የብርቱካን ቃለ ምልልስ ፍጹም ሃሰትና የተደራጁ አካላት ከኢቢኤስ ሰራተኞች ጋር በቅንጅት ያስተላለፉት ትርክት መሆኑን የኢቢኤስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አማን ፍስሐፅዮን አስታወቁ። አቶ ፍጹም የብርቱካን ተመስገን ሀሰተኛ ዶክመንተሪ ፊልምን በተመለከተ የሰጡት መግለጫ በፋናና በተለያዩ የመንግስት ሚዲያዎች ከቀረበው እውነተኛ የተባለ ዶክመንታሪ ጋር ተዳምሮ ዘገባው ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ለመሆኑ ማስረገጫ ሆኗል።
ሕዝብን ያስለቀሰው ቪድዮ ሲጣራና ሲተርተር ሙሉ በሙሉ ሃሰት መሆኑን ኢቢኤስ በይፋ አስታውቆ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቁ በበጎ ጎኑ የሚታይ ቢሆንም ከከሸፈው አደጋ አንጻር መንግስት ከፍተኛና አስተማሪ በገደብ የተደገፈ ቅጣት ሊጥል እንደሚገባ አሁንም እየተገለርሰ ነው።
ብርቱካን ፕሮግራሙ ከተዘጋጀ በሁዋላ “የቤሰብ ውርስ አለኝ፤ ያበላሽብኛል” በማለት የስርጭቱን ጊዜ ማስቀየሯ፣ ከተቀረጸ በሁዋላ “ህይወቴን ያጠፉታ ይውረድልኝ” ማለቷን፣ ጠቅሰው የኢቢኤስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጠቅሰው የዝግጅቱን መልክ አሳይተዋል።
ደጋግመው ይቅርታ የጠየቁት ኃላፊው ማፈራቸውን ሳይሸሽጉ አስታውቀዋል። የቀረበው ዶክመንታሪ ሲተለተል ሙሉ በሙሉ ሃሰትና የተደራጁ ኃይሎች ያዘጋጁት እንደሆነ አምነዋል። ሙያዊ ጉድለትና የቁጥጥር ችግር እንዳለባቸው ተናግረዋል።
እንዲህ ያሉ ዝግጅቶች አገር ሊያጠፉ፣ ህዝብን ከሕዝብ ሊያጋድሉ የሚችሉ በመሆናቸው በሙያው የተሰማሩ ሁሉ ጥንቃቄ እንዲወስዱ ተማጽነው ለተፈጠረው ስህተት ደጋግመው ይቅርታ የጠየቁት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ በድርጅታቸው ሰራተኞች ላይ አግባብና ለሌሎች ትምህርት የሚሆን እርምጃ እንደሚወስዱ አመልክተዋል።
የኢቢኤስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አማን ፍስሐፅዮን የብርቱካን ተመስገን ሀሰተኛ ዶክመንተሪ ፊልምን በተመለከተ የሰጡት መግለጫ እንዳመለከተው እውነቱ ተጣርቶ ሲያልቅ በራሳቸው ሚዲያ ሙሉ በሙሉ እንደሚያወጡት ቃል ገብተዋል። ዝግጅቱ በከፍተኛ ደረጃ የተቀናጀና ጣቢያችንን የጎዳ ነው በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። በቀረበው ዶክመንታሪ ላይ ጋዜጠኞቻችን መሳተፋቸው ሃፍረት መሆኑን አውስተዋል።
የጉዳዩ ባለቤት ሰራተኞቻቸው ሳይቀሩ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ድርጅታቸው ይርሃሰት ትርክት መስራቱን አምነው ይቅርታ ሲጠይቁ፣ “ካፈርኩ አይመልሰኝ” ባዮች አሁንም ሲከራከሩ ይስተዋላል። ራስዋ ባለ ታሪኳ ” የሃሰት ትርክት ነው” ስትል በይፋ የተናገረቸውን፣ ትርክቱን ያሰራጨው ሚዲያ ባለቤት በይፋ ” ሃሰት አሰራጭተናል ይቅርታ” በማለት የመስከሩበትን የብርቱካን የሃሰት ትርክት “እወነት ነው” በሚል የሚሞግቱ የማይረጥቡ አሳዎች ግራሞት እየፈጠሩ ነው።
“በዝግጅት ክፍላችን ላይ እምነት ማጣት ያስከትላል። የቁጥጥር አካሄዳችንን ጎዶሎ ነበር። ስለዚህ ከአሁን በሁዋላ ምንም ዓይነት ስህተት እንዳይፈጠር ዘመቻ ላይ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ ሙሉ ፕሮግራሙ ቅጥፈትና ትረካ ነው፤ ይቅርታ እጥየቃለሁ” ሲሉ የኢቢኤስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አማን ፍስሐፅዮን የብርቱካን ተመስገን ሀሰተኛ ዶክመንተሪ ፊልምን በተመለከተ የሰጡት መግለጫ ያድምጡት፣ ይመልከቱት