የፌደራል መንግስት በአሁኑ ሰዓት ከፋኖና ከሸኔ ጋር እያደረገ ባለው ጦርነት አቅሙ በመዳከሙ ጦርነት መክፍት እንዳለበት በዶ/ር ደረጽዮን የሚመራው የትህነግ ስራ አስፈጻሚ አሳብ አቀረበ። አሳቡ ከሻዕቢያ ጋር በመተባበውር ከፋኖና ከሸኔ ጋር በጋራ ኝባር በመፈጠር የፌድራል መንግስቱን ማስወገድ ነው። አሳቡ ከዘጠኙ ተሰብሳቢዎች በአራቱ ተቃውሞ ቀርቦበታል።
ይህ ዜና የተሰማው በዶክተር ደብረጺዮን የሚመራው የህወሓት አንጃ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሰብሰባ እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነው። መረጃው ቀደም ሲል “አፈንጋጭ ” የተባለው ቡድን በድጋሚ መከፈሉን እየገለጹ ያሉትን ወገኖች መረጃ የሚያጠናክር ሆኗል።
ይህንንኑ “መንግስት በጦርነት ተወጥሮ ተዳክሟል። ጊዜው አሁን ነው” የሚለውን ስሌት በቅርቡ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አንስተው ነበር። ጦርነት ለመቀስቀስ እየተዋዋሉ ያሉ ኃይሎች መኖራቸውን ስም ሳይዘዘሩ አንስተው ስለ ስሌታቸውና ዕቅዳቸው “አይመስለኝም። ይቅርባችሁ” የሚል መልዕክት አስተላልፈው ነበር።
ጋት ሚዲያን ጨምሮ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑና በቀጥታ ከመቀለ መረጃ ያላቸው ይፋ እንዳደረጉት ዘጠኙ የአፈንጋጩ ትህነግ የስራ አስፈጻሚ አባላት ሆነው የተሰበሰቡት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ሰብሳቢ፣ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ)፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ፣ ዶ/ር ረዳኢ ፣ አቶ አማኑኤል ኣስፋ፣ አቶ አለም ገብረዋህድ ፣ አቶ ተክላይ ገ/መድህን ፣ሊያ ካሳ እና፣ ዶ/ር ፍሳሃፅዮን ናቸው።
ይኸው አካላ በትናንትናው ዕለት የመጀመሪያውን ስብሰባ ሲያደርግ፣ የቀረጸው አጀንዳ አራት ሲሆኑ እነሱም ፤ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግስት ወታደራዊ አቅም ያለበትን ሁኔታ መገምገም፣ምዕራብ ትግራይን በተመለከተ፣ ተፈናቃዮችን መመለስ በተመለከት፣ የጊዚያዊ መንግስቱን አደረጃጀት ማጠናከርና እየከዳ ስላለው ታጣቂ ኃይል በተመለከተ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
በአጀንዳዎቹ መወያየት ጀምሮ በይደር የተለያየው የትህነግ አንድ ክፍል ሰፊ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች እየከዱ መሆኑን አስመክቶ ውይይቱን በይደር የሚነጋገሩበት ሲሆን፣ ለጊዜው በተወያዩበት “ከሻኧቢያ፣ ፋኖና ሸኔ ጋር ተባብረን ጦርነት እንጀምር” የሚለው አሳብ ላይ ልዩነት መነሳቱ ታውቋል።
“I fought for Tigray to become its own country. Now our leaders can’t even agree on making it a functioning region, ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር ትሆናለች ብዬ ተዋጋሁ። አገር መሆኑ ቀርቶ ትግራይን እንደክልል እንኳን ለማስቀጠል መሪዎቹ ምወስማማት አልቻሉም” ሲል መንገXአ የተባለ የታጣቂው አባል Augustine Passilly (Special Correspondent in Mekele) la-croix ሚዲያ ላይ እንደገለጸው በርካታ የቲዲኢኤፍ አባላት መዋጋት አይፈልጉም።
አሁን ክልሉን በፕሬዚዳንትነት እንደሚመሩ ግምት የተሰጣቸው የቀድሞ ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረድ ” ሰፊ ቁጥር ያለው የቲዲኤፍ ኃይል እየከዳ ነው” ሲሉ በገሃድ መናገራቸው አይዘነጋም።
ከርዕዮት ሚዲያ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት የአቶ ጌታቸው ረዳ ካቢኔ አባል ዶክተር ሺሻይ፣ ሰፊ ቁጥር ያለው ታጣቂ ኃይል ” ሴጣናዊ አስተሳሰብ አለው ካሉት” አንጃ እየከዳ መሆኑን ይፋ አድርገው ” ይህን ኃይል መልሰን እናደራጀዋለን” ብለዋል፡፡ ከቲዲኤፍ የሚሸሹት ታጣቂዎች ለትግራይ ስለሚያስፈግልጉ ሲበተኑ ዝም ብለው እንደማያዩ ያስታወቁት ዶክተሩ እየሸሹ ያሉት ታጣቂዎች ከትግራይ ውጪ ባሉ አካባቢዎች እየተሰባሰቡ መሆኑን አምልክተዋል። እየከዱ የወጡትም አለቆቻቸው በፈጸሙት ተግባር መነሻ መሆኑን አመልክተዋል።
በተመሳሳይ የፋኖ፣ ቀድሞም ከትህነግ ጋር ጥምረት መፍጠሩን ያስታወቀው የጃልመሮ ኃይል በገሃድ ከትህነግ ጋር ተጣምረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። ብርጋዴል ጄነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን ጥምረቱ የማይቀር እንደሆነ ቦናገሩም ቀሪ ክፍ
ከቲዲኤፍ ጥለው የወጡ በተለያዩ የማህበራዊ አውዶች “ራሳችንን አደራጅተን እንታገላለን” ሲሉ ተሰምተዋል። የትግራይን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉ አንቂዎችም ይህንኑ የሚያጠናክር መረጃ እያሰራጩ ባለበት ሁኔታ “ጊዜው አሁን ነው ከሻዕቢያ፣ ከፋኖ፣ ከሸኔ ጋር ተባብረን መንግስትን እናስወግድ” የሚሉት ወገኖች ያቀረቡትን አሳብ አቶ አለም ገብረዋህድ ፣ አቶ ተክላይ ገ/መድህን ፣ሊያ ካሳ እና፣ ዶ/ር ፍሳሃፅዮን መቃወማቸው ታውቋል።
እነ አቶ አለም ገብረዋህድ ወይም አራቱ ከላይ የተዘረዘሩት፣ በፕሪቶሪያን የሰላም ሥምምነት መሰረትመንቀሳቀሱ ትርፋማ ሊያደርግ እንደሚችል ስብሰባው ላይ አንስተዋል። መረጃ አለን በሚል የስብሰባውን ውሎ ይፋ ያደረጉ ገልጸዋል።
በተቃራኒ የቆሙት እነዝህኞቹ ወገኖች፣ “ከፌድራል መንግስት ጋር በትብብር ብንሰራ ያዋጣል። ከዚህ ውጭ ከሻዕቢያም፣ ከፋኖና ከሸኔ ጋር ኝባር በመፍጠር ጦርነት መክፈት አያዋጣንም” ማለታቸው ተሰምቷል።
ከጠቀሷቸው አካላት ጋር ሆነው በመንግስት ላይ ውጊያ ቢከፍቱ፣ ዓለም አቀፍ ጫና እንዲሁም ማዕቀብ ሊጣልባቸው እንደሚችል የገለጹት የእነ ዓለም ገብረዋህድ ወገኖች፣በጦርነቱም መሸነፍም እንደሚኖር አውስተዋል። ከዓለም አቀፉ ተቃውሞና ማዕቀብ ባሻገር እንደቀድሞው ህዝብ ከጎናቸው ላይቆም እንደሚችል አንስተው ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።
እነ ዶክተር ደብረጽዮን “የትግራይ ተፈናቃዮችን ወደ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ለመመለስ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን ፋኖ እየደገፍን በዞኑ ያለውን መዋቅር እንዲያፈርስ እየተንቀሳቀስን ስለሆነ ተፈናቃዮች የሚመለሱት አካባቢውን በሃይል መልሰን ከተቆጣጠርን በኋላ የእኛን መዋቅር ስንዘረጋ ነው” የሚል አቋም ላይ መደርሳቸውን በስብሰባው ላይ አንስተዋል። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ሙሉ መዋቅርም በነባር የትህነግ አባላት እንዲያዝ የሚል አቋምም አንጸባርቀዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ትህነግ ምንም አይነት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ” እግድ መጣሉ የሚታወቅ ነው።
በቅርቡ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው ታዋቂው መጽሄት የአሜሪካ ኦፊሳላዊ ባለስልጣናት እንደነገሩት ጠቅሶ ባወጣው መረጃ መሰረት “አክራሪ” ያላቸው የትህነግ አመራሮች ወደ ጦርነት የሚገቡ ከሆነ የተለያዩ ማዕቀቦችንና በውጭ አገር ያለ ሃብታቸውን እንዳይንቀሳቀስ ሊያደርግ እያሰበ ነው።
በጦርነቱ ወቅት የትህነግ ደጋፊና አዝማች የነበሩ ሚዲያዎች ዛሬ ላይ “ወቅት፣ የሃይል አሰላለፍን፣ የአካባቢና የቀጣናውን ፖለቲካ መረዳት የማይችሉ ቆሞ ቀሮች” በሚል እያወገዟቸው ቢሆንም፣ አሁንም በድጋፍ የቀጠሉት በጣም ጥቂቶቹ ” የፋኖ ኃይል ወደ ወልቃይት ገብቷል እነሱን ተጠቅመን መልሰን ምዕራብ ትግራይን እንቆጣጠራ” በሚል በይፋ በድምጽና በምስል ቀርበው ሲናገሩ እየተድመጠ ነው።
በዚሁ መነሻ ” ምዕራብ ትግራይ የገባ የፋኖ ታጣቂ ይውጣ እያሉ፣ አብረን ከፋኖ ጋር ግንባር ገጥመን የፌደራል መንግስትን እናፍርስ እያሉ፣ እንደገና ፋኖ ወደ ወልቃይት ገብቷል / የጎጃሙን ፋኖ ማለታቸው ነው/ ወልቃይትን እናስለቅቅ ይላሉ” በማለት ፋኖን እንዴት እየተጠቀሙበት እንደሆነ የሚናገሩ፣ ይህ አካሄድ ዳግም እልቂት እንጂ ለተፈናቀሉ ሰላማዊ ዜጎች መፍትሄ እንደማያመጣ ያስጠነቃቃሉ።
ሰሞኑን ከአንድ ሚዲያ ጋር በትግርኛ ሰፊ ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቶ ጌታቸው ረዳ ” ቆሞ ቀር” ሲሉ የሚገልጹትን ይህን ኃይል፣ ” ለተፈናቀሉት ሳይሆን ለሰሊጥ ነው ትኩረታቸው” ሲሉ መግለጻቸው አይዘነጋም።
ወልቃይትን አስመልክቶ ገለልተኛ ወገኖች ” መጀመሪያ የተፈናቀሉት ይመለሱ፣ ዞኑ ከአማራም ሆነ ከትግራይ ክልል ውጪ ሆኖ ለተወሰነ ጊዜ ሕዝቡ እንዲያገግም ይሁን። ከተወሰነ ጊዜ በሁዋላ ሕዝብ ራሱ በነጻነት የሚወስንበት አግባብ ተግብራዊ ይሁን” የሚል አሳብ አላቸው።
በትግራይ ህዝብ በአብዛኛው ጦርነት እንደማይፈልግ በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገለጸ ሲሆን፣ ወጣቱ በተለይ በአደባባይ ተቃውሞ እያሰማ እንደሂኦነ የምስል ዘገባዎች ምስክር ናቸው።
በመቀለ ተገኝታ ” Former Tigray fighters say no to war፣ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎች አንዋጋም አሉ” በሚል ርዕስ ዘገባ ያቀረበችው የላ ክሮኢክስ ዘገቢ ” መሞት አልፈልግም” ያለውን የሰራዊቱን አባል ትጠሳቅሳለች። “ከአሁን በሁዋላ ገቢ የለንም፤ ቢያንስ ቢያንስ ቲዲኤፍ ዳቦ ያበላኛል ብዬ አስብ ነበር” በሚል የሚጠብቀውና የሆነው እንድተለያየበት ያመልክታል፤ በኢሁ ዘገባ “ጦርነት ቢጀመር ወደ አዲስ አበባ እሸሻለሁ” ያለች ወጣትና “… ካሁን በሁዋላ እኔ ሞቼ ቤተሰቦቼን ለዕድሜ ልክ ጸጸት መዳረግ አልፈልግም” ያሉትን በዘገባዋ አካታለች።
በሌላ ዘገባ ወደ ወልቃይት የገባውን የፋኖ ኃይልም ሆነ ይህንኑ ተንተርሶ ውጊያ ለመክፈት እይሰበና እየተዘጋጀ ነው የሚባለውን ትህነግን እንከላከላለን በሚል ስሙ ” የተከሼ ዘብ” የተሰኘ ሰፊ ቁጥር ያለው ኃይል ማስመረቁን የወልቃይት ጠገዴ ዞን አስተዳደር መግለጫ ባወጣ በሳምንት ጊዜ ውስጥ አስታውቋል።
መንግስትም ባለፉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከ150 ሺህ በላይ ወታደሮች፣ የተለያዩ ባለሙያዎችና የውጊያ አመራሮችን አሰልጥኖ ማስመረቁን የመንግስት መገናኛዎች እያሳዩ ነው። የአማራ ክልልም ሰፊ ቁጥር ያለው አድማ በታኝ ሰራዊት አስመርቆ ወደየዞን ከተሞች ልኳል።
መንግስት ወደ ጦርነት የመመለስ ፍላጎት እንደሌለው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ” የሚሞክሩ ካሉ አጻፋው እጅግ ከባድ ነው” ሲል ማስጠንቀቁ አይዘነጋም። በተለይም ሻዕቢያ አንድ ጥይት ከተኮሰ የሚወሰደው ርምጃ የኢትዮጵያን አየር ኃይልና የከባድ መሳሪያ አቅም የሚያሳይ እንደሚሆን ስለ ዝግጅቱ የሚያውቁ እያስታወቁ ነው።
ስለማን የሚሰብኩ እንደሚሉት ጦርነት ማናቸውንም ወገን የማይጠቅም፣ ሕዝብን ለመከራ የሚዳርግ፣ ድሉም ዘላቂ ሰላም የማያመጣና ሌላ ወገንን ዳግም ወደ ጫካ የሚልክ፣ በተደጋጋሚ ጉዳቱ በተግባር የታየ በመሆኑ ጠብመንጃ ያነሱ ኃይሎች ለምስኪኑ ሕዝብ ሲሉ ጉዳያቸውን ወደ ጠርጴዛ ይዘው እንዲመጡ እየወተወቱ ነው።