በቀደሙት ጦርነቶች በግልጽ እንደታየው ትህነግ ቀለብ፣ ነዳጅና መድሃኒት ብሎ ድምጽ ካሰማና ደጋፊዎቹ ሚዲያዎች ይህንኑ ጩኸት ካስተጋቡ ነገሩ ሌላ ነው። ቀደም ባሉት ጦርነቶች ኢትዮጵያ ለሚወጋት ቡድን መጉጓጓዛ፣ መለዋወጫ፣ ቀለብ፣ መድሃኒት፣ ነዳጅና አስፈላጊ ሎጅስቲክ፣ ስልክ፣ መብራትና ኤትዎእክ እንድታሟላ ጫና የተደረገባት የዓለም ብቸኛዋ አገር ተደረጋ እንደተወሰደች የሚታወስ ነው።
“የሚወጋሽን ወይም ሊወጋሽ የተዘጋጀውን ቡድን ፍላጎት አሟይ” በሚል የጸጥታው ምክር ቤት፣ ተመድ፣ አሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረትና የዓለም ጫና ፈጣሪ መንግስታት፣ የውጭ አገርና ታዋቂ ሚዲያዎች፣ የመብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች፣ አሁን የተዘጋውን ቪኦኤን ጨምሮ በውጭ መንግስታት በጀት የተቋቋሙ በአገር ውስጥ ቋንቋዎች በራስዋ ዜጎች የሚሰራጩ ሚዲያዎች ሲፈጽሙ የነበረው ተግባር ለታሪክ የሚቀመጥ እንደሆነ በወቅቱ መገለጹ የሚታወስ ነው።
ትህነግ ለሁለት መስንጠቁን ተክትሎ አንደኛው ቡድን ከሻዕቢያ ጋር ገጥሞ የጦርነት ዝግጅት ላይ እንዳለ በርካታ መረጃዎች እየወጡ ባለበት በአሁኑ ወቅት እንደተለመደው ትህነግ “ነዳጅ በመቀሌ የለም። የትግራይ ሕዝብ ነዳጅ ተከለከለ” በሚል ባለፈው ሳምንት ድምጹን አሰምቶ ነበር። ታሪክ ራሱን ይደግማል እንደሚባለው ኢትዮጵያ ለሚወጋት ድጋሚ ሎጅስቲክ እንድታሟላ ትህነኛ ደጋፊዎቹ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል። ይሁን እንጂ ከላይ የተዘርዘሩት አጋሮቻቸውና አለቆቻቸው ያሉት ነገር የለም።
አሁን እየወጣ ባለ መረጃ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በትግራይ መድሃኒት እጥረት ማጋጠሙንና ህዝብ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ መኖሩን ጠቅሶ ለዓለም “የድረሱልን” ጥሪ ለማስማት በዝግጅት ላይ ነው። ይህ ጥሪ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ነው መረጃው ያላቸው እያስታወቁ ያሉት።
ትህነግ ይህን ዕቅድ የያዘው በትግራይ ከተለያዩ የጤና ተቋማት ያሉትን መድሃኒቶች ለጦርነት ሎጅስቲክ ወደ መረጠው ቦታ እያጋጋዘ መሆኑን ተከትሎ ነው። እማኞች እንደሚሉት
የትግራይ ንግድና ኤክስፖርት ኤጀንሲ ሃላፊ አቶ ገ/መስቀል ታረቀ በትግራይ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ገልጸው ደብዳቤ ለፌደራል መንግስት መጻፋቸውን ተከትሎ የትህነግ ደጋፊ ሚዲያዎች ” የአብይ መንግስት ትግራይን እንደ ለመደው በእጥረት ማሰቃየት ጀመረ። ይህ ትግራይን ሲጅ የማድረግ ዕቅዱ ጅማሬ ነው” በሚል ዜናውን ተቀባበሉ።
“ዛሬም ነዳጅ ተከልክለናል” በማለት ሚዲያዎቹ በቅብብል መንግስትን ፣ በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ሲያውግዙ በመካከሉ የትግራይ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ቢሮ ሃላፊ አቶ ጠዓመ አረዶም “ነዳጁን በሙሉ ወስደው ጨርሰውታል። እሱም አልበቃ ብሏቸው ከራያ አላማጣና ከአፋር እያስመጡ ነው” ሲሉ ኃላፊነታቸውን መሰረት አድርገው ለትግራይ ሕዝብ እውነታውን አስታወቁ፤ ይህ ሲሆን ኃላፊውን በመጠቅሰ አስቀድመው “የትግራይ ሕዝብ በነዳጅ እጥረት እንዲሰቃይ ተፈረደበት” ያሉት ሚዲያዎች ማስተካከያ አላደረጉም።
አቶ ጠዓመ አረዶም ” ከጂቡቲ የሚመጣውን ነዳጅ በሙሉ በቀጥታ አዲ ፀፀር (ሸራሮ አካባቢ ) ፣ አዲክልተ፣ ገዛ ተጋሩ ፣ ዛና ፣ ህርሚ ፣ ሰመማ ፣ አዲደቂ በቅሊ ወዘተ በሚባሉ አካባቢዎች ውስጥ አከማችተውታል” በማለት ስም ዘርዝረው ያላቸውን መረጃ ይፋ አደረጉ።
ነድጃ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል የደበቁትን ከባባድ መሳሪያዎቻቸውንም እያወጡ ከቦታ ወደ ቦታ እያንቀሳቀሱ መሆኑንንም አቶ ጠዓመ አረዶም ምስክርነታቸውን በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ ምልልስ አመልክተዋል።
የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ማስረከብ ሲገባቸው ደብቀው ያቆይዋቸውን ሮኬቶች፣ መድፎችና ታንኮች ከቀበሩበት በማውጣት ወደ አዲ ደቀበቅሊ እና የጭላ እንዳጋዙ አቶ ጠዓመ አረዶም ከጦርነት ስጋት ጋር አያይዘው ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው ሰሞኑን “ስልጣን ወይም ሞት ብሎ የተነሳው ኋላቀር ቡድን ወደሌላ ዙር የጥፋት አዙሪት ሊያስገቡን ቋምጠዋል” ሲሉ ባሰራጩት ጹፍ፣ የትህነግ አፈንጋጩ ቡድን የጦርነት ዝግት ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል። “[ትህነግ] ምዕራብ ትግራይ [ወልቃይት] ሲባል ለሰሊጥ መሬቱ እንጂ ስለ ተፈናቃዮቹ ተጨንቆ አያውቅም” ሲሉም አክለዋል።
“ይሄ ሁሉ ጥድፊያ ለጦርነት እየተዘጋጁ እንደሆነ ግልፅ ነው። እነዚህ ሰዎች ጦርነት እየጠመቁ ያሉት ለትግራይ ደህንነት አስበው አይደለም ለስልጣናቸው ሲሉ ነው” ሲሉ አቶ ጠዐመ በይፋ “ጦርነትን አንፈልግም” ላለው ለትግራይ ህዝብ መልዕክት አስተላለፈዋል።
ከነዳጁ ቀጥሎ ትግራይ ውስጥ በየጤና ተቋማቱ ያለውን መድሃኒት በማጓጓዝ ወደ ተመረጡ የኮማንድ /ማዘዣ ማዕከል ማከማቸት ላይ የተጠመደው ትህነግ፣ ማጓጓዙን ሲጨርስ “የትግራይ ሕዝብ በመድሃኒት እጥረት እንዲያልቅ እየተደረገ ነው” በሚል ድምጽ ለማሰማት ዝግጅት ላይ መሆኑን እንቅስቃሴውን የሚከታተሉ አስቀድመው እያስጠነቀቁ ነው። እነዚህ ወገኖች እንዳሉት ከሆነ መድሃኒት ለጊዜው እንዲከማች እየተደረገ ያለው አዲፀፀር ባለው የማዘዣ ማዕከል ነው፡፡
ይህ ዜና ከመነገሩ አንድ ቀን በፊት፣ በኩሃ ሁለት ሆስፒታሎች ውስጥ የነበረን መድሃኒት፣ እንዲሁም ለጊዜው በመቀሌ መጋዘን ውስጥ ተቀምጦ ወደ ደቡብ ትግራይ ሆስፒታሎችና ጤና ኬላዎች ሊሰራጭ የነበረ መድሃኒት ጠራርገው በሌሊት ወደ አዲ ፀፀር ማጓጓዛቸውን ምስክሮቹ አመልክተዋል። መድሃኒቱ ሊጓጓዝበት በነበረው አካባቢ የሚኖሩ ዜጎች ሆነ ተብል ለችግር እንዲጋለጡ ተደርጓል።
እንደ ምስክሮቹ ገለጻ ትህነግ በቀጣይ ቀናት ውስጥ ” በትግራይ የመድሃኒት አጥረት አጋጥሟል። የትግራይ ሕዝብ አደጋ ውስጥ ነው” በሚል ባስቸኳይ መድሃኒት እንዲላክ ጥያቄ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል። ይህ መረጃ ያለው መንግስት ለክልሉ ጤና ቢሮ የተላከውን መድሃኒት ዘርዝሮ የስርጭት ሪፖርት ዝርዝር ለመጠየቅ መዘጋጀቱ ተሰምቷል። መረጃውን ለሚመከታቸው አገራት ኤምባሲዎች ማስታውቁም ታውቋል።
አሁን መሳሪያ፣ ነዳጅና መድሃኒት እየተከማቸባት ያለችው አዲ ፀፀር አዳዲስ የጦር ወታደራዊ ካምፖች ተቋቁመውባታል። አዲ ጸጸር ለምን የወታደራዊ ማዘዣ ሆና እንደተመረተችና አስር የሚጠጉ አዳዲስ ካምፖች ሊመሰረቱባት እንድተመረጠች ምስክሮቹ አላብራሩም። ነገር ግን ሻዕቢያ በተጠቀቸው ስራ ካምፕ መመስረቱን አልሸሸጉም።
ሻዕቢያ ጦርነቱ የማይቀር ከሆነ በትግራይ ምድር እንዲሆን ቀደ ሲል አስመራ በተደረገ ስብሰባ በተወሰነው መሰረት አስቀድሞ በወረራ የይዛቸውን ጨምሮ ሸራሮ ፣ አዲሃገራይ ፣ አዲ አውአላ ፣ ራማና አዲስ ጸጸር በመሳሰሉት ስፍራዎች ነጻ ካምፕ ማዘጋጀቱን ወታደራዊ ምንጮች ሲገልጹ ሰንብተዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ከትግራይ ከወጡና የጊዜያዊ አስተዳደሩ ኃላፊዎች እንዲባረሩ ከተደረገ በሁዋላ ሻዕቢያ በገሃድ የጦር መኮንኖችና የስለላ ሰራተኞቹን ወደ መቀለ ማስገባቱን ነዋሪዎችን ጠሰው መገናኛ ዘዴዎች ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
ቀደም ሲል የትህነግ ታጣቂ ኃይል አዛዦች የድንበር መንገዶችን ከመጠገን በዘለለ በሽሬ አቅጣጫ ወደ ኤርትራ የሚዘልቅ አዲስ መንገድ መጥረጋቸው መዘገቡ የሚታወስ ነው።
“ይህ እንቅስቃሴ ሻዕቢያ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲፈርስ መግፋቱን ወይም ጫና ማድረጉን ያረጋግጣል” በማለት አስተየት የሰጡ፣ በቅድሚያ አዲግራትን ከጊዜያዊ አስተዳደሩ መቀማት የተፈለገው ከተማዋ ለሻዕቢያ ቁልፍ በመሆኗ ነው፡፡
የሸዕቢያ ወገን የሆኑ በስም ያልጠቀሷቸውን ወታደራዊ ባለሙያዎች ጠቅሰው እንዳሉት አዲግራት ላይ ጸረ ሚሳይልና ድሮን በመትከል አስመራን ለ150 ኪ.ሜ ርቀት አዲግራት ላይ ሆኖ ለመከላከል ነው፤ የ የትህነግ ሰራዊት አዛዦች በተሰማሙት መሰረት ጦርነት ከተነሳ አዲግራት የጦርነት ስበት ማኧከል እንድትሆን ተፈርዶባታል። ይህ “ጦርነት በቃን” የሚሉትን የትግራይ ተወላጆችና ኢትዮጵያንን አሳዝኗል።
ይህን ሁሉ ዕቅድ እዛው ትግራይ ውስጥ ሆነው ሲከታተሉ የነበሩት ባይተዋሩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው “ከግብፅ ጋር ንግግር ጀምረናል ብሎ የነገረኝ ወታደራዊ አዛዥ አለ” አለ ሲሉ ግብጽ ከጀርባ እንዳለች አመልክተዋል።
ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት የቀድሞ ሚቴክ ስራ አስኪያጅ የነበሩትን በቀርቡ የተፈቱት ጄኔራል ክንፈ ዳኘው “ህዝባችንን ወደቦታው ከመለስን በኋላ እንገነጠላለን” ሲሉ በአደባባይ ሲናገሩ በቪዲዮ ተደምጠዋል።
በትግርኛ ቋንቋ “በመጀመሪያ ህዝቡን ወደ ምዕራብ ትግራይ ‘ወልቃይት ጠገዴ’ እንመልሳለን” ካሉ በሁዋላ “… ሰማዕቶቻችን የተሰዉበትን ዓላማ እውን እናደርጋለን። እሱም ነፃ ሃገር መመስረት ነው። የማትደፈርና የማትለምን ነፃ ትግራይን እንገነባለን። የሸዋን ትራፊ የማትበላ ነፃ ትግራይን እንገነባለን ።እንደ ቀድሞው ኢትዮጵያንና ሸዋን ተሸክማ ከሸዋ የማትለምንን ነፃ ትግራይ እናንፃለን” የሚል ዲስኩር አሰምተዋል። የቪዲዮው ትርጉም የተወሰደው ከእአስፋው አብርሃ ነው።
ይህ የክንፈ ዳኘው ንግግር ሻዕቢያና ወያኔ በወልቃይት ጉዳይ ተስማምተውበታል የተባለውን ጉዳይ ግልጥ አድርጎ የሚያሳይ እንደሆነ በመግለጽ ነው አማራ ሆነው ከትህነኛ ሻዕቢያ ጋር ኝባር ለገጠሙት “ዓላማችሁ ምንድን ነው? ወልቃይትን መሸጥ ወይስ ወልቃይቴ አማራ አይደለም የሚል ውል ቋጠራችሁ” ሲሉ ጥያቄ የሚያነሱት።