ከመቼውም ግዜ በላይ ኢትዮጵያ አሰብን ወደራሷ መቀለቀል የምትችልበት ሁኔታ እየተፈጠረ መጥቷል። ኢትዮጵያ በዚህ ግዜ አሰብን መታደግ ካልቻለች ምናልባት “ኦልድ አቢሲኒያ – አጋዚያን ” ተብሎ ሊቋቋም የሚችለው አዲስ ሀገር ሊጠቀልለው ይችላል – እኔ ግን ይህ የሚሆን አይመስለኝም!!!
የአለም ኢኮኖሚ የሚንቀሳቀሰው በነዳጅ ነው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁን ነዳጅ የምታመርተው ሳዑዲ አረቢያ ናት። ትልልቆቹ ነዳጅ ገዥዎች ደግሞ አሜሪካና አውሮፓ ናቸው።
የሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ክምችት ያለው በሀገሪቱ ምዕራባዊ ግዛት በኩል ነው፤ በዚህ የተነሳ ሳዑዲ ለረጅም ግዜ ኢራን በምትቆጣጠረው ባህር በኩል ነዳጇን ለምዕራባውያኑ ስታቀርብ ቆይታለች። ነገር ግን ኢራን ከሳዑዲ አረቢያ ጋር እያደር እሳትና ጭድ እየሆነች በመምጣቷ የነዳጅ ዝውውሩ መስተጓጎል ጀመረ።
ለዚህ ጉዳይ መላ ሲፈለግ ቀይ ባህር ተመራጭ ሆነ፤ ሳዑዲ አረቢያም ነዳጇን ከምዕራብ ወደ ሠላም ቀጣና ቢሊዮን ዶላሮች መድባ በፓይፕ ማጓጓዝ ቻለች – ጉዳዩ ለግዜው ተፈታ።
ነገር ግን ኢራን የየመን ሁቲ አማፅያንን በማስታጠቅ የቀይ ባህርን የመርከብ ጉዞ ማወክ ጀመረች። አማፅያኑ እስራኤል ላይ ሮኬት ማስወንጨፋቸውን ልብ ይሏል !
የነዳጅ ተጠቃሚዎቹ አሜሪካና አውሮፓ የየመን አማፅያንን ፀጥ ለማድረግ ሚሳኤል መተኮስ ሁሉ ጀመሩ – ነገር ግን ኢላማቸው ቋጥኝ እንጂ የታጠቀውን ኃይል መምታት አልቻለም። አንድ የምዕራብ ሚሳኤል ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጭ አለው ። የሁቲ አማፂ አንድ የመርከብ ኢላማ ደግሞ ሃያ ሺህ ዶላርም አይሞላም – ውጊያ አዋጭ መሆን አለበት እንዲ የሞንጎሉ ጂንግስ ካሃን!
በቀይ ባህር ጂኦፖለቲክስ ግራ የተጋቡ የነዳጅ ተጠቃሚ ሀገራት የጦር ሰፈራቸውን በቀይ ባህር ዙሪያ መትከል ቢጀምሩም፣ ይሄም ውጤት አላመጣም! መፍትሄው ኢትዮጵያ እጅ ላይ እንዳለ ዓለም ዘግይቶ ነው የገባው።
በፊት በፊት ምስጋና ለቀድሞው ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም ይሁንና ኢትዮጵያ ከየመን ጋር ጥሩ ግንኙነት አላት። የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ በሃኒሽ ደሴቶች ይገባኛል ውዝግብ ከየመን ጋር ሲዋጋ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ወረራውን ለማስቆም የተጫወቱት ሚናም ቀላል አልነበረም። አሁን በቅርቡ የመን በጦርነት ስትናጥ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንደተሰደዱ ልብ ይሏል!!!
አሁን የቀይ ባህርን ችግር ልትፈታ የምትችለው የዶ/ር ዐቢይ ኢትዮጵያ ብቻ ናት! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሶፍት ዲፕሎማሲ ይህንን ሥራ በሚገባ እየሠሩ እንደሆነ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ! ሰውየው ብዙ ርቀት ሄደው ታላቋን ኢትዮጵያ ሊመልሱ ከጫፍ ደርሰዋል!
የቀይ ባህር ተዋሳኝ ስምንት አገሮች ይህንን ችግር አልፈቱትም ፍሬ አልባ ሆነ እንጂ ኢትዮጵያ የሌለችበት የቀይ ባህር ፎረምን ሁሉ መስርተዋል – የአረቡ ዓለም ቅብ ነኝ የምትለው ግብፅም ይህን ችግር አልፈታችውም፣ ግብፅ አንድ ነገር አድርጊ ስትባል አባይን ከሰጣችሁኝ ብላ ቅድመ ሁኔታ የምታስቀምጥ ሀገር ሆናለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ግን በአባይ አትምጡብኝ ብለዋል! ስለ አብርሃም አኮርድ ፈትፍቶ ሚያጎርሰን ሰው ቢኖር አሪፍ ነበር !
ግብፅ በዓመት አስር ቢሊዮን ዶላር የምታገኝበት ስዊስ ካናል ጥቅም አልባ እንዳይሆን፣ ሳዑዲ አረቢያም 70 ከመቶ በላይ ፖለቲካዋ የተመሠረተበት ፔትሮ ዶላር ጭራሹኑ ወደ ኤሌክትሪኮ ዶላር እንዳይዞር፣ የትራምፕ ከጦርነት ነፃ የሆነ ምድር የመፍጠር ዕቅድ እንዲሳካ፣ የኢትዮጵያ አስፈላጊነት ጎልቶ ወጥቷል – አሰብ ለኢትዮጵያ እንደሚገባ ዋና ዋናዋቹ አምነውበታል !
ይህ ግዙፍ ዕቅድ መሳካቱ አይቀርም – ለሚያልፍ ብስጭት የሚያስቆጫችሁን ታሪክ አትፃፉ !
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ ያጣችው የለምና !
WZ news
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security