” የዕዳ ሽግሽግ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ትልቅ የእፎይታ ጊዜን ይሰጣል ” – ዓብዱልመናን መሐመድ (ዶ/ር)
የገንዘብ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ፣ ኢትዮጵያ ከመንግስታዊ አበዳሪዎቿ ጋራ በምርህ ደረጃ የዕዳ ሽግሽግ ለማድረግ መስማማቷን አስታውቋል፡፡
በዚህ ጉዳይ ዙርያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየት የሰጡት፣ የፋይናንስ ባለሙያው ዶ/ር ዓብዱልመናን መሐመድ፣ ” ስምምነቱ የግድ የዕዳ ስረዛን ላያካትት ይችላል፣ ግን ደግሞ የዕዳ መክፈያ ጊዜ ማራዘም በራሱ፣ ትልቅ ድል ነው ” ይላሉ፡፡
በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ጉዳዮች ላይ ለረጅም ጊዜ ትንታኔና አስተያየት በመስጠት የሚታወቁት ዶ/ር ዓብዱል መናን፣ ለውጭ ዕዳ መክፈያ ሊውል የነበረው የውጭ ምንዛሪ፣ ለሀገር ውስጥ ክምችት ማሳደጊያ እና ለሀገራዊ ልማት ሊጠቅም እንደሚችል ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ዓብዱልመናን መሐመድ በዝርዝር ምን አሉ ?
” ድርድሩ አራት አመታትን የፈጀ ነው፡፡ ሀገሪቱ ግጭት ውስጥም ስለነበረች፣ ይህ ፖለቲካዊ ምክንያት ሆኖ ለድርድሩ መዘግየቱ አስተዋፅኦ ሳያደርግ አልቀረም፡፡ አበዳሪዎቹ ሀገራት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም / IMF ጋራ መስማማትም እንደ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠውት ነበረ፡፡
ኢትዮጵያ፣ ባለፈው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ከተደረገው አጠቃላይ የማክሮ ኢከኮኖሚ ማሻሻያ ጋራ ተያይዞ ከዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም ጋራ ተስማምታለች፡፡ ከዛም፣ ቻይና እና ፈረንሳይ የሚመሩት የአበዳሪዎች ቡድን ጋራ ሲደረግ የነበረው የዕዳ ሽግሽግ ድርድር ቀጠለ።
የኢትዮጵያ መንግስት ከአበዳሪዎቹ ሀገራት ጋራ በመርህ ደረጃ ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል፡፡ እርምጃው ደስ ይላል፣ የዕዳ መክፈያ ጊዜን በማራዘም ትንሽ ፋታ ያገኛል፡፡
ይህ ስምምነት የብድር ስረዛን ላያካትት ይችላል፡፡ ግን ደግሞ የዕዳ አከፋፈል ስርዓት ለውጥ በራሱ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሀገሪቱ ዕዳዋን የምትከፍልበትን ጊዜ ያራዝምልታል ማለት ነው፡፡
በአምስት አመት ውስጥ መክፈል የነበረብህን ዕዳ በአስር አመት ክፈል ስትባል፣ ትልቅ ፋታ ይሰጥሀል፡፡ በአሁኑ ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ዕዳውን ለመክፈል የ 3 እና 4 አመታት ፋታ ያገኛል ” ብለዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር በመግለጫው፣ የዕዳ ሽግሽግ ድርድሩ፣ በቡድን 20 ሀገራት ማዕቀፍ መሰረት 8.4 ቢሊዮን ዶላር የሚሸፍን እንደሆነ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ጋራ በተደረገው ስምምነት መሰረትም፣ ኢትዮጵያ የ3.5 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ እንዲሸጋሸግላት በመደራደር ላይ መሆኗን አመልክቷል፡፡
አሁን በመርህ ደረጃ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ 2023 እስከ 2028 ድረስ የሚቆይ የ 2.5 ቢሊዮን ዶላር የእዳ መክፈያ ጊዜ እፎይታ ማግኘቷን ተገልጿል፡፡
ዶ/ር ዓብዱልመናን ስለዚህ ጉዳይ ሲያስረዱ እንዲህ ይላሉ
” ኢትዮጵያ በርከት ያለ የውጭ እዳ አለባት፡፡ ከተለያዩ ሀገራት ሌሎች ብድሮችም ቢኖሩም የመክፈያ ጊዜያቸው ረጅም በመሆኑ አንገብጋቢ አይደሉም፡፡
በጣም አንገብጋቢ የነበረው ከአጠቃላይ ዕዳዋ 8.4 ቢሊዮን ዶላሩ ነው፡፡ ለምን ብትል፣ የመክፈያ ጊዜው በመቃረቡ ነው አንገብጋቢ የሆነው፡፡ በዚህኛው የእዳ መጠን ላይ፣ የዕዳ ሽግሽግ እንዲደረግ አራት አመታትን የፈጀ ድርድር ነው የተደረገው፡፡
ከዓለምቀፉ የገንዘብ ድርጅት ጋራ በተደረገው ስምምነት መሰረት ደግሞ፣ ከ8.4 ቢሊዮን ዶላሩ ውስጥ በ3.5 ቢሊዮን ዶላሩ ላይ የዕዳ ሽግሽግ ድርድር እንዲደረግ ግፊት ሲደረግ ነበር፡፡
አሁን የኢትዮጵያ መንግስት በ2.5 ቢሊዮን ዶላሩ ላይ በመርህ ደረጃ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቋል፡፡ ይህ ማለት እ.ኤ.አ እስከ 2028 ዓ.ም ድረስ የእዳ መክፈያ ጊዜ ተራዝሟል ነው፡፡ እስከዛ ድረስ እፎይታ አግኝተናል፡፡ “
ዶ/ር ዓብዱልመናን የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት መደረጉ ኢኮኖሚያዊ አንድምታው ምንድነው ? ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፦
” የእዳ መክፈያ ጊዜን በማራዘም እፎይታ ሲገኝ፣ ለውጭ ዕዳ መክፈያ ስንጠቀምበት የነበረው ሀብት፣ የሀገር ውስጥ የውጭ ምንዛሪ ክምችትን ለማሳደግና ለልማት ስራዎች ልናውለው እንችላለን ” ብለዋል፡፡
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security