“ብረት ያነሱት ኃይሎችን ማሰባሰብ” የሚለው አዲሱ የትግል ስልት ሻዕቢያ ከግብጽ ጋር አብሮ በገሃድ ኢትዮጵያ ላይ ተቃውሞ ማሰማት ከጀመረ በሁዋላ ግልጽ እየሆነ የመጣ ጉዳይ ነው። ጃውርና የቀድሞ የግንቦት ሰባት አመራሮች በዲሲ መምከራቸው የተደመጠው ከዚሁ ዘመቻ አዋጅ ቀደም ሲል መሆኑም ጉዳይን አጠንክሮታል።

በትግራይ የትህነግ አንጃ ከሻዕቢያ ጋር ግንባር ገጥሞ እየሰራ እንደሆነ በስም የሚጠቀሱ አመራሮች፣ አቶ ጌታቸው ረዳና በውጭ ያሉ የሁለቱም ድርጅቶች ደጋፊዎች በተመሳሳይ ቋንቋ ያለ አንዳች መሸማቀቅ ዕለት ዕለት እየተናገሩ ነው። በፊት ጎራ ለይተው ከሻዕቢያ ጋር ሲቧቀሱና በጄኖሳይድ ሲከሱ የነበሩ አንዳንድ የትህነግ ደጋፊ ሚዲያ ባለቤቶች ወደ አስመራ ግብዣ ተደርጎላቸው እሺታቸውን ሲገልጹም እየተሰማ ነው።
ትህነግ የሕዝብ ማዕበል አስነስቶ ወደ ሸዋ ሲቃረብ በይፋ ከኦነግ ሸኔ ወይም ኦላ ጋር ስምምነት ማደረጉን ባስታወቀ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ከሰማይና ከምድር በተከፈተ የመልሶ ማጥቃት ክፉኛ የሰብአዊ ቀውስ አስተናግዶ መቀለ ዙሪያ ከደረሰ በሁዋላ “አሻፈረኝ” ሲል ለነበረው ሰላም እጅ ሰጥቶ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎ ያኮረፈው ሻዕቢያ የዕርም ጎፈሩን ተላጭቶ ነው እንግዲህ እንደ አዲስ ትግራይና አማራ መካከል የተሞሸረው።
ከሰላም ስምምነቱ በሁዋላ ትህነግ የአሸባሪነት ማዕረጉ ቢነሳም፣ በትጥቅ ትግል ከቀጠለው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ጦር ጋር የጀመረውን ጥምረት ይህ እስከታተመ ድረስ በይፋ አላነሳም። የፊደራል መንግስትም ይህን አንስቶ ፊትለፊት ተቃውሞ ሲሰነዝር አይሰማም።
ይህ በንዲህ እንዳለ ሻዕቢያ “ኢትዮጵያ ሰላም ከሆነች የአሰብ ወደብን ትጠይቃለች፤ ትወስድብናለች” በሚል ስጋቱና ከዚሁ ስጋት ጋር መነሻነት ኢትዮጵያን የማተራመስ የቆየ ዕቅዱ መነሻነት፣ አማራ ክልል የተፈጠረውን ትርምስ ከጀርባ ሆኖ እንደሚመራ ከበቂ በላይ ማሰረጃ እያቀረቡ ያሉ ወገኖች ቡዙ ናቸው። መንግስትም በሚያስተዳድራቸው ሚዲያዎችና በውጭ ጉዳይ በኩል ይህንኑ ጉዳይ ይፋ አድርገዋል። በተደጋጋሚም ፕሮግራም እየተሰራበት ነው። ሕዝብም “ኢትዮጵያ የጋራ” የሚለውን ክህደት ወለድ ንግግር ” ሁለቴ የሚሸወድ የለም” በሚል አሰብን በአደባባይ እየጠይቀ ርሱን የአገሩ ሰላይ ወደማድረግ እያደገ ነው።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳድር መሪ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ “ጦርነት ናፋቂና የስልጣን ጥመኛ” ሲሉ የሚጠሩት የእነ ዶክተር ደብረጽዮን አፈንጋጩ ትህነግ ሻዕቢያ ጉያ ውስጥ መወተፉን በይፋ የተናገሩት በበቂ ደረጃ መረጃ እንዳላቸው ጠቅሰው ነው። ይህን ሚስጢር ይፋ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የትግራይ ወጣቶች በቂ መረጃ እንዲኖራቸው በመደረጉ ዛሬ የትግራይ ሕዝብ ጦርነት እንደማይፈልግ፣ ይህንኑም በአደባባይ እያስታወቀ ሲሆን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችም ተመሳሳይ አቋም እያራመዱ ነው።
በሻዕቢያና በትህነግ ታጣቂ ኃይሎች የተወሰኑ መኮንኖች ስልት ወደ መንደፍ የተሸጋገረው ግንኙነት ” ብረት ያነሱ ኃይሎችን ማሰባሰብ” በሚለው ዕቅድ መሰረት በተለይም በጎጃምና በጎንደር ውስን አካባቢዎች “የአንድነት ዘመቻ” በሚል የተቀናጀ ጥቃት መሞከሩን የአገር መከላከያ አስታውቋል። በወቅቱ የአገር መከላክያ በስምንት አቅጣጫ ጥቅት ተሞክሮ መክሸፉን ከጦርነቱ ውሎ ሪፖርት ጋር በዝርዝር ሲያስታውቅ፣ የፋኖ ኃይሎችም ገደልን ያሉትን ቁጥር ጠቅሰው ድል በድል እንደሆኑ አመልክተዋል። ምግበ የሚባሉት ጀነራልም “እኔ የለሁበትም” ሲሉ አስተባብለዋል። አፈንጋጩ ፓርቲያቸውን “ስማቸው ጠፍቷል ይቅርታ ይጠየቁ” ሲል መግለጫ አውጥቶ ተከላክሎላቸዋል።
የ”ዘመቻ አንድነትን” መጀመር ሲጀመር የተነገረለትን ያህል ከተጀመረ በሁዋላ በተጠበቀውና በተነገረለት መጠን የድል ዜና አላሰማም። የድል ወሬ ባይኖርም ጅምሩ ግን ሰፊ ነበር፤ ውስጥ ውስጡን የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሻዕቢያ በተላላኪነት፣ ግብጽ በገንዘብና በቁስቁስ የምትደግፍርው የፋኖ እንቅስቃሴ አድማሱን አስፍቶ በኦሮሞ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ በትህነግ በኩል ጃል መሮና ጄነራል ተፈራ ማሞ እንዲገናኙ ተደርጓል።
ኢትዮሪቪው እንደሰማችው ሻዕቢያ ባዘጋጀው ዕቅድ መሰረት ጃልመሮና ጄነራሉ ከትህነግ መኮንኖች ጋር ሆነው የተገናኙት ኤርትራ ድንበር ነው። ጃልመሮ አስመራ ገብተው ወደ ድንበር በማምራት ከጃልመሮ ጋር የትግል አጋርነት ስምምነት አድርገዋል። ስምምነቱም ፋኖ ዘመቻ አንድነትን ሲጀመር በኦሮሚያ በሁሉም አቅጣጫ የጃልመሮ ኃይል ጦርነቱን በተመሳሳይ ቀናት እንዲያስፋፋ ነበር።
አብይ አሕመድ በፓርላማ ንግግራቸው የአገር መከላከያ በሁሉም ግንባር ስለተወጠረ ጊዜው አሁን ነው በሚል ጦርነት ለመክፈት ለሚያስቡ “አይመስለኝም” ሲሉ ምክር መሰል ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተከትሎ በትህነግ ጄነራል የተመራ የስምንት አቅጣጫ ጦርነት መከፈቱን ዜና ያደረገው ጃዋር መሐመድ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የተፋፋመ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን በማህበራዊ ገጾቹ አመልክቶ ነበር።
በዚሁ የጃዋር ዜና ” በተጨማሪ” ተብሎ እንደ አዲስ ሆኖ የተጠቆመው በምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ ምስራቅ አርሲና ሃረርጌ ዞን OLA /ኦላ አዲስ ጦርነት መክፈቱን ነው። ጃዋር ይህንን ቢልም በተባሉት አካባቢዎች በተባለው ደረጃ ጦርነት ተካሂዶ ስለተገኘ ድል ከኦላ የተሰማ ነገር የለም።
ጃዋር ለመጽሃፉ ምረቃ ዲሲ በነበርበት ወቅት ከዚህ ታክቲካል ስምምነት ጎን ለጎን በገሃድ ለሻዕቢያ ከሚሰሩት ከአቶ ነአምን ዘለቀ፣ አቶ ኤፍሬም ማዴቦና በስም ካልተጠቅሱ አንድ የሻዕቢያ ወኪል ጋር የተቀናጀ ጥቃት ስለሚፈጸምበት ሁኔታ ስብሰባ ማድረጉን ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ የአካባቢው ተባባሪዎች ለኢትዮሪቪው ጠቁመዋል።
“While Abiy, in his parliamentary speech, sought to reassure the public about the potential resumption of war in the North, fighting has intensified in both the Amhara and Oromia regions. In addition to ongoing clashes in West and East Shewa, the OLA has opened new battlefronts in the East Arsi and Hararge zones—areas where it previously had little to no presence.”
ጃዋር በአርሲና በምዕራብ ሃረርጌ በተለይም ጎሮጉቱና ካራሚላና መልካበሎ አካባቢ ኬንያ ተቀምጦ ኃይል የማደራጀት ስራ ሲሰራ እንደነበር ሚስጥር አዋቂ ነን የሚሉ የቀድሞ ባልደረቦቹ አስቀድመው ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው። ጃዋር በሃረርጌና በአርሲ ተፈፍሟል ሲል እንደ አዲስ ያስታወቀው ይህን ኃይል ይሁን ሌላ አላብራራም። በደፈናው ኦላ ሲል ነው የገለጸው። ጃዋር ለመጽሃፍ ምረቃው የአርሲና የባሌ ሰዎች ብቻ የመገኘታቸው ጉዳይ ከዚሁ ጋር ይያያዝ አይያያዝ የታወቀ ነገር የለም። ለጃዋር ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት ጃዋር ከቀድሞ ባልደረቦቹ ጋር ከተለያየና በአደባባይ ከተዘለፈ በሁዋላ በመላው ኦሮሚያ እየፈረሰ የሄደው ተቀባይነቱ ወደ ተወሰነ ግሩፕ መውረዱ ብስጭት ውስጥ ለቶታል። በዚህም የተነሳ ከፋኖ የቅርብ አመራር ነን የሚሉ የሻዕቢያን ወኪሎች ማግኘት ጀምሯል። በአማርኛም ከወትሮው በተለየ መልኩ እለት እለት በማህበራዊ ገጹ ታታሪ ለመሆን ተገዷል።
ሰላማዊ ትግል እንደሚከተል የሚገልጸው ኦፌኮ በዚህኛው የጃዋር አቋም ላይ ምን አስተያየት እንዳለው ፕሮፌሰር መራራን ለመጠይቅ ሞክረን “አሁን አይመቸኝም” የሚል መልስ ሰጥተዋል። ጃዋር የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መሆኑ አይዘነጋም።
የኦላና የመንግስት ድርድር እንዲሳካ ከፍተኛ ስራ መስራቱንና ከኦላ ጋር ኝኙነት እንዳለው በራሱ አንደበት የገለጸው ጃዋር የሻዕቢያ ወኪል ከሆኑት ከእነ ነአምን ጋር ስብሰባ መወመጡን ተከትሎ በተጀመረው ዘመቻ አንድነት ጦርነት ውስጥ ጃዋር ምን ያህል ተሳታፊ እንደሆን ለማርጋገጥ በእጅ ስልኩ ብንደውልም መልስ ሊሰጥ አልቻለም።
በዚሁ ጦርነቱን ለጥጦ የመንግስትን ጉልበት ለማዛል በተዘጋጀው ዕቅድ ኦላ ኦሮሚያ ላይ በስፋት ተንቀሳቅሶ መንገድ እንዲዘጋ፣ ከተሞችን እንዲይዝ፣ አገልግሎት መስጫዎችን እንዲቆጣጠር፣ የፋኖ ሃይሎች በዚሁ ዘመቻ ከሚያስመዘግቡት ድል ጋር በመናበብ በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት በማግኘት ድሉን የማስፋት ስራ ለመስራት ከጀነራል ተፈራ ማሞ ጋር ስምምነት ቢደረስም ይህ እስከታተመ ድረስ ይህ ነው የተባለ ድል መመዝገቡ አልተሰማም። የተያዘ በስም የሚታወቅ ከተማም ሆነ አገልግሎት ሰጪ ተቋም የለም። ይልቁኑም የአገር መከላከያ ከደመሰሳቸው ሌላ የማረካቸውን ታጣቂዎችና አመራሮች እንዲሁም ሰፊ ቁጥር ያላቸውን የኦላ አባላት በምስል አስደግፎ አሳይቷል። ጃውርን ጨምሮ ስለዚህ ጉዳይ ያሉት ነገር የለም።
ከታሰበው በግልባጭ ” የጋላን መንግስት እናስወግዳለን፤ እስከ ወለጋ ያለውን ድንበራችንን እናስመልሳለን” በሚል በግልጽ ኦሮሞ ላይ ጥላቻ አንግቦ ከተነሳ ኃይል ጋር ጃልመሮ መገናኘቱ ልዩነት ማስነሳቱ ጎልቶ ወጥቷል። በዚህም ሳቢያ ጃልመሮን ሊከዳ የሚችል ኃይ፤ እንዳለ ነው የተሰማው።
በጃል ሰኚ የሚመራው የኦላ/ ሸኔ ሰፊ ኃይል እጁን ሰጥቶ ከመንግስት ጋር አብሮ መስራት መጀመሩን ተከትሎ እጅጉኑ መመናኑ የሚነገርለት የጃልመሮ ኃይል ኬንያ ያለው መሰረቱና ምሽጉ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ያሳደረበት ጫና ሳያንሰው በዚህ ኣይነት እልፍ የማይል ስምምነት ውስጥ ተሳታፊ መሆኑ የራሱን አባላትና ደጋፊዊች ሳይቀር ማነታረኩን የድርጅቱ የቅርብ ሰዎች ይናገራሉ።
“እንደ ጅብ እንኳን ጎን ለጎን መሄድ አንችልም” ሲሉ አስተየታቸውን የሰጡት አቶ አዳባ ” በአደባባይ የጋላን መንግስት እናስወግድ” በሚል ባነር ለጥፎና መፈክር አዘጋጅቶ ኦሮሞን ለማጥፋትና ከአማራ ህዝብ ጋር ለማጣላት ከሚሰራው የፋኖ ኃይል ጋር የሚፈጠረው ሕብረት መተማመን የሚባል ነገር ከቶውንም እንደማያመጣ አመልክተዋል። እሳቸው ባላቸው መረጃ በዚሁ የሃሳብ ልዩነት ሳቢያ የተፈጠረው አለመግባብት የጃልመሮን ቡድን ይከፍለዋል።
ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኦፌኮ አመራር ” እርስ በእርሱ መስማማት ካቃተውና በአደባባይ ጥላቻን ከሚያስተጋባ ኃይል ጋር ምን የሚሉት ስምምነት ነው የሚደረገው? ለመሆኑ ድርጅታዊ ቅርፅ አላቸው? እኛን ብዙ ጊዜ በውጭ አገር አመራሮቻቸው ጠይቀውን ዝምታን ነው የመረጥነው። ገና ለገና ታቃዋሚ ነን በሚል ያገኘነውን አናግበሰብስም” በሚል የፋኖ መሪና ጃልመሮ ተገናኝተው በጣምራ ጦርነት ለማስኬድ መስማማታቸውን አውግዘዋል።