አቶ ኤሊያ መሰረት እንደወትሮው በትጋት ሳይሆን፣ አሁን ላይ አልፎ አልፎ በግል የማህበራዊ ገጹ ላይ “ ለመሰረት ሚዲያ እንደነገሩን ከሆነ” በሚል ስም ሳይጠቅስ ካሰራጫቸው ዜናዎች መካከል ሰሞኑን ከጥሻ ውስጥ ተነስቶ የተጠገነው ዳሽን5 የተሰኘው አውሮፕላን ጉዳይ ይገኝበታል። እኔንም መጠነኛ አስተያየቴን ለማቅረብ የተነሳሳሁት በዚሁ ዜና መነሻነት ነው።
መነሻዬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ለ37 ዓመት ጥሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረውን “የቀድሞ ፕሬዚዳንት የኮሎኔል መንግስቱ አውሮፕላን ተጠግኖ ስራ ላይ ዋለ” የሚለው ዜና ነው። ዜናው ቅድሚያ አድናቆት ሊቸረው የሚገባ ድንቅ ዜና ሆኖ ሳለ አቶ ኤሊያስ ዜናውን ለማቆሸሽ የሄዱበት ርቀት እንደ ዜጋ አሳዘነኝ።
ይህ እና ይህን መሰል መልካም ዜናዎችን እግር በእግር እየተከታተሉ ከማቆሸሽ ማን እንደሚጠቀም ሊገባኝ ያለመቻሉ ብቻ ሳይሆን፣ ባህል እየሆነ የመጣው ሁሉንም ጉዳይ የማጠልሸት፣ የማቆሸሽ፣ የማዳከና የማጣጣል ባህል በሚገርም ፍጥነት መለመዱ ነው። ለዚህም ምስክሩ በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ተከታይና አድማጭ ወይም ተመልካች ያላቸው በዚህ መሰሉ አሰራር የተቀኙ ክፍሎች መሆናቸው ነው።
“ዳሽ 5 ወይም ቡፋሎ በሚል መጠሪያ የሚታወቀውና ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለ ማርያም አገልግሎት ይሠጥ የነበረው ይህ አውሮፕላን የተጠገነው በኢትዮጵያ አየር ኃይል የጥገና ሰራተኞች ነው” መባሉን ተከትሎ አቶ ኤሊያስ መሰረት፣ ዜናውን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር በማያያዝ የሚከተለውን መረጃ አሰራጨ።
“የመንግስት ሚድያዎች “የቀድሞው ፕሬዝደንት መንግስቱ ኀይለ ማርያም አውሮፕላን” የሚል መረጃ ደጋግመው ሲጠቀሙ ታይተዋል፣ ይህ ደግሞ አሳሳች ነው። ኮ/ል መንግስቱ ሲጠቀሙ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን እንጂ የራሳቸው አውሮፕላን አልነበራቸው። ይኼ ነገር ምናልባት ከሰሞኑ ቅንጡ እና የ VIP አገልግሎት የሚሰጥ አውሮፕላን ሀገር ቤት አገልግሎት ሊጀምር ስለሆነ እና ጠ/ሚሩ ይጠቀሙበታል ስለተባለ እሱን ዜና ማደንዘዣ እንዳይሆን ብዬ አሰብኩ”
ከላይ በተቀመጠው የአቶ ኤሊያስ መረጃ ላይ አውሮፕላኑ የቀድሞ መሪ የኮሎኔል መንግስቱ መባሉ “አሳሳች ነው” በሚል ነቀፌታን ለማስቀደም የፈጠነ ሆኖ እግኝቸዋለሁ። ጥገና መደረጉን በአዎንታዊነት፣ ይህ አሮጌ አውሮፕላን እንዴት ዘምኖ ተሰራ የሚለውን ጉዳይ አንስቶ መማማርና ሲገባ፣ ትልቁን ዜና በማይገባ አተካሮ እንዲተካ መፈለጉ ከምን የመነጨ እንደሆነ እንድመረምር አስገድዶኛል። ይህንኑ ምርመራዬን በሌላ ጊዜ አቀርባለሁ።
ሃራሬ ድረስ በመሄድ የኮሎኔል መንግስቱን ታሪክ በመጽሃፍ ያሳተሙት ገነት አየለ “ … ይቺ የፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም እንደነበረች ራሳቸው አረጋግጠውልኛል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ካዝና በወጣ ገንዘብ የተገዛች ሳትሆን የሶቭየት ኅብረት መንግሥት በስጦታ የሰጣቸው እንደነበረች ዛሬ በስልክ ጠይቄያቸው ነግረውኛል። አረጋግጭልን ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ መልሱ ይኼው “
ደውለው እንዳረጋገጡ የገለጹትና በሰጡት መረጃ “ነጭ ውሸት” ተብለው የተገረመሙት ገነት አየለ፣ “ተጨማሪ መረጃ” በማለት የመረጃ ምንጫቸውን ስምና የስራ ድርሻ ጠቅሰው ምናባዊ ሳይሆን የሚጨበጥ መረጃ አስከተለዋል።
ተጨማሪ
ስለዚች አውሮፕላን የሚያውቁና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰው ይሄንን ነግረውኛል።
1 – የሶቭየት መንግሥት የዚችን መሰል አውሮፕላኖች ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሶሻሊስት አገሮች በተመሳሳይ ጊዜ በስጦታ እንደሰጡ የሶቭየት መንግሥት አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሶሻሊስት አገሮች በተመሳሳይ ጊዜ በስጦታ እንደሰጡ
2-ለኢትዮጵያ የተሰጠችው አውሮፕላን መሪ በመሆናቸው ለመንግሥቱ ትመደብ እንጂ ተጠቅመውባት እንደማያውቁ
3-ይህ የሆነው አውሮፕላኗ በጣም ደካማ በመሆኗ ነው። ለዚህ ማስረጃ በወቅቱ የአርሚ አቪዬሽን ባልደረባ የነበሩት ፓይለት ኮሎኔል እሸቱ ዋጋዬ ያጋጠማቸው ነገር ነው። መረጃ ሰጪዬ እንደነገሩኝ ይቺው አውሮፕላን ጓድ ፍስሐ ደስታን ይዛ ከድሬደዋ ስትነሳ አብራሪዋ ብቃት ያላቸው ፓይለት ቢሆኑም ከአውሮፕላኗ ደካማነት የተነሳ የደንገጎን ከፍታዎች ለመውጣት ተቸግረው እንደምንም ታግለው መምጠቅ እንደቻሉ ነው። ከዚያ በኋላ በአውሮፕላኗ መብረር አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ሪፖርት ተደርጎ እንደቀረች ነው።
በደራሲዋ መረጃ መሰረት ኮሎኔል መንግስቱ ተሰጣቸው የተባለችው አውሮፕላን ራሽያ ስለመሰራቷ ያሉት ነገር የለም። ኮሎኔሉም በጥራቷ ምክንያት አይሄዱባትም።
“ የተሳሳተ ዜና” በሚል ስራቸውን በወጉ ባማይሰሩ የመንግስት የሚዲያ ተጧሪዎች ላይ አፉን የሚጠርገው ኤሊያስ፣ እንደለመደው ገነት ላይ እንደለመደው አፉን አሟሽቷል።
አቶ ኤሊያስ “ይህ መረጃ ነጭ ውሸት ነው!“ በማለት ጀምሮ “ቀላሉ ማስረጃ እና ማንም በሰከንዶች ጉግል አድርጎ የሚረዳው ሀቅ አለ፣ እሱም እሷ በለጠፈችው ፎቶ ላይ የሚታየው እና ታድሶ መብረር ቻለ ተብሎ በመንግስት ሚድያዎች ጭምር ስሙ ተጠቅሶ የነበረው DHC Buffalo የተባለ የካናዳ ስሪት አውሮፕላን ሲሆን እሷ የምታወራው ስለ ሶቪየት ህብረት አውሮፕላን ነው። ማስረጃውም ይኸው” ሲል ማስፈንጠሪያ አክሎ አትሟል። https://www.baesystems.com/…/de-havilland-canada-dhc-5…
እርግጥ ነው አቶ ኤሊያስ መሰረት ከኔም፣ ከማናችንም በላይ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ኃላፊና እሳቸው በፖለቲካና በአካባቢያዊ ስሜት ለሰበሰቧቸው ካድሬ የድርጅቱ ሰራተኞች ቀረቤታ ነበራቸው። አሁንም ድረስ ከዛ እንዳገኙ በመጥቀስ የሚያናፍሷቸው መረጃዎች በዚሁ የቀድሞ ትሥሥራቸው መነሻነት እንደሆነ አይታበልምና መረጃ የላቸውም አልልም። ግን አውሮፕላኑ ጃፓን፣ ጋቦን፣ ኡጋንዳ፣ ኤርትራ፣ ቬትናም፣ ሩዋናዳ … ወይም ሩሲያ ተሰራ በሚል ገነት የት ጋር ተነፈሱ?
“ከኢትዮጵያ መንግሥት ካዝና በወጣ ገንዘብ የተገዛች ሳትሆን የሶቭየት ኅብረት መንግሥት በስጦታ የሰጣቸው እንደነበረች ዛሬ በስልክ ጠይቄያቸው ነግረውኛል” ሲሉ ኮሎኔሉን ጠቅሰው መረጃ ማከፈላቸውን ተከትሎ “ ከላይ ያለውን መረጃ የፃፍሽው ትክክለኛው የኮ/ል መንግስቱን ትዝታዎችን የፃፍሽው ገነት አየለ ከሆንሽ መንግስቱ የነገሩሽን ደግመሽ አጣሪው” ስር ስራቸው እያለ ይኖርባቸው ከነበሩት ካድሬዎችና አለቆቻቸው እንደተማረው ለማሸማቀቅም ሞክሯል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለሙያዎችን ለማጣታል ከቀድሞውና በሌብነት አገር ይዞ የተገነደሰውን፣ የኢትዮጵያን አንጡራ ሃብት በገሃድ ሲቸበችብ የኖረውንና የአገሪቱን ምርጥ ተቋም አገር ያለበሰ ተቋም ጉያ ስር በድርጎ የኖረው ኤሊያስ፣ ይህንኑ በሌብነት የበሰበሰ ተቋም ጠቅሶ “መሸሻ” ስለሚባለው አውሮፕላን የጥገና ታሪክ በማንሳት ሊያላግጥ ሞክሯል።
አቶ ኤሊያ ለገነት በሰጠበት ዘለፋ አዘል ምላሽ፣ “ ምናልባት ለማለት የፈለገችው በአንድ ወቅት ሶቪየቶች ለኮ/ል መንግስቱ ሰጥተውት ስለነበረው ‘መሸሻ’ የሚል ቅፅል ስም ስለነበረው Tupolev ስሪት አውሮፕላን ሊሆን ይችላል፣ እሱ ግን ሌላ አውሮፕላን ነው።” ሲል የሰማውን ተረት ያቀርባል። ተረቱ የሚያስፈግግ ቢሆንም የቀረበበት አግባብ አሁን በድንቅ ችሎታ አውሮፕላኑን ደረጃውን አሻሽለው የሰሩትን ባለሙያዎች እንደ በስብሶ ከነበረው ሜቲከ የብየዳ ስራ ጋር ለማዝመድ የሄደበት ርቀት ነው። ይህን አስመልክቶ ጥገናው በምን ደረጃ እንደተከናወነ ለባለሙያዎቹ እተወዋለሁ። ይቀጥላል አቶ ኤሊያስ፤
“ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል እና፣ ስለዚህ “መሸሻ” ስለተባለ የሶቪየት አውሮፕላን በቅርቡ የሰማሁትን ላካፍላችሁ። ሶቪየቶች ይህን አውሮፕላን ለኮ/ል መንግስቱ ከሰጡ በኋላ ፕሬዝደንቱ አልተጠቀሙበትም ነበር። ሙሉ ነጭ የተቀባው እና ጭራው ላይ የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለው “መሸሻ” ለበርካታ አመታት በቢሾፍቱ አየር ሀይል ግቢ ቆሞ ነዋሪዎች ያዩት ነበር። ከዛም ኢህአዴግ ከገባ በኋላ እና ሜቴክ ከተቋቋመ በኋላ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ይህን የሶቪየት አውሮፕላን ለጠ/ሚር መለስ ዜናዊ የ VIP አውሮፕላን እንዲሆን እቀይረዋለሁ በማለት ቆራርጠው፣ ቀጥለው፣ ነቃቅለው፣ ሰካክተው ጨረሱ። ከዛ ለበረራ ብቁነት ምዝገባ ሲቪል አቪዬሽንን ሲጠይቁ ተቆጣጣሪዎቹ “ይሄ ለበረራ ብቁ አይደለም” ብለው ፍቃድ እንደተከለክሉ እና ከዛ በኋላም ቆሞ እንደቀረ ሰምቻለሁ”
አቶ ኤሊያስ በዚህ መልኩ ሩቅ ሄዶ የተረከበት ምክንያት አንባቢያን እንድትመረመሩት እያሳሰብኩ፣ ገነት ለዚህ ተረት የሰጡት ምላሽ የበኩሌን እንድል፣ ያለልማዴ በቅጽበት አስተያየቴን እንድጽፍ እንዳነሳሳኝ ለመግለጽ እወዳለሁ። የረበሸኝና ያነሳሳኝ የገነት ምላሽ ላይ እንዲህ የሚል ሃረግ አለ።
“የምንሰጠውን ወይንም የምንቀበለውን መረጃ በተመለከተ ያለ ነቀፋና ስድብ፣ ያለ ሽኩቻና ቅናት በሰለጠነ መንገድ መነጋገር የሚያቅተን ለምንድነው? ይህ በረጋ መንገድ ሃሳብ የመለዋወጥን ባህል አለማዳበራችን፣ልዩነታችንን ለማጥበብ ቁጭ ብለን መነጋገር ያለመቻላችን ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል። አሁንም እያስከፈለን ነው”
“መንግስቱ ኃይለማሪያምን ጠይቄ እንዲህ አሉኝ” ማለት በዚህ ደረጃ ሊያዘላልፍ ይግባ ነበር? ስህተት ቢኖርስ በጨዋነት መተራረም አይቻልም ነበር? በዚህ ደረጃ ልዩነትን ለማስፋት መድከምን ምን አመጣው? እስከ ማሸማቀቅና የምናብ መረጃ ምንጮች በመጥቀስ ማጠልሸት እስከመቼ?
በቅርቡ አቶ ኤሊያስ የአዲስ አበባ አስተዳደር ባለቤት አልባ ውሾች መገዳላቸውን ጠቅሶ የአዲስ አበባ አስተዳደርን በምናብ በፈጠራቸው ምንጮቹ ሲያወግዝ፣ መርዙ ዘመኑ ያለፈበት፣ የተከለከለ እንደሆነ ጉዳይ ያሳዘናቸው ነገሩት። ኤሊያስ “ስጋታቸውን አጫወቱኝ” ያላቸውን መንፈሶቹን አስቀድሞ አሞራና ሃይቅ ፈጠረ።
የሞቱትን ውሾች የተመገቡ አሞራዎች ወንዞችና ውሃ የተጠራቀሙባቸው አካባቢዎችና ግድቦች ላይ እንደሚጸዳዱ ገለጸ። ከዛ ውሃው እንደሚበከል አንድ ከፍተኛ የምናቡ ዓለም ባለሙያ ነገሩት። ከዛም የተበከለውን ውሃ የሚጠቀመው የፈረደበት ሕዝብ ሊያልቅ እንደሚችል በእንስፍስፍ ልቡ አስተነቀቀ።
ይህን ያየ አንድ የሎንዶን ነዋሪ ባለቤቱ የማይታወቅ ውሻ አዲስ አበባ ጎዳና ላይ ነክሶት ያየውን መከራ አጣቅሶ አቶ ኤሊያስን አውገዘ። አዲስ አበባ የውሻ መንጋ ውጧታል። አቶ ኤሊያ አሜሪካ ናቸው።
ኬንያ መከተሙ ያልተመቸው ኤሊያስ ያለውን ግንኙነትና ትሥሥር ተጠቅሞ አገሪቱን እያዳረሰ ስላለው የእርስ በርስ ወይም የተመሳሳይ ጾታ ስሪያና ግልቢያ ለምን አይነግረንም። ጋዜጠኞች ሰፈር ሳይቀር እየዳኸ ያለውን ይህን ነውር ምነው ዝም አለው። ምን አልባት ያስፈራው ነገር ይኖር ይሆን? ለማንኛውም መከባበር ጥሩ ነው!!