የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ማስጠንቀቂያ
1446ኛው ታላቁ የረመዳን ወር መስጂዶች ደምቀውና ተውበው ህዝበ ሙሊሙን በተገቢው መንገድ በመቀበል እያሰተናገዱ ነወ።
በአብዛኛዎቹ መስጂዶች ህዝበ ሙሰሊሙ እምነቱ በሚያዘው መሠረት ዒባዳውን እያከናወነ ሲሆን በጣት በሚቆጠሩ መስጂዶች ሁከት ለማስነሣት የተደረጉ ሙከራዎችን በየመሰጂዱ የሚገኙ ኮሚቴዎች፣ ሀዲሞችና ህብረተሰቡ ባደረገው ጥረት በቁጥጥር ሰር ሊውሉ ችሏል።
በተለይም ጠሮ መስጂድ ፣ሎሚ ሜዳ(ዓሊ) መስጂድና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው ሀምዛ መሰጂድ የረመዳንን መግባት ተከትሎ በአንዳንድ ሰውር አላማ ያላቸው ግለሰቦች ሁከትና ብጥብጥ በማሰነሣት ከፍተኛ ችግር ሲፈጥሩ የቆዩ አካላት መሸሸጊያ ሆኖ የቆየ ቢሆንም መጅሊስ ከዛሬ ነገ ይቀየራሉ ብሎ ሁኔታውን አባታዊ በሆነ ትዕግሰት ይዞት ቆይቷል።
መጅሊሰ በእነዚህ ጥቂት መስጂዶች የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶችን ቢያደርግም ዕድሉን ባለመጠቀም ቡድኑ መሰጂድ ሰብሮ በመግባት፣ ጄነሬተር በማጥፋት፣ ለደህንነት የተገጠመ ካሜራን በመሰባበር እና አማኞች የተረጋጋ ዒባዳ(የአምልኮ ስርዓት) እንዳይከውኑና የረመዳንን ወር የብጥብጥና የረብሻ አውድማ የማድረግ እንቅሰቃሴያቸውን ቀጥለውበታል።
ከወራት በፊት ማዕከላቸውንና የብጥብጥ መነሻቸውን ዓሊ መስጂድ በማድረግ ሴቶችና ህፃናትን ከፊት በማሰለፍና የተወሰኑ ግለሰቦችን በገንዘብ በመደለል የተጀመረው ውንብድና ኢማሞችን ማይክ ቀምቶ በመደብደብ የተራዊ ሰላት እንዲቋረጥ እሰከ ማድረግ ደርሰዋል
ይህ በግልፅ በሚታወቁ ግለሰቦች የሚመራው ቡድን በተመረጡና ለማምለጥ ምቹ በሆኑ መስጂዶች ከተለያየ አካባቢ ተጠራርተው በመግባት አወል ሰፍን (የሰላቱን የመጀመሪያ ረድፍ) ለመሰጂድም ሆነ ለሸማግሌዎች ክብር የሌላቸው አሰቀድመው በመያዝ ረብሻ በማሰነሣት መሰጂዱን አውከዋል።
በየጊዜው በየመስጂዱ እየተዘዋወሩ ሁከት የሚፈጥሩ አካላት በሚገባ የሚታወቁና መረጃ ያለን ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ለህዝብ እንደምናሳውቅ እየገለፅን መጅሊሱ ከዚህ በላይ እንደማይታገሰና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የፀሎት ቦታዎች ሠላማዊ እንዲሆኑ መስራቱን እንደሚቀጥል ለህዝበ ሙስሊሙ ያሣውቃል።
መጅሊሱ ካለበት ሀላፊነትና ተጠያቂነት አኳያ ጉዳዩን በትዕግሰት መያዙ አግባብ ቢሆንም በዚህ የሠላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመተዛዘን ወር በሁለቱ መስጂዶች በተፈጠረው አሳፋሪ ተግባር ክፉኛ ማዘኑን እየገለፀ ሙስሊሙ ማሕበረሰብ ዒባዳውን(የአምልኮ ሥርዐቱን) የሚፈፅምባቸው መስጂዶች ሠላማቸው እንዲጠበቅ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እንደሚሠራ በድጋሚ ለመግለፅ ይወዳል።
የአ/አ/ከ/እ/ጉ/ከ/ም ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
Via_dagu
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring