በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ካርል አደባባይ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለቢቢሲ ተናገረ።
ክስተቱ ያጋጠመው ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም. ሲሆን፤ ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተፈጠረው ‘የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም’ በሚል ምክንያት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
አቶ ሽፈራው ረጋሳ የተባለ የባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ ለሥራ ባልደረባው የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ምላሽ ባለማግኘቱ ግለሰቧን እና ከግለሰቧ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው በሚል የጠረጠረውን ሌላ ባልደረባውን በመግደል ራሱን እንዳጠፋ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ግለሰቡ የፍቅር ጥያቄ ያቀረበላት ወይዘሪት ሃና ተስፋዬ የተባለች 32 ዓመት ወጣት እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለ የሥራ ባልደረቦቹን በጥይት ተኩሶ የገደለው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ እንደገለጹት ወንጀሉን የፈፀመው የጥበቃ ሠራተኛ ካልተራው ሌላ ሠራተኛን ተክቶ በመግባት እና ከምሽት የጥበቃ ሠራተኞች የጦር መሳሪያ በመቀበል ግድያውን ፈፅሟል።
ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው ተጠርጣሪው ወደ ዕለታዊ ሥራቸው እስኪገቡ ድረስ በመጠበቅ መጀመሪያ አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለውን ግለሰብ በሁለት ጥይት መትቶ መግደሉን ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል።
ግድያው ማክሰኞ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም. ጠዋት ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ለሁለት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ድረስ ባላው ጊዜ ውስጥ መፈፀሙን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ቃል አቀባይ፤ በሁለቱ ግድያዎች መካከል እስከ 15 ደቂቃ የሚሆን የጊዜ ክፍተት እንደነበረ አመለክተዋል።
ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ ባልደረባውን ተኩሶ ከገደ በኋላ ሌላኛዋን የጥቃቱ ሰለባን ከመግደሉ በፊት ከድርጊቱ እንዲቆጠብ መጠየቁን ነገር ግን ፈቃደኛ እንዳልነበረ ተገልጿል።
ግለሰቡ መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ እና እጁን እንዲሰጥ በተደጋጋሚ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦለት የነበረ ሲሆን፣ በዚህ መካከልም ወደ ባንኩ አንደኛ ፎቅ በማምራት የፍቅር ጥያቄውን አልተቀበለችም ያላትን በተመሳሳይ ሁኔታ በጥይት መትቶ መግደሉን ፖሊስ ገልጿል።
ግለሰቡ ሁለቱን ባልደረቦቹን ከገደለ በኋላ በያዘው መሳሪያ የእራሱንም ሕይወት እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለቢቢሲ ገልጸው በክስተቱ በአጠቃላይ የሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።
ሁለቱ ሟቾች ወ/ሪት ሃና ተስፋዬ እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው የሚጠቁም ፎቶግራፎች መገኘታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ፖሊስ በምርመራው ስለግንኙነታቸው እንደሚያጣራ ገልፀዋል።
ከዚሁ ክስተት ጋር በተያያዘ ፖሊስ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ሂደት እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ቢቢሲ ስለ ግድያው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊዎችን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
BBC
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security