በኢትዮጵያ የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል ለማቋቋም የሚስችል ውይይት በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን
ከተመራ ልዑክ ጋር ተደረገ። የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለማቋቋም የሚስችል ፕሮጀክት ፕሮፖሳል አቅርቧል፡፡
ፕሮጀክቱ በተርኪሽ ትራንስፕላንት ፋውንዴሽ፣ ተርኪሽ ኮኦፖሬሽን ኤጀንሲና ኢተርናሽናል ትራንስፕላንት ኔትወርክ ድጋፍ ይተገበራል። በኢትዮጵያ የሚሰጠውን የህዋስ፣ ህብረህዋስና የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ አገልግሎትን ለማስፋፋት ይረዳል፡፡
በቅርቡ በተወካዮች ምክርቤት የጸደቀው የጤና አዋጅ የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላን ያካተተ መሆኑን ያስታወሱት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ በሃገራችን የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ አገልግሎት አሁንም ያልተሟላ ፍላጎት መኖሩን ተናግረዋል፡፡ አገልግሎቱን ለማስፋት የህዋስ፣ ህብረ-ህዋስ እና የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ አገልግሎት አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱንም አከለዋል፡፡
የልኡካን ቡድኑ ያቀረበው ፕሮጀክት ዕቅድ በሃገራችን እየተሰጠ የሚገኘውን የህብረ-ህዋስ እና የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ አገልግሎትን እንደሚያሳድግ የተናገሩት ደግሞ የደምና ህብረ-ህዋስ ባንክ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው ሲሆኑ፤ የቀረበው የፕሮጀክት ዕቅድ ከደም እና ህብረ-ህዋስ ባንክ እቅድ ጋር የተጣጣመ መሆን እንዳለበት ተናገረዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ብሄራዊ ሰውነት የአካል ንቅለ-ተከላ ማስተባበሪያ ማእከልን ማቋቋም፣ የአካል ንቅለ-ተከላ ማዕከል በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መመስረት፣ የሰውነት አካል-ንቅለ ተከላ ሲሙሌሽን ማሰልጠኛ ማቋቋምና የባለሙያዎች ስልጠናን ያካተተ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የአካል ክፍሎች ንቅለ ተከላ ማዕከል ለማቋቋም የቀረበው የፕሮጀክት ሀሳብ አስፈላጊነት ጥልቅ ነው፤ ይህም በሀገሪቱ ያለውን ያልተሟላ የሰውነት አካል ንቅለ ተከላ አገልግሎት ፍላጎት ለመፍታት ያለመ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ የሴል፣ የቲሹና የሰውነት አካል ንቅለ-ተከላ ተደራሽነትን በማስፋት ህይወትን የመታደግ፣ የጤና ውጤቶችን የማሻሻል እና ዘላቂ የሰውነት ንቅለ-ተከላ አገልግሎትን በኢትዮጵያ የመገንባት አቅም ይፈጥራል። ለሀገሪቱ አጠቃላይ የጤና አጠባበቅ ስርዓት መሻሻል አስተዋጽኦ ያደርጋል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን ጋር የፕሮጀክቱን ፋይናንስ ምንጭ፤ ሁለቱ ሃገሮች በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ በሚያጠናክሩበት ላይ መወያየታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ጠቅሶ ኢፕድ ዘግቧል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring