በአማራ ክልል 10 ሺህ 600 ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ መቀበላቸውን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቴ የሱፍ (ዶ/ር) አስታወቁ። ሰባት Xኢህ አምስት መቶ የሚሆኑት ወደ ማስለጠኛ ሊገቡ ዝግጅት ላይ እንዳሉ ተመለከተ።
እንደ ኃላፊው ገለጻ፤ በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በዘረፋ፣ ግድያና በተለያዩ የወንጀል ተግባራት ላይ የተሰማሩ የሰላም ጥሪ ተቀብለዋል። ኃ፤አፊው “ፅንፈኛ ቡድን” ሲሉ በጠሩት የታጠቀ ኃይል ላይ የተጠናከረ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑንንም አመልክተዋል።
ተጠናክሮ በተካሄደው ዘመቻ በዚህም በበርካታ አካባቢዎች መረጋጋት ተፈጥሮ ሕዝብ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሱን ኃላፊው አስታውቀዋል። ከተጠነከረው ዘመቻ ጎን ለጎን የመንግሥትን ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎችም እጃቸውን ለመንግሥት እየሰጡ መሆኑን ኃላፊው ለኢዜአ አስረድተዋል። በዚህም በተያዘው ዓመት እስከ አሁን ድረስ 10 ሺህ 600 ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ መቀበላቸውን ተረጋግጧል።
ከእነዚህ መካከል ቀደም ሲል እጅ የሰጥጡ ከሶስት ሺህ የሚልቁት የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀላቸውን ያስታወቁት ዶክተር እሸቴ፣ በቅርቡ የተካሄደውን ወጥ ዘመቻ ተከትሎ እጅ የሰጡትን ከሰባት ሺህ አምስት መቶ እጅ የሰጡ ታጣቂዎች ወደ ስልጠና ማዕከል ለማስገባት ዝግጅት መደረጉን ኃላፊው ገልጸዋል።
የሰላም አማራጭን ተከትለው ለሚመጡ ታጣቂዎች የመንግሥት እጅ አለመታጠፉን አመላክተው፤ የክልሉን ሰላም ለማወክ በሚንቀሳቀሰው ጽንፈኛ ቡድን ላይ ግን እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከኃላፊው ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter