“ማዕከላዊ ኮሚቴያችን ተቋቁሟል የሚባለው የብዙሃን ፍላጎትና ተሳትፎ ያገለለ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ የብዙሃን አመለካከትና ወገኖች ፍላጎት ባካተተ መልኩ ዳግም በአስቸኳይ እንዲዋቀር ጥሪ እናቀርባለን” ሲል የእነ አቶ ጌታቸው ትህነግ አሳሰበ። ይህ ካልሆነ ግን ” የትግራይ ህዝብ ከተጫነበት የኋላ ቀር ቡድን ፍላጎት ለማላቀቅ ትግላችንን አጠናክረን እንደምንቀጥል እናሳውቃለን” ብሏል።
ትግሉ እንዴት እንደሚቀጥልና ዓላማው ምን እንደሆነ ያስታወቀው መግለጫ፣ “… መላውን አመራሮቻችንን፣ አባላቶቻችንን፣ ህዝባችንን፣ የፌዴራል መንግስትን እና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ የትግራይን ህዝብ ፍላጎት እና የተለያዩ አመለካከቶችን በሚያረጋግጥ መልኩ ለማሳካት ነው”
የተካሄደው መፈንቅለ መንግስት የትግራይን መጻኢ ተስፋ ያጨለመና የትግራይ ተወላጆችን የበታተነ ቢሆንም የፌደራል መንግስት የተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት ወደ ሰላማዊ አግባብ ለመመለስ የስራ ጊዜው ያጠናቀቀውን ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ከስልጣን በማንሳት አዲስ ፕሬዝዳንት መሾሙን ያስታወሰው መግለጫው፣ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት የተለያዩ ፓርቲዎች እና አካላት የተሻለ ተሳትፎ የሚያረጋግጥ አካታች (inclusive) መንግስት እንደሚዋቀር በተሾመው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት እና በሌሎች የፌደራል አካላት ሲገለጽ ቆይቷል” ሲል መግለጫ ህግ እንዲከበር አሳስቧል።
በእነ ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት በምርጫ ቦርድ ተቀባይነት ያላገኘን አጠቃላይ ጉባኤ ማካሄዱ ተከትሎ የህወሓት አመራሮች ለሁለት የከፈለ አለመግባባት መፈጠሩ አይዘነጋም።
አለመግባባቱ ተካሮ ወደ ግጭት ሊያመራ ከጫፍ ሲደርስም በህወሓት ተመርጠው በዶ/ር አብይ አህመድ ተሹመው የክልሉ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ጌታቸው ረደ ከትግራይ ወጥተው ስልጣናቸውንም ለሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ አስረክበው እሳቸው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አማካሪ ሆኖው መሾማቸው ይታወአሳል።
እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነም ስልጣናቸው ባስረከቡ ማግስት በትግራይ ፖለቲካ ውስጥ ለመሳተፍ ቃል የገቡት አቶ ጌታቸው የህወሓትን ህጋዊ እውቅና ለማስመለስና ፓርቲውን ከጥፋት ለመታደግ ሲባል ጉባኤ ለማካሄድ መወሰናቸው በመግለጫ አስታውቀዋል።
በጌታቸው ረዳ ከሚመራው ህወሓት የተሰጠ መግለጫ በሚል በተሰራጨው ፅሑፍም “ጉባኤ እናካሂዳለን፣ ፓርቲያችንን ህጋዊ ሰውነት እንዲኖረው እናደርጋለን፣ ግላዊና ቡዱናዊ ፍላጎቶቻችን ወደ ጎን በመተው ታረካዊ ውሳኔ እንወስን” ብልያል።
ሲቀጥልም ምርጫ ቦርድ ውሳኔ ለመስጠት ያስቀመጠው የገዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ ህግና ስርዓት በሚፈቅደው መሰረት መላው የፓርቲው አባላትና የትግራይን ህዝብ ባሳተፈ መልኩ ገለባኤ እናካሂዳለን ሲል በእነ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው አስታውቋል።
አሁን በእግድ ላይ የሚገኘው ህወሓት የምርጫ ቦርድ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ፤ ለሦስት ወራት በምንም ዓይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ አንዳይሣተፍ እንዲታገድ የወሰነ ሲሆን ፓርቲው ለእግዱ ምክንያት የሆነውን ጥሠት በማረም፤ ዐዋጁን ተከትሎ የወጣውን መመሪያ፣ የቦርዱን ውሣኔዎችና ትዕዛዞች በማክበር ፖርቲው ሊያደርግ የሚገባውን ጠቅላለ ጉባዔ ለማድረግ የሚያስችለውን የጉባዔ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለመሥራት ለቦርዱ በጽሑፍ ሲያሳውቅና ቦርዱ ይህንኑ ሲያረጋግጥ በመመሪያው መሠረት ቦርዱ ዕግዱን የሚያነሣ መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም።
ከዚህ ባሻገር ፖርቲው በተሰጠው የሦስት ወራት የዕግድ ጊዜ የዕርምት ዕርምጃ ሳይወስድ ቢቀር የፓርቲው ምዝገባ እንዲሠረዝ የምርጫ ቦርድ የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ/ም ባካሄደው ስበሰባ ወስኗል። ይህ በእነዲህ እንዳለ እነ አቶ ጌታቸው ረዳ የትንሳዔ በዓልን ተንተርሰው የሚከተለውን መግለጫ አውጥተዋል።
የአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ትህነግ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቤኔ አወቃእርን አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ! አማርኛ ትርጉም
የተከበርክ የትግራይ ህዝብ፣ የተከበራችሁ የህወሓት አባላት፣ የተከበራችሁ የአጋር ፓርቲዎች አመራርና አባላት፣ የተከበራችሁ የሲቪል ማህበራት አመራርና አባላት፤ የተከበራችሁ የትግራይ ዲያስፖራ ማህበረሰብ፤ በመጀመሪያ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ!
ኮርና እና ከኮር በላይ የተባለው የአደመ (የደብረጽዮን ቡድን) ህገወጥ ጠባቂ ባሳለፈው ኢፍትሃዊ ውሳኔ በትግራይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ከተካሄደ ወደ አርባ ቀናት ይሆነዋል::
የተካሄደው መፈንቅለ መንግስት የትግራይን መጻኢ ተስፋ ያጨለመና የትግራይ ተወላጆችን የበታተነ ቢሆንም የፌደራል መንግስት የተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት ወደ ሰላማዊ አግባብ ለመመለስ የስራ ጊዜው ያጠናቀቀውን ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ከስልጣን በማንሳት አዲስ ፕሬዝዳንት ሾሞ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት የተለያዩ ፓርቲዎች እና አካላት የተሻለ ተሳትፎ የሚያረጋግጥ አካታች (inclusive) መንግስት እንደሚዋቀር በተሾመው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት እና በሌሎች የፌደራል አካላት ሲገለጽ ቆይቷል።
በእኛ በኩልም ምንም እንኳን ከፕሬዝዳንት ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደ ጋር ለማድረግ ያቀድነው ውይይት ባይሳካም የተሻለ አቃፊ ካቢኔ እንዲዋቀር ከሚመለካታቸው አካላት ጋር ስንወያይ ቆይተናል። በተጨማሪም ለሁሉም ተደራዳሪዎች እና አደራዳሪዎች ግልጽ የሆነ አቤቱታ አቅርበናል።
ነገር ግን ያደረግነውን ጥሪና የተገለጸውን አቅጣጫ ወደ ጎን በመተው አዲሱ ፕሬዝዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ የአንድ ተገንጣይ ህገ-ወጥ ቡድን ፍላጎት ላይ ብቻ ተመስርቶ የትግራይ ህዝብን ስሜትና ፍላጎት ያላሟላ፣ ተጀምሮ የነበረውን አቃፊነትና አሳታፊነት ወደኋላ የሚመልስ፣ የትግራይ ህዝብ አንድነትን በከፋ መልኩ የሚያፈርስ፣ የወጣቶችን የለውጥ ተስፋ የሚያጨናግፍ . . . መንገድ በመምረጥ አዲሱን ካቢኔ አዋቅሯል።
ይህ ወላጆቻችን “በድህነቷ ላይ ጥጃዋ ትሞታለች” እንደሚሉት ተረት ሆኖ አሁንም ትግራይ ከገባችበት ችግር እንዳትወጣ ጄኔራል ታደሰ ከቡድኑ (የደብረጽዮን) ጋር በመቆም የኮርና ከኮር በላይ ህገወጥ ውሳኔ የሚተገብር ሁሉንም ያላተፈ ካቢኔ አዋቅሯል:: ይህ ህገወጥ ውሳኔ በመገናኛ ብዙሃን በተደጋጋሚ ሲገለጽ የነበረው አሸናፊና ተሸናፊ የሌለባት የሁሉም የሆነች ትግራይን ሳይሆን ለሁለት አመታት በድብቅ ሲሰራ የቆየው ሴራ የሚያጋልጥ ሆኖ አግኝተነዋል።
ማዕከላዊ ኮሚቴያችን ተቋቁሟል የሚባለው የብዙሃን ፍላጎትና ተሳትፎ ያገለለ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ የብዙሃን አመለካከትና ወገኖች ፍላጎት ባካተተ መልኩ ዳግም በአስቸኳይ እንዲዋቀር ጥሪ እናቀርባለን::
ይህ ካልሆነ ግን መላውን አመራሮቻችንን፣ አባላቶቻችንን፣ ህዝባችንን፣ የፌዴራል መንግስትን እና አለም አቀፉን ማህበረሰብ የትግራይን ህዝብ ፍላጎት እና የተለያዩ አመለካከቶችን በሚያረጋግጥ መልኩ ለማሳካትና የትግራይ ህዝብ ከተጫነበት የኋላ ቀር ቡድን ፍላጎት ለማላቀቅ ትግላችንን አጠናክረን እንደምንቀጥል እናሳውቃለን።
ዘላለማዊ መታሰቢያ ለሰማዕቶቻችን!
12 ሚያዝያ 2017ዓ.ም
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter