በትግራይ ክልል ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች እስካሁን ወደ ትምህርት ገበታቸው አልተመለሱም ተባለ
በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ የወደሙ እና ወደ ሥራ ያልተመለሱ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስዩም ሀጎስ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ምዕራብ ትግራይ በሌሎች ኃይሎች ቁጥጥር ሥር በመሆኑ ትምህርት ለማስጀመር እንዳልተቻለ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ እንደ እቅድ ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ ከታሰበው 2 ነጥብ 45 ሚሊየን ተማሪዎች ውስጥ እስካሁን ወደ ትምህርት መመለስ የተቻለው 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ያክል ተማሪዎችን ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከነዚህም ውስጥ ባለው ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡”በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ቢሞከርም፤ ባለው የምግብ አቅርቦት ችግር እና በሌሎችም ተደራራቢ ጫናዎች ምክንያት ታዳጊዎቹ ለልመና እና ለቀን ሥራ እየተዳረጉ በመሆኑ ጥረቱን አስቸጋሪ አድርጎታል” ብለዋል፡፡
“በመጠለያ ውስጥ ያለው የእርዳታ አቅርቦት የሚፈለገውን ያህል ባለመሆኑ ወላጆቻቸውም ሰርተው ልጆቻቸውን ማስተማር የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ባለመሆናቸው፤ በተለይም እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናት ምግብ ለማግኘት ወደ ልመና ይሰማራሉ” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ግጭት ብሎም ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋ በተከሰተባቸው ክልሎች በርካታ ሕጻናት እና ወጣቶች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው የሚገለጽ ሲሆን፤ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ዓመት እንደ ሀገር ከ7 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
TIPS
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security
Ethiopia, Creditors Agree on $8.4 Billion Debt Restructuring