ሃሰን ሼኽ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስና የገብጹ መሪ አልሲሲ ጋር በፍቅር ከንፈው ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመው ነበር። ኤርትራና ግብጽ ሶማሊያን እንደሚታደጓት ሲገልጹና ሲዘምሩ ነበር። እንደ ውሃ ቀጂ ኤርትራና ግብጽ ሲመላለሱና ኢትዮጵያ ላይ ሲፎክሩ የነበሩት ሃሰን ሼኽ “ሰብር ፣ ቀልብ ግዙ” በሚል ተመክረው ነበር። የወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አቅጸስላሴ “መንግስት አክቲቪስት ከሆነ ዋጋ የለውም” በማለት ነበር ወደፊት ሊሆነ የሚችለውን በስጋት ያስቀመጡት።
የኢትዮጵያ መንግስት ከሞቃዲሾ ንቅንቅ ማለት ያልቻሉትን ሃሰን ሼኽን ከመምከር አልፎ ገስጾም ነበር። በስተመጨረሻ አልሸባብ ስጋት ሲሆን ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ቢያወርዱም የተሳካላቸው አይመስልም። ግብጽ በድጋፍ ስም ሶማሊያ የጦር መሳሪያ ካፈሰሰችና ኤርትራ ስለጠኑ የተባሉ ወታደሮች ወደ ሶማሊያ ከገቡ በሁዋላ አልሸባብ ጥቃቱ ጨመሯል። ጉዳዩ የሚጠናና በትኩረት ሊታይ የሚገባው ቢሆንም እስካሁን የጥርጣሬ መረጃዎች ከመውጣታቸው በቀር ሌላ በይፋ የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ ግብጽ በስራቅ በኩል ኢትዮጵያ ሌላ የውጊያ ቀጠና እንዲገጥማት ዕቅድ በመያዝ መንቀሳቀስ መጀመሯ ገሃድ ነው።
ለዚህም ይመስላል ኢትዮጵያ ግብጽ እያራገፈችው ያለው መሳሪያ አልሸባብ እጅ ሊገባ እንደሚችል ስጋቷን ገልጻ ለተመድና አፍሪካ ህብረት አስታውቃ የነበረው። የተፈራው ደርሶ ዛሬ ከሞቃዲሾ የሚሰማው ዜና ከፍቷል። ግብጽና ኤርትራ አቀጣጥለው ዝምታን መርጠዋል።
የሶማሊያ ጦር እየፈረሰ አልሸባብ ወደ ዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ እየገሰገሰ መሆኑ እየተሰማ ነው። ትናትን ሶማሊጋርዲያን እንደዘገበው በግምት ከሞቃዲሾ 10 ኪሎሜትሮች እርቀት ላይ በአልሸባብና በሶማሊያ ጦር መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው። ቱርክ ኮምንዶ ኃይሏን ልካ ድጋፍ እየሰጠች ነው።
የአሁኑ የአልሸባብ ግስጋሴን ከታሊባን የ 2021 ግስጋሴ ጋር እያነፃፀሩት ያሉ በርካታ ወታደራዊ ጠበብቶችና የፖለቲካ ተንታኞች የሶማሊያ መንግስት በቅርቡ በአልሸባብ ይወድቃል የሚል ስጋታቸውን እያስቀመጡ ይገኛሉ። የአሚሶም ጦርም የአልሸባብን ግስጋሴ ማስቆም እንደተሳነው እየተገለጸ ነው።
ወደ ሞቓዲሾ እየገሰገሰ መሆኑ የተነገረለትን የአልሸባብ እንቅስቃሴ ለመግታት የቱርክ መከላከያ ሰራዊትን የያዙ ሁለት የጦር አውሮፕላኖች ሶማሊያ ሞቃዲሾ መድረሳቸውን የመገናኛ ዘዴዎች እየዘገቡ ነው።
እንደ ዜናው ከሆነ 500 የቱርክ ኮማንዶ ኃይሎች ሞቃዲሾ ደሰዋል። ባለፉት ቀናት ውስጥ አልሸባብ በሶማሊያ ጦር ላይ ከፍተኛ የማጥቃት ዘመቻ መጀመሩን ተከትሎ የሶማሊያ ጦር የመፈራረሰ አደጋ ውስጥ መግባቱን የተመለከተችው ቱርክ በሁለት አንቶኖቭ አውሮፕላን 500 ሰራዊት ከበቂ መሳሪያ ጋር ወደ ሞቃዲሾ መላኳ ታውቋል።
በፑንትላንድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የአልሸባብ ታጣቂዎች ሳይሆኑ አይቀሩም በተባሉ ታጣቂዎች ተገደሉ
በሱማሊያዋ ፑንትላንድ ራስ ገዝ የኢትዮጵያ ቆንስላ ውስጥ ተመድበው ይሠሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ፋራህ አይዲድ ጃማ ከሱማሌላንድ ራስ ገዝ በቅርቡ በተነጠለችው “ኤስ ኤስ ካቱሜ” ግዛት ላስ አኖድ ከተማ ውስጥ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን የሱማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
የግዛቲቷ ባለሥልጣናት፣ ግድያውን የፈጸሙት ለጊዜው ታጣቂዎች የአልሸባብ አባላት ሳይኾኑ አይቀርም የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ዘገባዎቹ መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል። በዲፕሎማቱ ሕልፈት ዙሪያ የግዛቲቱ ባለሥልጣናት ምርመራ እያደረጉ እንደኾነ ተገልጧል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በዲፕሎማቱ ሕልፈት ዙሪያ በይፋ ያለው ነገር የለም።
የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት፣ ከሶማሌላንድ መገንጠል እንፈልጋለን ያሉ የጎሳ ሚሊሻዎች ከደም አፋሳሽ ውጊያ በኋላ የመሠረቷትን “ኤስ ኤስ ካቱሜ” ግዛት፣ ባለፈው ሳምንት የፌደሬሽኑ አባል ግዛት አድርጎ መቀበሉን ማወጁ ይታወሳል።
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter