“ጭንቀታችን ቴዲ አፍሮ ነው” ሲል “እኛ” ብሎ በኤርትራዊያን ስም ስጋቱን ይገልጻል። አክሎም “ፈጣሪ እሱንና ቤተሰቡን ከዲያብሎስ ይጠብቃችው” ሲል ጸሎት ያደርጋል። ይህን ሁሉ የሚለውና ለቴዲ አፍሮና ቤተሰቦቹ ከኢትዮጵያን በላይ የሚያነባው ኤርትራ ፕሬስ የተሰኘው የሻዕቢያ የፕሮፓጋንዳ አንድ ክንፍ ነው።

ቴድሮስ ካሳሁንም ሆነ ባለቤቱ አምለሰት ሙጬ ምንም ባላሉበት ኤርትራ ፕሬስ በኤርትራዊያን ስም ቴዎድሮስን “ተጨነቅንለት” ማለቱ ከሻዕቢያ የሚታወቁ ባህሪዎች አንጻር ትልቅ ጥያቄ አስነስቷል።
ኤርትራ ፕሬስ በማህበራዊ ገጹ ሃዘኑን፣ ስጋቱንና፣ መላምቱን በማስቀደም ለኢዮጵያዊያን አደገኛ አጀንዳ የቀረጸው በአንድ ፌስ ቡክ ፖስት መነሻ ነው። ይህ ጉማ ሳቃታ በሚል መጠሪያ የተሰየመው የፌስ ቡክ ገጽ የለጠፈው ሰሞኑን መነጋገሪያ የሆነውን ጉዳይ ነው።
ኢቢኤስ የተባለው ቲቪ ያቀረበው በድርሰትና በልምምድ ታጅቦ ኦሮሞና አማራን ለማጫረስ ታቅዶ የቀረበው የብርቱካን ቃለ ምልልስ ስህተት መሆኑን፣ ቢገልጽም ጉዳዩን በሩዋንዳ የዘር ፍጅት አቀጣጣይ ከነበረው RTLM (Radio Télévision Libre des Mille Collines አገናኝተው ጉዳዩ በጥብቅ እንዲመረመር እየጠየቁ ያሉ ያላቸውን መረጃ በማህበራዊ ገጾች በመለጠፍ ላይ ይገኛሉ።
ሁሉም መረጃዎችና ጥቆማዎች ትክክል ናቸው ተብሎ መደምደም ባይቻልም፣ በተለይ መዐዛ መሃመድ በይፋ ” ነገሩ ተበልሽቷል፡፡ አፍረታችንን በውስጣችን ይዘን መቀመጥ ነው፤ አማሮችም መንግስትም ስለሚገድሉሽ ወደ ደብረብርሃን ፋኖዎች ያሉበት አካባቢ እልክሻለሁ እዛ ቀን እስኪያልፍ ልጅXን ይዘሽ ተደበቂ ….። ” ስትል በስልክ የተናገረችው ቅጂ መሰማቱን ተከትሎ ነገሩ በቅንብር የተሰራ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ታምኗል፡፡

ጉዳዮን ሲያቀጣጥል የነበረው መሳይ መኮንን “ዳይ ወደ ስራ” በማለት በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጊዜ መውሰድ እንደማይገባ መግለጹ ዝግጅቱ እጅግ ሰፊና በደንብ የታሰበበት እንደሆነ ስለሚያሳይ ዜጎች መንግስት ይህን ባደረጉ ላይ ጥብቅ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቃቸው ስህተት እንደሌለው በርካቶች ይስማምሉ።
ነገሩ በዚህ ደረጃ ከባድና በመሆኑ፣ ዕቅዱ አብሮ የኖረውንና እየኖረ ያለውን የአማራና ኦሮሞ ህዝብ ለማጫረስ በመሆኑ ኢቢኤስን ሩዋናዳ ውስጥ የተፈጸመውን የዘር ፍጅት ካቀጣጠለው RTLM (Radio Télévision Libre des Mille Collines በማመሳሰል መንግስት እውርምጃ እንዲወስድ ጫና የሚፈጥሩ ወገኖች እየበረከቱ ነው።
እንደ ሚዲያ ዕልቂትን ማውገዝ፣ ሕዝብ እንዲጫረስ አልመው የሚሰሩትን ማጋለጥ ዋና ተግባር መሆን ሆኖ ሳለ፣ ኤርትራ ፕሬስ “ሉዛ ገዙ የኤርትራዊ ዶላር መንዛሪ ድርጅት ባልቤት ልጅ ነች።የኢቢኤስ ባለንብረት አቶ አማን ፍስሃ ጽዮን ሚስት ስትሆን፡፡ የአቶ አማን ፍስሃ ጽዮን ሚስት የቴድሮስ ካሳሁን ሚስት እህት ናት” በመባሉና “መቅደስ ደበሳይን ደግሞ የኤርትራ የደህንነት ሹም የደበሳይ ጸጋይ ልጅ ናት” ተብሎ ፖስት መደረጉን ዋቢ አድርጎ ” እኛ ኤርትራዊያን ለቴዲ አፍሮ ሰጋን” የሚል አዲስ አጀንዳ ይዞ ብቅ ብሏል።
በኤርትራ ዕድሜ ላካቸውን ከመሬት በታች ባለ እስር ቤት የታጎሩ፣ መኖራቸውና መሞታቸው የማይታወቅ፣ በግል እምነታቸው ሳቢያ መከራ የሚያዩ ዜጎቹን ረስቶ፣ በአዲስ አበባ ከበለቤቱና ከቤተሰቦቹ ጋር እንዳሻው የሚምነሸነሸውን አርቲስት በስጋት ቀለበት ውስጥ መክተቱ ለምን አስፈለገ? የሚል ጥያቄ ያላቸው ሃሳቡን በዚህ መልኩ እንድናቀርብ ጥቆማ ሰጥተዋናል። ቢቻል ቴድሮስንም ሆነ ሚስቱን በማነጋገር ሴራው ማክሸፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በሴራ የተካነው ሻዕቢያ ከገባበት ስጋት አንጻር ኢትዮጵያን በማተራመስ ለመበተን ከሚጠቀምባቸው ሚዲያዎች መካከል አንዱ የሆነው ኤርትሪያን ፕሬስ በተደጋጋሚ፣ አማርኛና እንግሊዘኛ በመቀላቀል ዘመቻ ላይ ከተሰለፉ ወራት ተቆጥረዋል።
ከፕሪቶሪያው ስም፣ምነት በሁዋላ እጃቸውን አጣጥፈው የተቀመጡ የሻዕቢያ ፍልፍል ሚዲያዎችና ራሳቸውን የሸጡ “ኢትዮጵያዊ የሚዲያ ባንዳዎች” አዋራቸውን አራግፈው በቅብብል ኢትዮጵያ ላይ መርዝ እየረጩ ስለሆነ አገር ወዳዶች ይህን መመከትና ማጋለጥ ይገባል።
ኤርትሪያን ፕሬስ “ለአሁኑ በኤርትራ ላይ ያለውን ውንጀላ ወደ ጎን እንተወው” ይላል ልክ እንደ ተበዳይ አገር። “ይህ የአሁኑም ሆነ ያለፈው የኢትዮጵያ መንግሥት የነቀፋ አካሄድ ለእኛ አዲስ ነገር አይደለም” በማለት በደፈናው ያለቃቅሳል። “እኛ” ወይም ” እኛ ኤርትራዊያን” እያለ ዝርዝር በሌለው ብሶትና ስጋት ያላዝናል።
“ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልገኛል” ማለቷን ተለትሎ ዕለት ዕለት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ዜጎች በላይ የኢትዮጵያን ጉዳይ እየነቀሰ የሚተቸውና አቅጣጫ በማሳት ለሻዕቢያ ፕሮፓጋንዳ በሚጠቅም መልኩ የሚያቀርበው ኤርትራ ፕሬስ፣ “እኛን የሚያሳስበን በቀጣይ በአንጋፋው ቴዲ አፍሮ ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸው ነው” የሚል አጀንዳ ይተክላል፡፡ ቴድሮስን በማንሳት አድናቂዎቹ እንዲንጫጩ የቁጩ ደረት እየመታ ይጣራል።
ይህ የሻዕቢያ አንደበት የሆነ ሚዲያ ኤርትራዊያን ለቴዲ አፍሮ እንደሚሰጉ ሲገልጽ እንደመነሻ ያሳየው የአንድን ግለሰብ የፌስ ቡክ መረጃ በመንተራስ ጉዳዩ የመንግስት እንደሆነ አድርጎ ይስለዋል።
ቴዲ አፍሮ በተለያዩ ጊዜያት የገጠሙትን ውጣ ውረዶች ያስታውስና ” የፒፒ ካድሬዎች ውንጀላ ከጅልነት ጋር የሚጋጭ ሲሆን የቴዲ አፍሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደጋፊዎቸ የማይናወጥ ጸሎት እና ድጋፍ ከጎኑ እንደሚቆሙ ግልጽ ነው” የለበጣ ምኞቱን በማሳረጊያነት ተጠቅሟል።
ኢቤኤስ የሚባለው ሚዲያ ታቅዶና ታስቦበት ሶስት ወር የፈጀ ዶክመንታሪ በማዘጋጀት ለትርምስ የታሰበው ዕቅድ መፍረሱን ተከትሎ ኢሪትሪያን ፕሬስ ልክ እንደ ሌሎቹ የተበሳጩ ጸረ ኢትዮጵያ ሚዲያዎች ሌላ አጀንዳ መትከሉ የሚጠበቅ ቢሆንም አካሄዱን እየተከታተሉ ማጋለጥ ለአፍታ ቸል የሚባል ጉዳይ አይሆንም። ኢትዮጵያዊነት ማልትም ይህ ነው።
በተመሳሳይ ጉዳይ የብርቱካን ተመስገን ቃለምልልስን ተከትሎ፣ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩ የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ሠራተኞች መካከል ባለቤቶች አማን ፍስሀፅዮንና ባለቤታቸው ወ/ሮ ማክዳ ከእስር መለቀቃቸው ተሰምቷል።
ሶስት ወር ሙሉ ዝግጅት የተደረገበትን ፕሮግራም አለማወቅ ለሰሚው ግራ በመሆኑ በርካቶች “ቢፈቱም ምርመራው ሊቀጥል ይገባል” ባይ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ በብሮድካስት ባለስልጣን “ለሥርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ኘሮግራም ወይም ዜና፤ የማንኛውንም ሰው የግል ሕይወት የመከበር መብት የሚጥስ፤ የሰው ልጆችን ክብር የሚፃረር፤ በቀጥታ ጉዳት የሚያስከትል፤ የጤናና ለደህንነት ጎጂ የሆነ ባህሪን የሚያበረታታ፤ የወንጀል ድርጊት እንዲፈጸም፤ ሠልምና ፀጥታ እንዲደፈርስ የሚቀሰቅስ፤ ማንኛውም ሰው ማንነት መሰረት በማድረግ እንዲጠላ፣ የሚቀሰቅስ፤ መሆን የለበትም!” የሚል አዋጅ ስላለው ይሕንኑ ህግ አንስቶ ኢቢኤስን ሊመረምረው እንደሚገባ በርካቶች “ይህ ሁሉ ሲሆን የት ነህ ” እያሉ እየጠየቁ ነው።
ባለስልጣኑ ” ማንኛውም የውጭ ዜጋ ከባለሥልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ ተራኪ ወይም ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያ ውስጥ መስራት አይችልም፡፡ በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡” ሲል ህግ ጠቅሶ ማስታወቂያ ያስነግራል።
