“ባለፉት ሃያ ቀናት በትግራይ የሚታየው ፖለቲካዊ ትርምስ ስልጣን ወይም የሞት ሽረት ብሎ የተነሳው ኋላቀር ቡድን ላለፉት ሁለት ዓመታት የተበተበው ሴራ የመጨረሻ ጡዘት/ምዕራፍ መድረሱን ያመላክታል::
“[ትህነግ] ምዕራብ ትግራይ [ወልቃይት] ሲባል ለሰሊጥ መሬቱ እንጂ ስለ ተፈናቃዮቹ ተጨንቆ አያውቅም” – ጌታቸው ረዳ
ህግና ስርዓት ያስከብራሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው አንዳንድ የተሻለ ታሪክ የነበራቸው ዝነኛ ሰው ሳይቀሩ የሥርዓቱ ጭቃ ውስጥ ገብተው የሚያቦኩበት ከፍታ ላይ ነው የተደረሰው::
ከማህተም መልቀም ዘመቻ በኋላ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በጉልበት የተቆጣጠረው ኃይል እስካሁን ያከናወናቸው ነገሮች ሁለት ብቻ ናቸው።
በመጀመሪያ ተቆጣጥሬያቸዋለሁ በሚላቸው ዋና ዋና ከተሞች ደጋፊዎቼ ለሚላቸው መሬት ማከፋፈል እና ለገቢ ምንጩ ሽያጭ የሚውል ሰፋፊ መሬት መውረር ይጠቀሳል።
ዋነኛ ትኩረቱም በመቐሌ/ሓድነት፣ በሽሬ/በታች ቆራሮ፣ በአክሱም/፣ በማይጨው እና በአዲግራት እና በአካባቢው ተጀምሮ ከምእራብ ትግራይበስተቀር በሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች ይቀጥላል።
ያገኘውን መሬት ለመከፋፈልና ለመሸጥ እንጂ የጠፋውን ለመመለስ ምንም ፍላጎት ወይም ተነሳሽነት የሌለው ኃይል በመሆኑ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት ለመመለስና የትግራይን ሉዓላዊ መሬት ለማስመለስ ከመፈክር ያለፈ ጥያቄ እንኳን ሲያቀርብ አልታየም። ስለሆነም መላው የትግራይ ወጣቶች መሬታችሁን ከሽፍቶች ጠብቁ።
በማህተም ቀሚዎች የተወሰኑ ውሳኔዎች ህጋዊ ተቀባይነትን ተፈጻሚነት እንደማይኖራቸው በመገንዘብ በመሬት ወረራ እንድትሳተፉ በመጋበዝ ላይ የምትገኙ ባለሀብቶችም ገንዘባችሁ ቁምነገር ላይ መዋሉን አረጋግጡ።
ሁለተኛው የዚህ ኋላቀር ቡድን ትኩረት አዲስ አበባ እየተመላለሰ ስልጣን ይገባኛልና አጽድቁልኝ እያለ ደጅ መጥናት ነው።
‘ሰላም ፈላጊዎች ነን፤ የፕሪቶሪያውን ውል እናስፈጽማለን፤ ብቻ ወንበር እንረከብ’ በማለት እየተማለደ ይገኛል።
ፕሬዚዳንት መሾም ስልጣኑ እንዳልሆነ እየተቀበለ ነገር ግን እነእገሌ ለፕሬዝዳንትነት አጭቻለሁ እያለ፤ እጩዎች የሚላቸውንም በየሦስት ቀኑ እየቀያየረ ዕድሉን እየሞከረ ነው። አሁንም ቢሆን ስለተፈናቃዮችና ምእራብ ትግራይ ተሳስቶም የሚያነሳበት አጋጣሚ የለም፤ አጀንዳውም አይደለም።
ምዕራብ ትግራይ ሲባል የሰሊጥ መሬት እንጂ የተፈናቀለው መከራና ስቃይ ላይ የሚገኘው ህዝብ አይታየውም::
ይህ ቡድን እና አሽከሮቹ በህልማቸውም ሆነ በእውናቸው የማይፋቷቸው ሁለት አጀንዳዎች ካሉ መሬት እና ስልጣን ብቻ ናቸው።
የመላው ህዝባችን ሰላም፣ የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ተስፋ እና የትግራይ ወጣቶችን መጻኢ ህልምና ነገን ቀምተው ሊፋቱት ያልቻሉትን አመላቸው ለማርካት ወደሌላ ዙር የጥፋት አዙሪት ሊያስገቡን ቋምጠዋል።
ለትግራይ ህዝብ በትግረኛ ያስተላለፈው መልዕክት ትርጉም በአማረኛ: