በቀጥታ ከፋኖ ጋር ይገናኛል ወይም አይገናኝም ለሚለው ሰፊ ማብራሪያ አልቀረበም። አቶ ፋሲል የኔዓለም ግን ላለፉት ሃያ ዓመታት በጋዛ ሲንቀሳቀስ የኖረው ሃማስ ላይ የተነሳውን የህዝብ የ”ጥፉልን” ተቃውሞ አንስቶ አጣቅሷል ። አቶ ፋሲል ይህን ያለው አቶ አንዳርጋቸው “ትግሉም ታጋዩም ይሞታሉ” በሚል የደረሱበትን ድምዳሜ ሲያስረዱት፣ ላነሱት የህዝብ ምሬትና መሰላቸት ማስደገፊያ አሳብ ሲሰጥ ነው።
ሰሞኑን የጋዛ ነዋሪዎች በሃማስ ላይ ያነሱት ተቃውሞ መሰላቸት የወለደው ነው። በጋዝ ለሚኖሩ ፍልስጤማውያን ነጻነት ትግሉን እንዲመራ መመስረቱ የሚነገርለት ሃማስ ” ዞር በሉልን” በሚል ተቃውሞ የተነሳበት ህዝብ በመሰላቸቱ ነው። ወደ ፍርስራሽ በተቀየረችው ጋዛ ሕዝብ በገሃድ ሃማስን “ውጡልን” እያለ ነው።
“አሁን 30 ዓመቴ ነው። ሐማስ ይህንን አካባቢ ሲቆጣጠር የ11 ዓመት ታዳጊ ነበርኩ። በሕይወቴ ምን ሠራሁ? ሕይወቴ በጦርነት እና በተባባሰ ግጭት ውስጥ ነው የባከነው” ማለቱን ቢቢሲ ይጠቅሳል። አል ናቶር ይህን ሲል በህይወቱ ቆርጦ ነው። በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ በዋሺንግተን ፖስት ላይ ቁጣ የተቀላቀለበት ጽሑፉን ታትሞለታል። “ሐማስን መደገፍ ማለት የፍልስጤማውያን ሞትን መደገፍ ማለት ነው። የፍልስጤማውያንን ነጻነት መደገፍ ማለት አይደለም።” ሲል ሕዝብ የደረሰበትን መከራ አጉልቶ አሳይቷል። ዓለም መታለሉንም ይፋ አድርጓል። በዛውም ተሰናብቷል።

የአቶ አንዳርጋቸው የሰሞኑ አነጋጋሪ ቃለ መጠይቅ ሃማስን የጎተተውም በዚሁ መነሻ ነው። ከተለመደው ዘዬ ውጪ “ትግልም ታጋይም ይሞታል” ሲሉ የተደመጡት አቶ አንዳርጋቸው፣ ሕዝብ ሮሮ ውስጥ መግባቱን፣ መሰላቸቱን በግልጽ ተናግረዋል። በራሳቸው አረዳድ፣ የፋኖ ትግል መሪና ስፖንሰር አድራጊዎች ጋር የሚገናኙ ዋና ሰው በመሆናቸው ምክንያት ድምዳሜያቸው በቀላሉ የሚታይ አልሆነም። ለዚህ ድምዳሚያቸው በርካታ ምክንያቶች ቢዘረዝሩም በዋናነት ያነሱት ትግሉ እንዲጠናቀቅ የማይፍልጉና የትግሉን መነሻና መዳረሻ የማያውቁ አመራሮች ስላሉ ነው።
ከመሳይ መኮንን ጋር ኤርትራ ከአቶ ኢሳያስ አፉወርቂ ጋር በመገናኘት የሚታወቀው ፋሲል የኔዓለም የጋበዛቸው አቶ አንዳርጋቸው “ታጋይ ይሞታል፤ ትግሉ ይቀጥላል” የሚለውን የተለመደ ንግግር ገልብጠው ” ትግልም ታጋይም ይሞታል” ያሉት ስለፋኖ አሁናዊ ቁመና ሲያብራሩ ነው።
አቶ አንዳርጋቸው “የትግሉን መነሻና መዳረሻ የማያውቁ” ሲሉ የዘለፏቸው የፋኖ አመራሮችን አንድ አመራር መፍጠር ያልቻሉ፣ ወደ አንድ የፖለቲካ ማዕከል መሰባሰብ ያቃታቸው፣ ችግርን መርምረው ስትራቴጂ መንደፍ የማይችሉ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የጎጃም ፋኖ ምክትል መሪ የሆነው አስረስ ማረ ” ወደ አንድ የፖለቲካ ማዕከል እየመጣን ነው” በማለት በቅርቡ የአንድነት ዜና እንደሚሰማ በተናገረ ቀናት ውስጥ አቶ አንዳርጋቸው በዚህ ደረጃ የፋኖ አማራሮችን መውቀሳቸው አስገርሟል። አንዳንዶች ” የፋኖ ትግል አንድ ሊሆን አይችልም” ሲሉ እስከንድር ነጋን በመጥቀስ አቶ አንዳርጋቸውን “ይህን ለመረዳት ዘገዩ” ሲሉ እንደ ሻለቃ ዳዊት ለመንሸራተት እያኮበኮቡ መሆኑን ገልጸዋል።
“ግዛታችን እስከ ወለጋ ነው” በሚል መፈክር ጀመረው፣ በሚልዮን ዶላር ስብሰበው፣ በመጨረሻ ” ራሴን ካገለልኩ ቆይቻለሁ” በማለት በድንግዝግዝ ካቀጣጠሉት የትርምስ ባቡር የወረዱት ሻለቃ ዳዊት ” ትግል ሳይሆን ጥቅም ማሳደድ ነው የተያዘው” ሲሉ የተናገሩትን ” ከደሙ ንጹህ ነኝ” መግለጫ አቶ አንዳርጋቸውም መድገማቸው መረጃዎቹን ለገጣጠሙ ወገኖች ትርጉም ከፍ ያለ ሆኗል።
በተጠለፈው የስልክ ንግግሩ ” ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል የሚል አጀንዳ እንደሌለን ንገራቸው” የሚል የስራ መመሪያ ወደ ኤርትራ እየላከው ላለው የአፋህድ የሎጂስቲክ ኃላፊ ሲሰጥ የተሰማው እስክንድር ነጋ ” እነሱ ችግር ላይ ናቸው። እኛ ከሁሉም የተሻልንና ድርጅት የመሰረትን ነን። ይህን ንገራቸው።” ማለቱ አቶ አንዳርጋቸው እንዳሉት የፋኖ ትግል ወደ አንድ አመራር ሊመታ እንደማይች ማሳያ በመሆኑ “አንዲ ተስፋ ቆርጠዋል” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ።
ዋናው ዓላማው አስመራ ቢሮ መክፈት እንደሆነ ደጋግሞ ያሳሰበው እስክንድ ነጋ “ከፈለጉ ድርጅት መስርተው ይምጡ” ሲል አንድ የመሆኑ ጉዳይ ሊሳካ የማይችል መሆኑን አመላክቶ ነበር። በዚሁ የተጠለፈ የስልክ ውይይት ወደ አስመራ እንዲሄድ መመሪያ የተሰጠውን ሰው መንግስት በቁጥጥር ስር እንዳዋለው መሰማቱ አይዘነጋም። መንግስት ግን በይፋ የተናገረው ነገር የለም።
ይህ ከተሰማ በሁዋላ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከአስመራ ቆይታቸው ሲመለሱ በሰጡት ማብራሪያ ሕዝብ እንደልቡ መንቀሳቀስ አለማቻሉ፣ ህክምና እንዳያገኝ መደረጉ፣ ማዳበሪያ እንዳይደርሰው መሆኑ፣ ትምህርት እንዲዘጋና ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው መገለላቸው፣ ምርት መቀነሱ፣ረሃብ ወዘተ የመሳሰሉት ችግሮች በአማራ ክልል መጋረጣቸውን ጠቁመዋል። አክለውም “በዚህ ሳቢያ ሕዝብ የትግሉ መጨረሻ ምንድን ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳቱንና ሮሮ ውስጥ መግባቱን ገልጸዋል። ቃል በቃል “መሰላቸት ተፈጥሯል” ብለዋል።
“አማራ የሚባል ብሄር የለም” በሚለው አቋማቸው የሚታወቁት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በኢትዮጵያ ለውጡ ዕውን ሲሆን ከሞት ፍርድ ነጻ መውጣታቸው ይታወሳል። በውል ያኮረፉበትን ምክንያት በራሳቸው አንደበት ሳይገልጹ “የለም” ላሉት አማራ መሪ ሆነው ብቅ ካሉ በሁዋላ በስፋት የሚቀርቡት ራሱን “አርበኛ በሉኝ” ባለው መሳይ መኮንን አንከር ሚዲያ ነበር።
አርበኛ መሳይ፣ አቶ ፋሲልና አቶ አንዳርጋቸው በኤርትራው መስመር አብረው የሚሰሩ እንደሆነ በራሳቸው አንደበት፣ በምስል አስደግፈው ራሳቸው የገለጹት እንደሆነ አይዘነጋም።

ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ማግስት ጀምሮ ከሻዕቢያ እኩል ወደ ተቃውሞ የዞሩት የሚዲያው ሰዎችና “ለኢትዮጵያና ኤርትራ ወዳጅነት አማላጅ ነበርኩ” ሲሉ ከአቶ ኢሳያስ ጋር ጥብቅ ትሥሥር እንዳላቸው ያስታወቁት አቶ አንዳርጋቸው፣ የፋኖ ትግል መሪ ሆነው አደረጃጀት፣ ስትራቴጂ፣ ስልትና መዋቅር ሲያዘጋጁ ነበር።
በተለያዩ የአንክር ሚዲያ ቆይታቸው፣ ” እባካችሁን ይህን ጽሁፍ አሰራጩልኝ” እያሉ በፌስ ቡክ ገጻቸው ጭምር የትግሉን አቅጣጫ ሲያሳዩ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው፣ ከፋሲል ጋር ባደረጉት ቆይታ “ትግሉ እንዲቋጭ የማይፍለጉ፣ ትግሉ ከተቋጨ ነህግ የሚጠየቁ አሉ” ሲሉ ሌብነት ህዝብረት እንዳይፈጠር ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል።
ትግሉን ንግድ ያደረጉና ከፍተኛ ጥቅም ያገኙበት መኖራቸውን አቶ አንዳርጋቸው አመልክተዋል። ትግሉ ንግድ የሆነላቸው አካላት መኖራቸውን መጥቀሳቸው ቀደም ሲል በአፍሪካ በተለይም ዩጋንዳና ደቡብ ሱዳን፣ በአውሮፓና አሜሪካ የሽርክና ንግድ ከፍተው ሃብታም የሆኑ እንዳሉ ሲገለጽ የነበረውን መረጃ አጉልቶታል።
በትግሉ ስም የተሰበሰብ ሃብት እንዳልደረሳቸው፣ የሰበሰቡት አካላት እንደዘረፉት፣ ተመርጦ በመጠኑ እንደሚሰጥ በቪዲዮ፣ በጽሁፍና በስልክ መረጃዎች የሚወጡበት የንግድ ጉዳይ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ በርካቶችን አሳዝኗል። በቁጣም አስተያየት ሲሰጡ የነበሩና በዚሁ የገነዘብ ጉዳይ ጎራ ለይተው በጫካ ውስጥ የተጋደሉ መኖራቸውም አይዘነጋም። ኃይል አሰባስቦ አንዱ ከሌላው በልጦ ለመገኘት አሁን ድረስ ፍልሚያ እየተደርገ መሆኑም የአደባባይ ሚስጢር ነው።
አቶ አንዳርጋቸው የአንድነትን መንገድ ከዘጉት መክንያቶች መካከል ሌላው ያነሱት፣ በተማሩና ባልተማሩ ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ነው። በፋኖ የተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ ፊደል ያልቆተሩ መኖራቸውን ያነሱት አንዳርጋቸው “በትግሉ ውስጥ በተማሩና ባልተማሩ መካከል ያለው መሳሳብ እንቅፋት ነው” ሲሉ ምንም ሳያውቁ አዛዥና መሪ የሆኑ መኖራቸውን አውግዘዋል።
“ሻዕቢያ፣ ትህነግ፣ ፋኖና ሸኔ ግንባር ገጥመው በየአቅጣጫው ወደ ማዕከል ሊተሙ ነው” የሚለው መረጃ በስፋት እየጎነ ባለበት፣ ትህነግ በገሃድ እውቅና ካልተሰጠው ትርምስ እንደሚፈጠር በሚያስጠነቅቅበት፣ ደጋፊ ሚዲያዎች ይህንኑ በሚያስተናግዱበት ወቅት አቶ አንዳርጋቸው፣ የፋኖ አመራሮች ተሰባስበው የሚቆሙበት የጋራ አመራር፣ ሰራዊት፣ሕዝቡን በፖለቲካ ቀርጸው የሚያደራጁበት ስትራቴጂ እንደሌላቸው ጠሰው “ታጋዩም ትግሉም ይሞታል” ማለታቸው እጅ በአፍ አስጭኗል።
የራሳቸውን ዝናና ክብር አግዝፈው የሚያዩ መኖራቸውን አንስተው የተቹት አቶ አንዳርጋቸው፣ “የብልጽግና እጅ የገባባቸው አሉ” ሲሉ የፋኖን ወቅታዊ ቁመና ለፋሲል አጫውተውታል። የኢትዮጵያን ውድ ጄነራሎች ከሻዕቢያ ጋር በመሻረክ ሱዳን ሆነው በማስፈጀታቸው የሚወነጀሉት ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ፣ አርበኛ መሳይ መኮንን ሚዲያ ላይ ተመሳሳይ ይዘት ያለው መረጃ ከሰጡ በሁውላ ትግሉን መሰናበታቸውን የአቶ አንዳርጋቸው ንግግር አስታውሷል።
አቶ አንዳርጋቸው አስመራና ዜግነት የሰጠቻቸው እንግሊዝ እየተመላለሱ ከሻዕቢያ የሚሰጣቸውን መመሪያ በማስፈጸም በቅርብ የሚያውቋቸው ይከሷቸዋል። አዲስ አበባ በነበሩበት የኢሳት ቢሮ ውስጥም ከአንድ በሃያዎቹ የዕድሜ ክልል የምትገኝ አዲስ ጋዜጠኛ ጋር ተዋደው ልጅ በመውለዳቸው በቢሮ ውስጥ ተቀባይነት እንዳጡ ሰራተኞች ይመሰክሩባቸዋል።
” ባለቤቲን ፍቱልኝ” በሚል በለኦንደን ጎዳናዎች፣ የመንግስትና የሚዲያ ደጃፎች ሲነከራተቱ የነበሩት ባለቤታቸው፣ “አባቴን ለቀቁት” ስትል የነበችው ልጃቸውና ቤተሰቦቻቸው፣ እንዲሁም ወዳጆቻቸው በአቶ አንዳርጋቸው የስተርጅና ምግባር ማዘናቸው በወቅቱ ተሰምቷል። “አንድርጋቸው ጽጌ እንዲህ ባሉ የሞራል ቀውስ ውስጥ ሆነው የለም ሲሉት የነበረውን አማራ ሲያሻቸው መሪ፣ ሲያሻቸው ተችቶ ተሰናባች ያደረጋቸው ከዚህ ህዝብ የወጡ አቅም ያላቸው ዝም በማለታቸው የተነሳ ነው” የሚሉ ” የአማራ ህዝብ ጨዋና ሌሎች ሊገዙት የሚችሉት ፖለቲካ የሚያራምዱ በወንዝና በሰፈር የማይታጠሩ ልጆቹ ካልተነሱለት በድህነት መማቀቁ፣ የጦርነት አውድማ መሆኑ፣ ለዘመናት ሊወታው ከማይችለው አዘቅት ውስጥ ሊወታ አይችልም” ይላሉ።

“አቶ አንዳርጋቸው ዕድሜያቸው ገፍቷል። ስቃይን አይተዋል። ሞትን ሲጠባበቁ የነበሩ ሰው ናቸው። በዚህ ደረጃ የአማራ ሕዝብ ስቃይ ከታያቸውና ከተረዱት ስለምን የሻዕቢያን አጀንዳ ተሸክመው ክልሉን የጦርነት አውድማ ለማድረግ ይሰራሉ? ስለምን የሰላም አማራጭ ላይ አይተጉም? ስለምን ዘመናቸውን ሁሉ ከሻዕቢያ ጋር አጣብቀው መኖርን ይመርጣሉ?” በሚል የሚጠይቁ “አሁን ላይ የሚሰደዱ፣ የሚፈናቀሉ፣ እሳቸው እንዳሉት የተሰላቸ ሕዝብ ምን መፍትሄ እንደሚያሻው ስለሚረዱ ቀሪ ዘመናቸውን ከደም ፖለቲካ በመውጣት እንዲያጠናቃቁ ይመክራሉ”
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter