሰሩ ተሰምቷል። መከላከያ ከተሞችንና ከታጣቂዎች የጸዱ አካባቢዎችን ለፖሊስ ኃይሉና ለሚሊሻ በማስረከብ የታጣቂው አመራሮችና ዋና ማዘዣ ወዳለበት አካባቢ ሲያጠና በቆየው ዕቅድ መሰረት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማጽዳት እንደሚጀመር ተሰምቷል።
መንግስትም ሆነ ክልሉ በተለያዩ ጊዜያት ለሰላምና ለውይይት ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የተወሰኑ የፋኖ ኃይሎች ፍላጎት ሲያሳዩ አንዳንዶቹ ፍላጎት ያሳዩት ላይ ውጭ አገር በሚገኙ ሚዲያዎች አማካይነት ጫና እያሳደሩ ጅምሩ መጨናገፉ አይዘነጋም።
መንግስት በውጭ አገር እነሱ በመረጡት አደራዳሪ አማካይነት ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑ ሲገለጽ፣ ችግር የሆነው አሁንም የፋኖ አመራሮች እርስ በእርስ አለመተማመንና አንድ አለመሆናቸው በመሆኑ እንደህነ ለሰላም የተሰየመው ኮሚሽን ሰሞኑንን ማስታወቁ አይዘነጋም።
ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ በተሰጠ መግለጫ አማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ሀይሎች በሚፈልጓቸው የአውሮፓ አገሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድሮች እንዲደረጉ መንግሥት ‘ፈቃደኛ’ መሆኑን የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት ይፋ አድርጓል።
የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ያየህይራድ በለጠ፣ ምክር ቤቱ ሁለት ዓመቱን ሊደፍን የተቃረበውን የአማራ ክልል ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁለቱም አካላት ወደ ድርድርና ውይይት እንዲመጡ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን የተናገሩት ለዶቼ ቬለ ነው።
በዚህም በሁለቱም አካላት በኩል ለውይይትና ለድርድር “ፈቃደኛነት መታየቱን” ገልጸው “የፌደራል መንግሥት በየጊዜው ለሠላምና ለድርድር ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ዝግጁነቱን በተደጋጋሚ ገልጧል፤ በፋኖ ወገኖቻችን በኩልም በምናደርገው ግንኙንት ድርድርና ውይይት እንደማይጠሉ ነግረውናል” ብለዋል።
ይሁን እንጂ አንደኛው ሌላኛውን ያለማመን አዝማሚያ ለውይይት የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቅሰው አለመተማመኑን ለማስወገድ የፋኖ ሀይሎች በሚፈልጓቸው የአውሮፓ አገሮችና አደራዳሪዎች አማካይነት ድርድሮች እንዲደረጉ መንግሥት ‘ፈቃደኝነት’ ማሳየቱን ጠቁመዋል።
ይህን አስመልክቶ ከአብዛኛዎቹ የፋኖ ሀይሎች ጋር “ውይይቶችን እንዳደረጉ” የገለፁት አቶ ያየህይራድ፣ ከፋኖ አመራሮች ምላሽ በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል።
የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት በክልሉ በሚንቀሳቀሱት የፋኖ ሀይሎዎች እና በመንግሥት መካከል እየተካሄደ የሚገኘውን ጦርነት በውይይት እና በድርድር ለመቋጨት የአመቻችነት ሚናውን እንዲወጣ ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም መመስረቱ የሚታወስ ነው።
ለሰላም ያለው ዝግጁነት እንዳለ ሆኖ፣ አሁን ሊጀመር የታሰበው ሁለገብ ዘመቻ ለድርድር አስገዳጅ ሁኔታ የሚፈጥር እንደሚሆን ኢትዮሪቬው ሰምታለች። ትህነግ ለሰላም ሲለመን ” ዞር በሉ፣ ከማን ጋር ነው ንግግር የሚደረገው” እያለ የሰላም ጥሪና አሸማጋዮችን ይገፋ እንደነበር በማስታወስ መረጃውን ያካፈሉን እንዳሉት፣ ትህነግ በመልሶ ማጥቃት ክፉኛ ሲመታና ይዞታውን በሙሉ ለቆ መቀለ ዙሪያ ሲከበብ በሰዓታት ውስጥ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ፈርሟል።
አሁን ላይ የተያዘው ዕቅድ ሰፊ ቁጥር ካለው የአድማ ብተና ኃይል፣ ከሚሊሺኢያና ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆኑ በአዲስ ኃይልና መንፈስ ከበባ በማድረግ የማያዳግም ጥቃት በማካሄድ ልክ እንደ ትህነግ ወደ ሰላም እንዲመጡ ማስገደድ፣ ካልሆነም ጦረንቱን በአሸናፊነት ለማጠቃለል ነው። ዕቅዱ ክረምቱ ከመግባቱ በፊት እንዲተገበር ነው የጊዜ ሰሌዳ የተያዘለት።
የኢትዮሪቪው የአሜሪካ ተባባሪያችን የፋኖና የሻዕቢያ ጥምረት ላይ የሚሰሩትንና፣ ኢትዮጵያዊ ሆነው ለሻዕቢያ እየሰሩ ካሉት የተገኘ መረጃ እንደሆነ ጠቅሶ እንዳለው ስለ ኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል ሶስት ግምገማ አላቸው።
በተለያዩ አቅጣጫዎች ስለተወጠር ኃይሉ ተበታትኗል፣ ያለውን መሳሪያና ኃይል አልተጠቀመም፣ ኃይሉ ወደ አሰብና ትግራይ አቅጣጫ በማድረጉ በአማራ ክልል ሙሉ ጥቃት ቢደረገበት መቋቋም አይችልም ሲሉ የራሳቸውን ትንተና ያስቀምጣሉ።በዚሁ ትንተና ነበር መንግስት ምግበ የሚባሉት ኡእትህነግ ጀነራል የመሩትና ” ዝመቻ አንድነት” የተባለው ዘመቻ የተመረጠው።
ዘመቻው በትነተናው እንደተመለከተው በአማራ ክልል በሰባት አቅጣጫ በተመሳሳይ ሰዓት በአገር መከላከያ ኃይል ላይ ተከፍቶ ነበር። ይህ በገኃድ ለደጋፊዎቻቸው ተነግሮና ሰፊ የቅስቀሳ ስራ ተሰርቶለት የተጀመረው ጦርነት በማግስቱ መክሸፉ ሲሰማ፣ ” አገር መከላከያ ኃይሉን ሙሉ በሙሉ እንዳልተጠቀመ ማሳያ ነው” የሚል አቋም መያዙን ተባባሪያችን ሰምቷል።
ጦርነቱን በማሽነፍ ልክ በደርግ ወቅት እንደሆነ ” የአብይ ሰራዊት” የሚል ስም በመስጠት በድጋሚ የኢትዮጵያን መከላከያ መበተን የሻዕቢያን አጀንዳ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት፣ አማራ ክልል ባስመረቀው የአድማ ብተና ኃይል ብዛት መደናገጣቸውን ተባባሪያችን አመልክቷል።
በአዲስ ዘመናዊና ቲከኖሎጂ እንዲጠቀም ተደርጎ እየተደራጀ ያለው የአገር መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ሁለገብ ዘመቻውን የሚጀምረበት ቀን በውል ባይታወቅም ብዙ እንደማይቆይ ለማወቅ ተችሏል። ይህ እየተሰራ ጎን ለጎን ደግሞ ለሰላም የተጀመረውን እንቅስቃሴ በማንኛውም ማገዙ እንደሚቀጥል የአማራ ክልል መሪ በምረቃው ላይ በይፋ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም የመንግስትን የሰላም አቋም በቅርቡ የፓርላማ ውሏቸው ማረጋገጣቸው እያዘነጋም።