በጥንት ዘመን ኢትዮጵያ ሰፊ የባህር ዳርቻ ያላት፤ በአዱሊስና በቀይ ባህር ወደቦች የተከበበችበት ነበረች። ወቅቱም የባህር ንግድ ያበበበት እና ኢትዮጵያም መግቢያ በር ሆና የምታገለግልበት ወቅት ነበር። ግርማዊ ቀዳማዊ ሀይለስላሴም አሰብ ወደብ በተመረቀበት ወቅት ካነሷቸው ሀሳቦች ውስጥ ጠቂቱን እናካፍላችሁ።
ኢትዮጵያ፣ በጣሊያን ወረራ ወቅት የባህር በሯን የተነጠቀችና የባህር በር አልባ የተደረገች ብትሆንም በጣሊያን ወረራ ያጣችውን የባህር ወደብ መልሶ ለማግኘት ብዙ መሰዋዕትነት መክፈሏም የሚረሳ አይደለም።
እ.ኤ.አ. በ1924 ወደ አውሮፓ ኢትዮጵያ ከተጓዘችባቸው ጉዞዎች ወይም የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች አንዱ በሊዝ ውስጥ የሚገኙ ወደቦችን ነፃ የማድረግ ወይም ለኢትዮጵያ ነፃ ወደብን ማስገኘት ነበር።
የባህር ወደብ ለማግኘትም ከኢጣሊያ መሪ ጋር ውይይት ተደርጓል፤ በተደረገው ውይይት ምክንያት በኮንሴሽን ለኢትዮጵያ ሊሰጥ የታሰበው የባሕር ዳርቻ ከጥቂት ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ አይበልጥም ነበር።
ዛሬ ግን ጣሊያን ልትሰጥ ካሰበችው ጥቂት ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ በእግዚአብሔር ቸርነት ኢትዮጵያ የግዛቷ እና የራሷ ወደቦች ባለቤት ሆናለች፤ ዛሬ እዚህ የቆምነው ታሪክ ራሱን ሊደግም ባለበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ እንደገና በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ የራሷ የሆነ ተገቢ ሚና በሚኖራት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያን የንግድ ልውውጥ በፍጥነትና በጉልህ የሚስማማው የአሰብ ወደብ ሲመረቅ፣ በውቅያኖስ ላይ የተንጠለጠሉ የአለም አቀፍ ንግድ ተሸካሚዎች እንደገና በኢትዮጵያ ውሃ ውስጥ መጠለያ እና አገልግሎት ይሰጣሉ ሲሉ ግርማዊ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ በምረቃ ወቅት ተናግረው ነበር።
የአሰብ ወደብን መከፈት በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ስንመኘው የነበረ የህልም ፍፃሜና ትልቅ የስኬት ምዕራፍ ነው ያሉት ንጉሱ፤ ይህ ሥነ-ሥርዓት በጉልህ የሚያስታውሰው የባህር በሮቿን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የታሰረውን ታሪክ በሰፊው ያስታውሳል ብለዋል።
የሀገራችን ኢኮኖሚ መታፈን ብቻ ሳይሆን ወደ ባህር መውጫ አጥታ በመቆየቷ ኢክኖሚያዊ ጉዳትን አስተናግዳለች።
የአሰብ ባህር መመረቁ ኢትዮጵያ መደበኛ እና ያልተገደበ የአለም አቀፍ ንግድ ፍሬ እንዳትገኝ አድርጓታል ሲሉ በወቅቱ ተናግረዋል።
በአለምአቀፍ ህግ የውሃ መስመር አቅራቢያ ያለች ሀገር በጂኦግራፊ አቀማምጥና በታሪክ ሁኔታ ወደብ ማግኘት እያለባት አለማግኘቷ የሚያሳዝን ነበር፤ ዛሬም ቢሆን አንዳንድ የአለም ሀገራት በተመሳሳይ ቅድመ ሁኔታ ሲሰቃዩ መኖራቸው ያሳዝናል።
ከጋዜት ፕላስ የተወሰደ