“ሰሜኖቹ” በሚል ሻዕቢያ ጠርናፊና የኦፕሬሽን ማናጄር ሆኖ እየመራው ያለው አዲሱ ጦርነት ከወትሮው የተለየ ያሳየው አዲስ ነገር ቢኖር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ታላላቅ መንግስታት ” ኢትዮጵያን አስቁሙልኝ” የሚለው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አዲሱ ልምምድ ነው። ይህን የሚለው ሻዕቢያ ጎን ለጎን የወታደራዊና ደህንነት መኮንኖቹን መቀለና አዲግራት እያስገባ ነው። ትግራይን ያደማው፣ የዘረፈው፣ ያወደመውና በጅምላ የጨፈጨፈው ሻዕቢያ ወደ መቀለ የገባው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከተገለበተ በኋላ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የነበራቸውን መዋቅርና አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ከዓለም አግልለው በማዕቀብ ቅርቃር ውስጥ ከተው ሽባ ያደረጉት ሻዕቢያ ለውጡን ተከትሎ ጨለማው የተገፈፈለት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በጻፉት “ልቀቁዋቸው” ደብዳቤ እንደሆነ ይታወሳል።

photo- In this Nov. 21, 2020 file photo, refugees who fled the conflict in Ethiopia’s Tigray region arrive with their furniture and donkey on the banks of the Tekeze River on the Sudan-Ethiopia border, in Hamdayet, eastern Sudan. (AP Photo/Nariman El-Mofty)
ይህን ጨምረው ያንብቡ Witnesses: Eritrean soldiers loot, kill in Ethiopia’s Tigray
Our season’: Eritrean troops kill, rape, loot in Tigray
በዚህና በሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ቂም የያዘው ሻዕቢያ ቀን ጠብቆ ትህነግ የሰሜን ዕዝን በክህደት ሲያርድ ወደ ትግራይ ያለ አንዳች ከላካይ ነዋሪዎችን በጅምላ ጨፈጨፈ። ዕድሜ ሳይለይ በደቦ አስገድዶ ደፈር። ተደራጅቶ ፋብሪካ ነቅሎ አጋዘ። የልማት፣ ህክምና ተቋማትንና ዩኒቨርስቲዎችን ኦና አደረገ። ጣሪያና ግድግዳ ሳይቀር እያፈረሰ አጋዘ፣ ቲቪና ማቀዝቀዣ ብቻ ሳይሆን ጭልፍ፣ ጀሪካን፣ ድስት፣ ካልሲና መወልዋያ ሳይቀር ጠራርጎ ወሰደ።
ትህነግ በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ክህደትና አማራና አፋር ክልልን ወሮ ያደረሰው ሰብአዊና ቁሳዊ ጥፋት የሕዝብን ስሜት ስላጎሸው፣ በወቅቱ ሻዕቢያን በሚገባው ደረጃ ማውገዝ ባይችልም፣ ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በሁዋላ ሻዕቢያና “ኢትዮጵያዊ” የሚሰኙ ተከታዮቹ በቅጽበት ያሳዩት ኩርፊያ በርካታ ጉዳዮችን ገላልጧል።
አጋጣሚውን ጠብቆ ከፌደራል መንግስት ጎን የቆመው ሻዕቢያ የፕሪቶሪያውን ስምምነት በገሃድ ተቃውሞ የተጀመረውን ወዳጅነት በመተው ወዲያውኑ ኢትዮጵያ ላይ ጦር የሚሰብቁ ኃይሎችን ከወትሮው በበለጠ ማዘጋጀት መጀመሩን መረጃዎችን ጠቅሰን መዘገባችን
ለዚህም ይመስላል ታዋቂው ዘ-ኢኮኖሚስት ይህንኑ ታሪክ አስታውሶ ሻዕቢያ ከትህነግና ከፋኖ ኃይሎች ጋር ግንባር ገጥሞ መንቀሳቀሱ በትግራይ ክልል ውጥረት እንዲበረታ አድርጓል።
ዘኢኮኖሚሲት ቢሮው ምንጮቹን ጠቅሶ በትግራይና በኢትዮ ኤርትራ ዙሪያ ባቀረበው ሪፖርቱ ላይ ሻዕቢያና ትህነግ እንዲሁም ፋኖ እያስተባበሉት ያለውን የመጣመራቸውን ጉዳይ ይፋ አድርጓል።
ሰሞኑን ርዕዮት ከአቶ ልደቱ ጋር አጣምሮ ያነጋገራቸው ኢንጂነር ይልቃል ” ከኤርትራ መንግስት ጋር አብሮ መስራት አስፈላጊ ነው” በሚል በትነተና አስደግፈው በይፋ አካሄዱን አድንቀው ምላሽ ሲሰጡ ተደምጠዋል።
ከዚህ ቃለ ምልልስ በሁዋ የርዕዮት ሚዲያ ባለቤት ቴዎድሮስ ከአሉላ ጋር ባቀርበው ውይይት ” ትህነግ አንድነቱን ሳይጠብቅ፣ በደከመበት ወቅት የሚፈጥረው ሕብረት አሽከር ያደርገዋል የሚል ስጋት አለብኝ እንጂ አብይን ለማስወገድ ህብረት መፍጠራቸውን እደግፋለሁ” በሚል ያለውን መረጃ ከነስጋቱ አቅርቧል።
ዘኢኮኖሚስት በማርች 11 ቀን 2025 ኤርትራን ከትግራይ በሚያዋስነው አዲግራት ከተማ ጭምብል የለበሱ በርካታ ታጣቂዎች መታየታቸውን እማኝ ጠቅሶ ዘግቧል። አቶ ጌታቸው ረዳና የተለያዩ ሚዲያዊች በመረጃ አስደግፈው ይህንኑ እውነት አስቀድመው የዘገቡ ሲሆን አዲስ የተሰማው የጭምብል መልበሱ ጉዳይ ነው።
እነዚሁ ታጣቂዎች ፊታቸው በጥቁር ጭንብል ተሸፍኖ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ወርረው ከንቲባውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ዘገባው አስረድቷል።
ሻዕቢያና ትህነግ ቀደም ሲል ባደረጉት ሚስጢራዊ ውይይትና ውይይቱን ተከትሎ ባዘጋጁት ዕቅድ፣ በትግራይ ያለውን ጊዜያዊ አስተዳደር ማፍረስ ላይ ስምምነት መድረሳቸውን የደህንነት ምንጮችን ጠቅሰው መረጃ ያካፈሉ እንዳሉት አቶ ጌታቸውም ይህንኑ አረጋግጠዋል። አቶ ጌታቸው አፈንጋጩ ትህነግ ዲ፣ ይህንኑ በማድረግ ለሻዕቢያ መተማመኛ መስጠቱን ከመቀለ ” አምልጬ መጣሁ” ባሉበት መግለጫቸው አረጋግጠዋል።
ይህንኑ ውል ተከትሎ በየደረጃው የጊዜያዊ አስተዳደሩን ያፈረሰው ደብረፂዮን የሚመራው ቡድን ባለፈው ሳምንት በዶክተር የመቀሌ ከተማን መቆጣጠሩን እና በርካታ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ደጋፊዎች፣ አክቲቪስቶች መታሰራቸውንና መደብደባቸውን ዘኢኮኖሚስት ይፋ አድርጓል። ተገባሩን በተቃወሙ ላይ መሳሪያ ተተኩሶ የሞቱና የቆሰሉ መኖራቸው በመስልና በቪዲዮ ተደግፎ መቅረቡ ይታወሳል።
ዘኢኮኖሚስት ዝርዝር ጉዳችን አመላክቶ እንዳለው ከሆነ ይህ ሁኔታ አሁን ላይ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለተፈጠረው ችግር ሌላ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው።
ባልተለመደ መልኩ ለዓለም መንግስታትና ህብረቶች ” ኢትዮጵያን አስቁሙልኝ” በሚል በተደጋጋሚ እየተማጸነ ያለው ሻዕቢያ፣ ቀደም ሲል በባህር ዳር ቅርንጫፍ ቢሮ ከፍቶ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከመንግስት እንዲያፈነግጡ ሲያደራጅ እንደነበር አሁን ዱባይ የሚገኘው የስለላ ሰራተኛ ለኢትዮሪቪው አስቀድሞ መረጃ መስተቱ አይዘነጋም።
ለውጡን ተከትሎ ሻዕቢያ ወደ አዲስ አበባ ከላካቸው የስለላ ሰዎች መካከል አንዱ የነበረና የስራ ጊዜውን ሲጨርስ ወደ አስመራ ሳይመስል ዱባይ ኑሮውን የጀመረው ይኸው ሰላይ “የኤርትራ ኤምባሲ ሰዎች ውሏቸው ባህር ዳር ነበር፤ የክልሉን የልዩ ኃይል መሪዎችና አሁን ላይ በጎጃም ፋኖን እየመራን ነው ከሚሉት ጋር አብረው ይመክሩ ነበር” ሲል ምስክርነቱን ሰጥቶ ነበር» አዲስ አበባ እስር ላይ ያሉ የኦሮሞና አማራ ትግል መሪዎችንም በመልዕከተኛ የማገናነት፣ ሰነድ እያዘጋጁ የመለዋወጥ ስራ ጎን ለጎን ይሰራ እንደነበር ዝርዝር መረጃ ሰትቶ ነበር» ስም ጠቅሶ ማን ከማን ጋር እንዲገናኙ ይደረግ እንደነበር መረጃው ያስረዳል።
” ይህ ሁሉ ሲሆን መንግስት አያውቅም ነበር” በሚል በወቅቱ ለተጠየቀው ” በወቅቱ መንግስት ገና ዳዴ እያለ ነበር። ገና ሁሉንም በአዲስ ባማዘጋጀት ላይ ተጠምዶ ስልበነር ሻዕቢያን ተው ማለት አይችልም። እያወቀ እንዳላወቀ ይሆን ነበር” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
“ኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት አላቸው እሱም ትህነግ ነው” በሚል የአትላንቲክ ካውንስሏ ብራውኒ ከጦርነቱ በፊት ባቅረበችው ሰፊ ትንተና፣ ትህነግ አቅሙ ከተዳከመ በሁዋላ ኤርትራ ውስጥ ያለው ሁኔታ በፍጥነት ካልተቀየረ ችግር እንደሚፈጠር ተንብያ ነበር።
ብራውኒ እንዳለቸው እ.ኤ.አ ከ 2020 እና 2022 በትግራይ በተደረገው ጦርነት የኢሳያስ ጦር ከፌዴራል መንግሥቱ ጦር ጋር በመሆን በትህነግ ላይ ” የጋራ ጠላት” በሚል አብረው ዘምተው እንደነበር ዘ- ኢኪኖሚስት ያስታውሳል።
ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሁዋላ ያኮረፈው ሻዕቢያ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሃይሎችን እያስታጠቀ መሆኑን፣ ከግብፅ፣ከሶማሊያና የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ከሆኑ ኃይሎች ጋር ጥምረት መፈጠሩን ዘ-ኢኮኖሚስት ይፋ አድርጓል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሆነ ዲፕሎማቶችና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች ትህነግና ሻዕቢያ ግንባር ገጥመው የፕሪቶሪያውን ስምምነት እየናዱት እንደ ሆነ ጠቅሰው ” አንድ በሉን፣ አለበለዚያ ውርድ ከራስ” ማለታቸው አይዘነጋም፤ በዚሁ መድረክ ላይ አቶ ጌታቸው ረዳም በተመሳሳይ በክልሉ የሚያውቁትን እውነት ዘርዝረው አስረድተው ነበር።
ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት፣ ይህም የህልውና ጉዳይ እንደሆነ፣ 130 ሚሊዮን ሕዝብ ተቆልፎበት ሊኖር እንደማይችል፣ ጠቅላይ ሚኒስት አብይ መናገራቸውን ተከትሎ ሻዕቢያ ከግብጽና ከሶማሌያ ጋር አብሮ ዘመቻ መጀመሩ ይታወሳል። በዚሁ መንደርደሪያ ዘ- ኢኮኖሚስት አሁን ላይ በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በሚገኘው የትግራይ ክልል ያለው ቀውስ ወደ አደገኛ ደረጃ መሸጋገሩን አመልክቷል።
ያለፉትን ሳምንታት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረገው የትግራይ ታጣቂ ኃይል አሁንም በአስር ሺዎች የሚቆጠር ጦር የያዙ ተዋጊዎች እንዳሉት የጠቀሰው ዘ-ኢኮኖሚስት፣ ትህነግ አሁንም ትልቅ የሀይል ሚዛን እንዳለው ጠቅሷል።ዘ-ኢኮኖሚስት በአስር ሺህ ሲል የጠራው የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች፣ ቁጥር 270 ሺህ መሆኑን አቶ ጌታቸው ረዳ ለደሞዝ ከስምንት ቢሊዮን ብር በላይ ማውጣታቸውን ይፋ ባደረጉበት መግለጫቸው አስታውቀው ነበር።
ዘ- ኢኮኖሚስት ባያብራራውም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኤርትራ ጋር በሚደረገው ጦርነት ከጎናቸው እንዲሰለፍ የትህግን አመራሮች ከዚህ ቀደም ጠይቀው እንደነበር አስታውሷል። ጥያቄውም በወቅቱ ተቀባይ እንዳልሆነ አመልክቷል።
ሙሉ መረጃው ግን ከሸቢያ ጋር ጥብቅ ትሥሥር ይላቸው አቶ ስብሃት ነጋ ከእስር ተለቀው ወደ አሜሪካ እንዳቀኑ ከሸዕቢያ ጋር ጥብቅ ግንኙነት መጀመራቸውን ላይ የተንጠለጠለ ነው። ቀድሞም የነበረው ይህ ግንኙነት፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት ያኮረፈውን ሻዕቢያን ለበቀል እንዲነሳ ስለገፋው በሚገርም ፍጥነት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ተሸጋገረ።
በህገወጥ የወርቅ ንግድ ታጅቦ የተጀመረው ግንኙነት ውስጥ ውስጡን ከሚሰማው የተጨለፈ መረጃ አልፎ በይፋ የኤርትራ ሰራዊት አመራሮች ትግራይ ምድር ድረስ እየዘለቁ የጦርነት ዝግጅት እንደሚያደርጉ የገለጽ ጀመር።
በስም የሚታወቁ የትግራይ ታጣቂ መሪዎች በገሃድ የፌደራል መንግስቱን ለመጣል ከኤርትራ ጋር ህብረት ለመፍጠር እንደሚሰሩ መናገር ጀመሩ። ከመንግስት ወገንም የድህንነት መረጃ ያላቸው ቦታና ቀን እየጠቀሱ ግንኙነቱ መፋፋሙን ማስታውቃቸውን ተያያዙት።
“ወሬ ነው። ስሜ በሃሰት እየተነሳ ነው” በማለት ሲያስተባብልና ኢትዮጵያ ወረራ ልትፈጽምብኝ ነው በሚል ተከታታይ አቤቱታ እያሰማ ያለው ሻዕቢያ ማስተባበያው ሃሰት መሆኑን ዘ – ኢኮኖሚስት ከዘገበው ዘገባ ለረዳት ይቻላል።
“የኤርትራ ወታደራዊ አማካሪዎች እና የመረጃ መኮንኖች ባለፉት ቀናት አዲግራት እና መቀሌ መግባታቸውን ከታማኝ የመረጃ ምንጮች ሰምቻለሁ” ሲል ያስታውቀው ዘ- ኢኮኖሚስት “ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አቶ ጌታቸውን ወደ ስልታናቸው ለመመለስ ወታደሮችን ወደ ትግራይ ከመላክ ይልቅ ትግራይን ለደብረጽዮን ቡድን የሰጡ ይመስላል” ሲል አስተያየቱን አክሏል።
ባሳለፍነው ሳምንት ታንኮች፣ ሎሪዎች እና ቡልዶዘርን ጨምሮ ትላልቅ ወታደራዊ ኮንቮይዎች በአፋር በኩል ወደ ትግራይ ምስራቃዊ አቅጣጫ ሲጓዙ እንደነበር ዘገባው አክሏል። ይሁን እንጂ ከመንግስት ወገን የተባለ ነገር የለም።
መንግስት ምንም መረጃ ባይሰጥም የኢትዮጵያ መከላከያ ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ እና ከኤርትራ የአሰብ ወደብ በስተ ምዕራብ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ቡሬ ከፍተኛ ኃይልና ማከማቸቱና ሜካናይዝድ ብርጌዱን በተጠንቀቅ ማስቀመጡን እማኞች ይገልጻሉ። ኤርትራም ይህንኑ ለመከላከል ይመስላል አሰብ ጫፍ ላይ የአየር መቃወሚያን ጨምሮ በርካታ ዳግም ዘመች ጦር ማስፈሯ ተሰምቷል።
የኤርትራ መንግስት ከየካቲት ወር ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወታደራዊ ግዳጅ ማወጁን ዘገባው አስታውሷል። ኢትዮጵያ ወደ ቡሬ ብረት ለበሶችና ሰፊ ኃይል ማስጠጋቷንም አመልክቷል።
ሰፊ ትነተና ያቀረበው ዘ-ኢኮኖሚስት የፌዴራል መንግሥቱ በትግራይ የተፈጠረውን ቀውስ በማርገብ እንደሚገባው መክሯል። አለበለዚያ ግን ከኤርትራ ጋር ካለው ውጥረት ጋር ተያይዞ ከባድ ቀውስ ሊፈጥር እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኤርትራ ሙሉ አጋዥነት የሚመራው የጎጃም ፋኖ ትህነግ ወልቃይትን ዳግም እንዲይዝ ስምምነት መደረሱን በጎንደር ላይ ክህደት ተደርጎ እንደሚወሰድ የወልቃይት ጠገዴ ሴቲት አካአቢ ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው። ይህን ስምምነት አስመልክቶ ከጎጃም ፋኖ ለጊዜው በግልጽ የተባለ ነገር የለም» ትህነግና ፋኖ አሁን ላይ ተስማምተው ጀምረውታል በተባለው ኦፕሬሽን ወልቃትን አስመልክቶ ያደረጉት ስምምነት በርካታ የአማራ ተወላጆችን እያነጋገረ ነው። ትህነግ ምዕራብ ትግራይ የሚለውን አካባቢ በምንም መልኩ እንደማይደራደርበት በተደጋጋሚ ያስታወቀና አቋሙ ግልጽ በመሆኑ ከትህነግ ጋር አብረው የሚሰሩ የፋኖ ኃይሎች ይህን አስመልክቶ አቋማቸውና ውላቸው ግልጽ ሊሆን እንደሚገባ በተደጋጋሚ እየተጠየቀ ነው።
በሰሞኑ የጦርነት ዜና ፋኖ በመቶዎች ገደልኩ ሲል፣ የአገር መከላከያ በበኩሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች በአንድነት የተከፈተው ዘመቻ መክኖ፣ በመቶዎች መገደላቸውን፣ መቁሰላቸውንና መማርካቸውን አስታውቋል።