“በኤርትራ ሰዓት ቆሟል” የሚል ስያሜ ያተረፈውና ከዓለም በጨለማ አገዛዝ ኝባር ቀደም እንደሆነ የሚነገርለት ሻዕቢያ የአውሮፓ ሕብረት ላይ አቤቱታ ለማቅረብ ጊዜ እንዲመቻችለት ያቀረበው ጥያቄ የ”ዝምታ” መልስ እንደተሰጠው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አስታወቁ። አሰብን ሳኡዲ ለትገዛው ነው በሚል የሚሰራጨው ዜና የሻዕቢያ ደጋፊና ራሱ ሻዕቢያ ያፈራቸው ሚዲያዎች የፈጠሩት ነው ተባለ።
መረጃውን ለኢትዮሪቪው ያስታወቁት ወገኖች እንዳሉት፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ “ኢትዮጵያ ልትወረን ነው” በሚል ከህጻን እስከ አዛውንት ክተት ከጠሩ በኋላ ጎን ለጎን የዲፕሎማሲ የበላይነት ለመያዝ ነበር አውሮፓ ህብረት ላይ ጊዜ አስመድበው ማብራሪያ ለመስጠት ጥያቄ ያቀረቡት።
ጥያቄው የቀረበለት የአውሮፓ ማርላማ ምንም ዓይነት ምላሽ ሳይሰጥ ዝምታን መምረጡን ያስታወቁት ወገኖች እንዳሉት እንደምታው “ስራህ ያውጣህ” እንደማለት ነው። አውሮፓ ሕብረትም ሆነ አሜሪካ በፕሬዚዳንት ኢሳያስ የግፍ አገዛዝ ሳቢያ በርካታ ስደተኞችን ለመቀበል የተገደዱ፣ በአደባባይ አገዛዙን የሚቃወሙና መወገድ እንዳለበት ደጋግመው አቋማቸውን የሚያስታውቁ መሆናቸው አይዘነጋም።
ህብረቱ ምላሽ ባለመሰጠቱ የተነሳ የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ተቀማጭነታቸው በአስመራ ለሆነ ውስን ቁጥር ላላቸው ለውጭ ዲፕሎማቶችና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኃላፊዎች ማብራሪያ ለመስጠት ተገደዋል።
የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ፤ አስመራ በህወሓት እና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እየተካሄደ ባለው ግጭት ውስጥ ምንም አይነት ሚና እንደሌላት፣ ኢትዮጵያ “የጎረቤቶቿን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንድታከብር” ግፊት እንዲደረግባት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ጥያቄ አቅርበዋል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ የኤርትራን ግዛት ነካች በማለት የጠቀሱት ቦታ የለም። ይህም ከስጋት የመነጨ የቀረበ ንግግር ተደርጎ ተወስዷል። ጦርነቱን ተከትሎ የኤርትራ ወታደሮች ወረው የያዙት የሚታወቅ አካቢቦዎች “ይዞታችን” ሲሉ አስተባብለዋል።
“የተዛባ እና ጊዜው ያለፈበት የባህር ዳርቻ ፍላጎት አላት” ሲሉ ኢትዮጵያን ኮንነዋል። ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲ ወይም በወታደራዊ ኃይል የባህር ላይ መዳረሻና የባህር ሃይል ሰፈር ለማግኘት ባላት የተሳሳተ እና ጊዜው ያለፈበት ምኞት ኤርትራ ግራ ተጋብታለች ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም “በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በሕወሓት መካከል እየተካሄደ ባለው የውስጥ ግጭት ውስጥ የኤርትራ መንግስት ምንም ዓይነት ሚና የለውም። ከዚህ ውጭ የሆኑ ውንጀላዎችን ወይም ክሶችን ሙሉ በሙሉ አንቀበልም” በማለት ከደሙ ንጹህ መሆናቸውንም አመልክተዋል።
ወይዘሮ ፈትለወርቅ፣ የትህነግ አፈንጋጭ ኃይል ደጋፊዎች ከሻዕቢያ ጋር ኝኙነት መጀመሩን በተደጋጋሚ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። በተለይም በአማራ ክልል ያለው ቀውስና ጦርነት ኤርትራ ስለመጠመቁ በርካታ መረጃ እንዳለ አሁን ዱባይ የ ሚኖር የሻዕቢያ የሰለላ መዋቅር አባል ማሰጃ ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም።
ኢትዮጵያ ከሶማሊ ላንድ ጋር የባህር በር ኪራይ ስምምነት መፈረሟን ተከትሎ በአደባባይ ዘመቻ የጀመረችው ኤርትራ እጃቸውን አጣጥፈው የነበሩትን የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊቶቿን ዳግም ቀስቅሳ ኢትዮጵያ አሰብን እንደምትወር በማስመሰል ዘመቻ መጀመራቸውን ልጥፋቸውን በመሰብሰብ አገራቸውን የሚወዱ እያጋለጡ ነው።
በኤርትራ የግዳጅ ውትድርና፣ ከዓለም መለየትና እጅግ ኃላ ቀር በሚባል ደረጃ መኖር፣ ስደትና ሞት ለታከታቸው ኤርትራዊያን ማነሳሻ የሆነው የአሰብ ጉዳይ አሁን ላይ “ሳኡዲ ገዛቸውና፣ ልትገዛው ነው” በሚል ዜና እንዲታጀብ የተደረገው በእነዚሁ የቅሰቀሳ ማሽን በሆኑ ተከፋይ ሚዲያዎች ፈጠራ እንጂ ከሳውዲ ወገን በገሃድ የተባለ ነገር እንደሌለ ተቀማጭነታቸው በሳኡዲ የሆነ ዜጎች መረጃ አጣቅሰው ገልጸውልናል።
እነዚ ወገኖች እንዳሉት ይህ እስከተጻፈ ድረስ በይፋ አሰብን አስመልክቶ ከሳኡዲ በኩል የተባለ ነገር የለም። አሰብ ከኢትዮጵያ በግፍ የተወሰደ ንብረቷ በመሆኑ በህጋዊ መንገድ መጠየቅ እንደምትችል ኢትዮጵያዊያን ምሁራን ለአቶ መለስ ዜናዊ በጽሁፍና በሰነድ ጥያቄ ማቅረባቸው አይዘነጋም። እነዚሁ ወገኖች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚዲያና በመጽሃፍት ይህንኑ ጉዳይ ለህዝብ ሲያስታውቁ እንደነበር፣ ይህን ሲያደርጉም ትችትና ነቀፌታ ይሰነዘርባቸው እንደነበር አይዘነጋም።
ዛሬ ላይ ቀደም ሲል የተፈጸመውን ደባ ወደጎን በማለት የባህር በር ጥያቄ በገሃድ የሚያነሳ መንግስት መነሳቱ በቁጭት ለኖረው ሕዝብ መነቃቃት መፍጠሩ ከየአቅጣጫው እየተሰማ ነው፤ በሌላ በኩል አቶ አንዳርጋቸውና ጽጌና አቶ ነዓምን በገሃድ ከሚመሯቸው ሚዲያዎች ጋር ሆነው ” አሰብን መተየቅ ወንጀል ነው” በሚል ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ ከፍተዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ኤርትራ ላይ አንድም ጥይት የመተኮስ አሳብ እንደሌላት፣ የባህር በር ጥያቄዋን ግን በአግባቡ እነምትገፋበት፣ ከዚያ ውጭ ግን ትንኮሳ ካለ አጻፋው የከፋ እንደሚሆን በይፋ “ዓለም ይስማ” ሲሉ መናገራቸው ዓይዘነጋም።
በቴሌግራም ያግኙን https://t.me/+f_kxmaPjD-9jYTdk