ግብጽ ጅቡቲን ወስውሳ ሚስጢራዊ ውል ስታደርግ ሻዕቢያ አሰብን እያጸዳ መሆኑ ተሰምቷል። የሻዕቢያን እንቅስቃሴ እግር በእግር የሚከታተሉ ኢትዮጵያዊ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉት አሰብን ኢትዮጵያ በአንዱ ቀን እንደምትቆጣጠረው አምነዋል። ሌሎች እንደሚሉት ኢትዮጵያ ስትወስን የምትጠቀመው ዘመናዊ መሳሪያና ሰው አልባ ድሮኖች በመሆኑ ሻዕቢያ ፍርሃቻው ከፍተኛ ነው። ኢትዮጵያ ይህንኑ ጠቅሳ ስታስጠነቅቅ ሻዕቢያ መስመሩን ካለፈ ቅጣቱ ከባድ እንደሚሆን አመልክታ ነበር።
“የዘመን ጉዶች ኢትዮጵያን እንደ አገር ለማጥፋትና ሕዝቧን እስረኛ ለማድረግ ያለመው ዜና ሲሰማ ፌሽታ ሆነላቸው” ሲል አሳቡን የሰጠው በሚኖሴታ የሚኖረው ኢትዮጵያን የሚወድ የሶማሌ ዜጋ ነው። “ግን ምን ነካችሁ ኢትዮጵያውያን?” ሲልም ጠይቋል።
- ሰበር ዜና:- የኢትዮጵያ የባህር በር አበቃለት፣ግብፅና ጅቡቲ ኢትዮጵያ ላይ ወሰኑ፣በሌሊት ወታደራዊ ማዘዣው
- ሰበር ዜና:- ያሳዝናል ጅቡቲ በድብቅ ያሰበችልን ሴራ | ከሊባኖስ …
- የብልጽግና ቅጥረኞች ተነሱ ፤ የኤርትራና ትግራይ ጥምረት ይቀጥላል ፤ ግብጽና ጅቡቲ ኢትዮጵያን አገለሉ. ኢ ኤም ኤስ
- ሰበ ርዜና ግብጽና ጅቡቲ ኢትዮጵያን ሊያንቁ ነው
ወዘተ በጩኸት የታጀበ ዜና አየሩን የሞላው በኢትዮጵያ በሚምሉ ባንዳዎች ነው። ኢትዮጵያን አንቆ ለማንበርከክ ታቅዶ የተከናወነው ሴራ ይፋ ሲሆን የጮሁት በኢትዮጵያ ካባ የተሸፈኑ የሻዕቢያና የሻዕቢያ ሽንት ውጤት የሆኑት የትህነግ ክፋይ ባንዳዎች ናቸው።
የህዳሴው ግድብ መገባደጃ ብስራት ሊታወጅ በቋፍ ላይ ያለች አገር ሚዲያዎች ስለ ቀጣዩ ግድብ ያወራሉ እንጂ “ውሃችሁን ለምን ገደባችሁ?” በሚል ለተነሳ ተላላኪና በመላላክ ያገኘውን እየበተነ ኢትዮጵያን ለሚሽከርከር ታሪካዊ ጠላቷ ሊያሸረግዱ ባልተገባ ነበር።
የጂቡቲው መሪ ኢትዮጵያ ላይ ጫና በሚፈጥር መልኩ የቀይ ባህር የውሃ ዳርቻዋን በግብጽ ጥበቃ ስር እንዲሆን ከግብጹ መሪ ጋር ሚስጥራዊ ስምምነት መፈጸሙና ኢትዮጵያ ላይ የበላበትን ወጪት ሰብሮ መማማሉን “ኢትዮጵያዊ ነን” ለሚሉ እንዴት “ሰበር” ዜናቸው ሊሆን ይችላል?
ኢትዮጵያን ዙሪያዋን የሚዞሯት የግብጹ መሪ አብዱልፈታህ አል ሲሲ ባለፈው ሳምንት ከጅቡቲ ፕሬዚዳንት ከኢስማኤል ኦማር ጉሌህ ጋር ተገናኝተው መዶለታቸውን አስመልክቶ የተሰማው ዜና ከወትሮው የተለየ የህልውና ጉሮሮ ላይ ያነጣጠረ መሆኑ አገራቸውን ለሚወዱ ሁሉ አጀንዳቸው ሆኗል። በሌላ በኩል ደግሞ “ለወታደርነት አትመለመሉ ” በሚል ጥሪና የፈጠራ ጩኸት ከሚያሰሙት ጀምሮ ግብጽ ጅቡቲን ተጠቅማ ኢትዮጵያን ለማነቅ ማስላቷን የሚያወድሱ ተሰምተዋል።
ለቅብ ይሁን ዘንዳ ከባህል፣ ንግድና መሰል ጉዳዮች ስምምነት በተጨማሪ የቀይ ባህርና የአዴን ባህረ ሰላጤ ዳርቻዎችን የመጠበቅና የመጠቀም ብቸኛ መብት ያላቸው የዳርቻው ተጋሪ አገራት ብቻ ናቸው የሚል አቋም መያዝቸውን ሲያታውቁ ሚስጢር ያደረጉት ዋና ጉዳይ ሌላ ነበር።
ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረው ዋና ምስጥራዊ ስምምነት ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ወደ ግጭት ከገባች ጁቡቲ ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ ወደ አገሯ እንዳታስገባ ወደቧን ለመዝጋት ከግብጽ ጋር መስማማቷ ነው።
የጅቡቲው መሪ ድሬደዋ ያደጉ፣ ድሬደዋ የተማሩ፣ አማርኛ የሚያውቁ፣ ድሬደዋ ሃብት ያላቸው፣ የኢትዮጵያ ደም ያላቸው እንደመሆናቸውና በወደብ አገልግሎት ከኢትዮጵያ በየዓመቱ ቋሚ ገቢ እያገኙ ኢትዮጵያ ላይ በዚህ ደረጃ ማሴራቸው ያሰገረማቸው የሶማሊያ ተወላጅ “ ጥፋቱ የኢትዮጵያ ነው” ብለዋል።
ጅቡቲ ኤለኤክትሪክ፣ ነጹህ የመጠጥ ውሃ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ጫት፣ የምግብ ቁሳቁሶች ያለማቋረጥ ከኢትዮጵያ የምታገኘው ጅቡቲ ይህን ሚስጢራዊ ውል ከማድረጓ በፊት በኢትዮጵያ ዋና ሸቀጦች ላይ ቤንዚንን ጨምሮ የማዘገየትና እጥረት የማባባስ ተግባር ሲፈስሙ እንደነበር ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በተከታታይ ጅቡቲ በቃኝ ካለች ምን ልንሆን እንደምንችል ሕዝብ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችና ምሁራን እንዲያስቡበት ሲወተውቱ “ኢትዮጵያ የራሷ መተንፈሻ ይዛስፈልጋታል” ማለታቸው ይታወሳል።
ይህንኑ አስደንጋጭና ሚስጥራዊ የተባለ ስምምነት ያጋለጡት በካናዳ የሚገኙት የጂቡቲው ተመራማሪና ጸሓፍት አብዱራህማን በሽር ናቸው። የጂቡቲው መሪ ለኢትዮጵያ ዋነኛ የንግድ መግቢያና መውጫ በር ሆኖ እያገለገለ የሚገኘውን ወደብ ከመዝጋት በተጨማሪ ከሲውዝ ቦይ እስከ ጂቡቲ ዳርቻ ያለውን የቀይ ባህር ክፍል በግብጽ ጥበቃ ስር እንዲሆን የሚፈቅድ ወታደራዊ ስምምነት ለመፈጸም መስማማታቸውን አክሏል።
ይህ መረጃ ሲወጣ ሻዕቢያ አሰብ ያለውን ንብረት ወደ አስመራ እያሸሸና በኢሮብ በኩል ኃይሉን እየገነባ መሆኑን፣ ትህነግ ሁለተኛ የልዑክ ቡድንና ወታደራዊ አመራሮቹን ወደ አስመራ ለመላክ ዝግጅት ላይ መሆኑ በተሰማበት ወቅት ነው።
ኢትዮጵያ በሆነ ቀን አሰብን ልትወር እንደምትችል ለሕዝቡ ደጋሞ የሚናገረው ሻዕቢያ ውስን የፋኖ ኃይሎችን ፣ትህነግና፣ ሸኔን አስተባብሮ ጦርነት በመክፈት የኢትዮጵያን መከላከያ ልበታተን የያዘው ዕቅድ በፈለገው መንገድ አልተሳካለትም።
ትህነግ ለሁለት መከፈሉ ብቻ ሳይሆን፣ በተከፍለው የእነ ደብረጽዮን ቡድን ውስጥ ያሉትም ቢሆኑ ከሻዕቢያ ጋር ወግኖ ለመዋጋት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ አቶ አንዳርጋቸው በንዴት የፋኖ ትግል ተበላሽቷል በሚል እንደገለጹት የፋኖ ኃይል በሚፈለገው መጠን አለመራመዱና አንድ አለመሆኑ፣ ከሁሉም በላይ ኦሮሚያ ላይ የሚፈለገው ሁከት አለመንሳቱና የጃል መሮ ኃይል መሽመድመዱ ሻዕቢያን ስጋት ላይ ጥሎታል።
በመሆኑም ጦርነቱን ኢትዮጵያ ከጀመረች ጥቃት ላለማስተናገድና የጦር መሳሪያና መሰለ ግብአቶች ላይ እጥረት ለመፍጠር ግብጽ ከጅቡቲ ጋር የጅቡቲን ወደብ ለመዝጋት ስምምነት ደርሰዋል። ይህንኑ ስምምነት ኢትዮጵያዊ የሚባሉት ሚዲያዎች፣ አክቲቪስት ነን የሚሉና የአንዳንድ ፓርቲ አመራሮች በገሃድ እያወደሱትና “ሰበር” በሚል እልል እያሉ ነው።
እነዚህ በአገራቸው ላይ እስርና መታነቅን ያወጁ ጉዶች፣ ግብጽ በተመሳሳይ የሞቃዲሾ መንግስት የሶማሊያ የውሃ አካል የሆኑ የኤደን ባህረ ስላጤና የህንድ ውቂያኖስ ደህንነት በግብጽ መንግስት እንዲጠበቅ አሳልፎ መስጠቱንም ማድነቃቸው አይዘነጋም። አፍሪካ ኢንሳይደር ይህን ውል አጣቅሶ የአፍሪካ ቀንድ ውጥረት ውስጥ እየገባ መሆኑን አስታውሷል። ኢትዮጽያ 95% የውጭ ንግድ በጂቡቲ ወደብ ላይ የተመሠረተ መሆኑ፣ ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለጂቡቲ ወደብ ኪራይ እሰከ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደምትከፍል በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል።
የሚኔሶታው ሶማሊያዊ እንዳለው እሱ በሚኖርበት አሜሪካ ኢትዮጵያን በደቡብ ክልልና በሶማሌ ክልል ለመወጠር ኢጄቶንና ሂጎ የሚባለውን የቀድሞ አደረጃጀት ለማንቀሳቀስ በጀት መመደቡንና ይህንኑ የሚመራ አክቲቪስት መመደቡን አመልክቷል። አክቲቪስቱን “ታዋቂ” ከማለት ውጪ በስምም ሆነ በልዩ መለያ አላስታወቀም።
ግብጽ በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን፣ በኬንያ ፣ በዩጋንዳ፣ በመዞር የአባይን ግድብ ለማስተጓጎል፣ አስገድዶ አሳሪ ውል ለማስፈረም በተዘዋዋሪ ስትሰራ ከርማለች። በአገር ውስጥም ባንዳ ቀጥራ የማተራመስ ስራ አጠንክራ እየሰራች ነው። የአሁኑ የጅቡቲው ስምምነት ግን በዓይነቱ ለየት የሚል ቢሆንም ኢትዮጵያ ይህ እስከተጻፈ ድረስ የመለሰችው መልስ የለም።
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter