አዲስ የተሾሙት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ ” የወጣቱ የለውጥ ጥያቄ የሚመልስ አዲስ ካቢኔ አላዋቀሩም ” በሚል ነቄፌታ እየቀረበባቸው ነው። ነቀፌታው የተሰማው ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ እንደ አዲስ የተዋቀረው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ስራ እንደጀመረ ማስታወቃቸውን ተከትሎ ነው። እሳቸው ” ጥሩውን ለራስ መጥፎውን ለሌላ መስጠት አይቻልም ድሉም ውድቀቱም የጋራ ነው ከእልህና ህዝብንና አገር ከሚጎዳ ፓለቲካዊ አካሄድ እንውጣ ” ማለታቸው ተሰምቷል።
“በእኛ በኩልም ምንም እንኳን ከፕሬዝዳንት ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደ ጋር ለማድረግ ያቀድነው ውይይት ባይሳካም የተሻለ አቃፊ ካቢኔ እንዲዋቀር ከሚመለካታቸው አካላት ጋር ስንወያይ ቆይተናል። በተጨማሪም ለሁሉም ተደራዳሪዎች እና አደራዳሪዎች ግልጽ የሆነ አቤቱታ አቅርበናል” ሲል አዲሱ ካቢኔ አወቃቀሩ ስምምነትን የሳተ አነደሆነ የእነ አቶ ጌታቸው ትህነግ አስቀድሞ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ አይዘነጋም።
መግለጫው አያይዞም “ማዕከላዊ ኮሚቴያችን ተቋቁሟል የሚባለው የብዙሃን ፍላጎትና ተሳትፎ ያገለለ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ የብዙሃን አመለካከትና ወገኖች ፍላጎት ባካተተ መልኩ ዳግም በአስቸኳይ እንዲዋቀር ጥሪ እናቀርባለን” ሲል ድምጹን ለዘረዘራቸው የህብረተሰብ ክፍሎችና የሚመለከታቸው አሰምቷል።
በአቶ ጌታቸው ረዳ ሲመራ የነበረውን የካቢኔ ቁጥር ከ27 ወደ 21 ፤ ሁለት ምክትል ፕሬዜዳንት የነበረውን ወደ አንድ እንዲወርድ ያደረጉት ፕሬዜዳንቱ እስካሁን ምክትላቸው ማን እንደሆነ በይፋ አላስታወቁም። እሳቸው ይፋ ባያደርጉትም የትህነት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ኣማኒኤል አሰፋ መሾማቸው በስፋት እየተገለጸ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከዚሁ ከእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የትህነግ ሃይል ሰፊ ቁጥር ያለው የካቢኔ አባል ያካተቱ መሆኑ ተሰምቷል።
የአዲሱን ካቢኔ አወቃቀር ” ይህ ወላጆቻችን “በድህነቷ ላይ ጥጃዋ ትሞታለች” እንደሚሉት ተረት ሆኖ አሁንም ትግራይ ከገባችበት ችግር እንዳትወጣ ጄኔራል ታደሰ ከቡድኑ (የደብረጽዮን) ጋር በመቆም የኮርና ከኮር በላይ ህገወጥ ውሳኔ የሚተገብር ሁሉንም ያላተፈ ካቢኔ አዋቅሯል:: ይህ ህገወጥ ውሳኔ በመገናኛ ብዙሃን በተደጋጋሚ ሲገለጽ የነበረው አሸናፊና ተሸናፊ የሌለባት የሁሉም የሆነች ትግራይን ሳይሆን ለሁለት አመታት በድብቅ ሲሰራ የቆየው ሴራ የሚያጋልጥ ሆኖ አግኝተነዋል” ሲል የእነ አቶ ጌታቸው ትህንግ መግለጫ አታጥሎታል።
ፕሬዜዳንት ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ አዲሱ ካቢኔ ስራ መጀመሩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ” ትግራይ በአሸናፊና ተሸናፊ የፓለቲካ ቅኝት ከገባችበት አዘቅት መውጣት አትችልም ” ብለዋል። ” ባለፉት ሁለት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ዓመታት በርካታ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ተፈፅመዋል ” ሲሉ ገልጸዋል።
” ጥሩውን ለራስ መጥፎውን ለሌላ መስጠት አይቻልም ድሉም ውድቀቱም የጋራ ነው ከእልህና ህዝብንና አገር ከሚጎዳ ፓለቲካዊ አካሄድ እንውጣ ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
” የቀድሞ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የጊዚያዊ አስተዳደር አመራሮች የሚመሰገኑበት መድረክ ይዘጋጃል ” ያሉት ፕሬዜዳንቱ ጥሪውን ተቀብለው እንዲገኙ ከወዲሁ በይፋ የግብዣ ጥሪ አቅርበዋል። የቀድሞ ፕሬዚዳንትና አመራሮች ይመሰገኑበታል የተባለው የምስጋና ስነስርዓት መቼ እና የት እንደሚዘጋጅ የተባለ ነገር የለም።
በሌላ በኩል ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ተፈናቃዮች የሚገኙበት ስቃይና ሰቆቃ ባወሳ ንግግራቸው ” በዚሁ ዓመት ወደ ቄያቸው የመመለስ ስራ ይሰራል ፤ በማቆያ ጣብያ የሚቆዩት ደግሞ አኗኗራቸው እንዲሻሻል ትኩረት ይደረጋል ” ብለዋል።
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter