የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን መነሻ ያደረገ የንግድ ስርአት እንዳይኖር ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ነጋዴዎች ላይ በተወሰደ እርምጃ ከ42 ቢሊዮን በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ መደረጉ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በተያዘው የበጀት አመት በዘጠኝ ወራት አፈፃፀም በስፋት ከሰራኋቸው ስራዎች አንዱ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን መቆጣጠር ነው ብሏል ።
በዚህም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን መነሻ ያደረገ የንግድ ስርዓት እንዳይኖር ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 9 ሺሕ 134 የንግድ ተቋማት ላይ በተደረገ ቁጥጥርና ነጋዴዎች ላይ በተወሰደ እርምጃ ከ42 ቢሊየን በላይ ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ መደረጉ ተገልጿል ።
ቢሮው ከተለያዩ የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ህገወጥ ነጋዴዎችንና ብልሹ አሰራር ብሎም የጎዳና ላይ ንግዶችን መቆጣጠሩን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ናቸው።
በተለይም አላግባብ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ብሎም ሃሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን በመጠቀም ህብረተሰቡን በማጭበርበር ላይ የተሰማሩ እንዲሁም ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎች ላይ የቁጥጥርና እርምጃ የመዉሰድ ስራዎች በስፋት መሰራታቸውን አመላክተዋል። የኮሪደር ልማቱ ላይ ያሉ የህግ ጥሰቶችንና ህጋዊ ያልሆኑ ነጋዴዎችንም በመቆጣጠር ወንጀልና ደንብ ጥሰትን መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል ።
ቢሮው በኑሮ ማረጋጋትና በህገ-ወጥ ንግድ ዙሪያ ክትትልና ቁጥጥር ላይ ትኩረት ሰጥቷል ያሉት ሃላፊዋ፤ ወደ ፊትም ህግና ስርዓት ከማስከበርና የነዋሪውን ሰላምና ደህንነት ከዚህ በተሻለ ለማስጠበቅ በተሻለ የቴክኖሎጂ አሰራር ለመስራት መታቀዱን መናኸሪያ ኤፍ ኤ፣ አመልክቷል።
ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች መጫን ብቻ
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter