የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር እንዲዘጋ የሚያደርገውን ትዕዛዝ በፊርማቸው ሊያፀድቁ መሆኑን እየተነገረ ነው።
የትምህርት እና የሲቪክ መብት ተከራካሪዎች እንዲሁም ዴሞክራት ፓርቲን የወከሉ እንደራሴዎች ትዕዛዙ የሀገሪቱን የትምህርት ሥርዓት ለማፈራረስ ያለመ ነው ሲሉ ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ስለመሆኑም ተነግሯል።
የጥቁሮች መብት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ‘NAACP’ የተባለ ተቋም ፕሬዚዳንት ዴሪክ ጆንሰን፣ “የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በፌዴራል መንግሥት ድጎማ ላይ ጥገኛ ለሆኑ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የአሜሪካ ሕፃናት የዛሬ ቀን ጨለማ ቀን ነው” ብለዋል።
የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተር ፓቲ ሙሬይ በበኩላቸው፣ “ትራምፕ እና ኢሎን መስክ ትምህርት ሚኒስቴርን ለማፍረስ የማይሆን ጨዋታ እየተጫወቱ እና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ግማሽ የሰው ኃይል እያባረሩ ነው” ሲሉ ተችተዋል።
የሀገሪቱ ብሔራዊ የወላጆች ኅብረት ደግሞ “እየተደረገ ያለው የትምህርት ሥርዓቱን ማስተካከል ሳይሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት የሚገባቸውን ነገር እንዳያገኙ የማድረግ እንቅስቃሴ ነው፤ እኛ ግን ይህ እንዲሆን በፍፁም አንፈቅድም” ብሏል።
እንደ ሚዲያዎች ዘገባ ከሆነ ትራምፕ የሚፈርሙት ትዕዛዝ የትምህርት ሚኒስትሯ ሊንዳ ማክማሆን የትምህርት ሚኒስቴሩ እንዲዘጋ አስፈላጊውን ሒደት እዲያመቻቹ እና ሥልጣኑን ለግዛቶች አንዲያስተላልፉ ያዝዛል።
በዚያውም አሜሪካውያን የሚተማመኑባቸው ውጤታማ እና ያልተቋረጡ አገልግሎት፣ ፕሮግራሞች እና ጥቅሞችን እንዲያቀርቡ የማድረግ ሥራዎች ይሠራሉ ይላል።
የትምህርት ሚኒስቴር ፈንድ ተጠቃሚ የሆኑ ማናቸውም ፕሮግራሞች እና ኢንሼቲቮች የብዝኃነት፣ የፍትሕን እና የአካታችነት እንዲሁም የሥርዓተ-ፆታ ፕሮግራሞችን ማስፋፋት እንደማይችሉም የሚደነግግ መሆኑን የኋይት ሐውስ መገለጫ አመልክቷል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የትምህርት ሚኒስቴሩን አባካኝ እና በሊበራል ርዕዮተ ዓለም የተበከለ ነው ብለው እንደሚያስቡ አልጀዚራ ዘግቧል።
ይሁንና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከተቋቋመበት የ1979ኙ የኮንግረስ አዋጅ ውጪ ሚኒስቴሩን የማፍረሱ ጉዳይ እውን ሊሆን እንደማይችልም ETV ዘገባ አመላክቷል።
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security