የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ያካሄደውን የ50 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ውጤት ይፋ ማድረጉ የመለከተ።
ባንኩ ይፋ ባደረገው መረጃ የጨረታው አሸናፊዎች የገዙት የውጭ ምንዛሬ በአማካኝ በአንድ የአሜሪካን ዶላር 131.7095 ብር መሆኑ ተገልጿል። በጨረታው በአጠቃላይ አስራ ሁለት ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ማግኘታቸውም ተገልጿል።
የሚቀጥለው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሁለት ሳምንት ውስጥ የሚካሄድ መሆኑም ነው የተጠቆመው። የውጭ ምንዛሪ ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት ከጨረታው ዕለት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ይፋ እንደሚደረግም ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንት የሚያወጣው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና ሪፎርሙ ከተጀመረ ወዲህ መሻሻል እያሳየ የመጣውን የውጭ ክፍያ ሚዛን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚረዳ ታምኖበታል።