ባንዳ ያው ባንዳ ነው! እናም አንድ ለባንዳ!
We know we hit a target so sharp !
እናም ቁንጮ ባንዳወች ክፉኛ አለቀሱ፤
የባንዳ ጩኸትም ተበራከተ!
ቁንጮ ባንዳወች ይጩሁ እንጅ ታዲያ ምን ያድርጉ ምንስ ይሁኑ ይባላል!?
ውሀ ሽቅብ እንዲፈስ አይጠበቅ፤
ባንዳም ሀገሩን ጠልቶ እንዲወጋ እንጂ ለሀገሩ እንዲሞግት አይጠበቅ!
ባንዳ ያው ባንዳ ነው! እናም አንድ ለባንዳ!
By Belete Molla
አብን በቅርቡ ያወጣውን መግለጫና በአንኳር አጀንዳወች ዙሪያ የወሰዳቸውን አቋሞች ተከትሎ ቁንጮ ባንዳወች ክፉኛ እንደሚያማቸውም ቀድሞውን እናውቅ ነበር። ይሄው አሟቸዋልና ካሉበት ተጠራርተው ለቅሶ ላይ ተቀምጠዋል!
በመግለጫችን የወሰድነው አቋም ኢትዮጵያዊውንና ባንዳውን አንጥረን የለየንበት መሆኑንም ተረድተናል።
የግዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር የባህር በር ጉዳይ፤ የሚፈጸም ፍትህ እንጅ የማይፈጸም ከንቱ ምኞት አይደለም። ውዷ ሀገራችን ኢትዮጵያም ቀና ትላለች። ዓባይን ገድባ እንዳትጠቀም ተሰቅዛ ተይዛ፣ የባህር በር ይገባኛል እንዳትል ተሰቅዛ ተይዛ አይሆንም! ዓባይን ገድባለች የባህር በር ባለቤትም ትሆናለች! ይሄንን ለትዝብትም ይሁን ለምስክርነት መዝግባችሁ ያዙት! ቁንጮ ባንዳወችም ደግሞ ለብዙ ብዙ ለቅሷችሁ ስንቅ እንዲሆን በደንብ መዝግቡት። ጉዳዩ ከንቱ ምኞት ሳይሆን የሚፈጸም ፍትህ ነው! ኢትዮጵያ አንገቷን ቀና የምታደርግበት ዘመን አሁን ነው፤ ልጆችም ዳግም ተገኝተውላታል!
ሰማዕቱ አባታችን ፕ/ር አስራት ወልደየስ ያኔ ገና በጧት ብቻቸውን ሆነው ሞግተው ነበር። ሁሉም ነገር በግዜ ይከወን ዘንድ ለነገሮች ሁሉ መሆን ወቅት ያስፈልጋልና ጩኸታቸው ያኔ የሚደመጥ ድምጽ አልነበረም። ስለሆነም ያ ወቅት የሳቸውን ጩኸት ጨርሶ ላያዳምጥ እሳቸውና ወቅቱ ተላለፉ!
ሆኖም ድምጻቸው በወቅቱ አድማጭ ቢያጣም ከንቱ ጩኸት ግን አልነበረም! ድምጻቸው በትውልዱ ውስጥ ሰርጎና አድፍጦ ቆይቶ አስቻይ “ትክክለኛ የሀገር ወቅት” ሲያገኝ reverberate አደረገ እንጅ ባክኖ የቀረ ከንቱ ጩኸት አልነበረም! እናም ይሄው ነቅቶ ለሚከታተል ዛሬ ስለኢትዮጵያ የሚሞግት ወቅት ተገልጧል! “ለሁሉም ግዜ አለው” እንዲል ጠቢቡ እነሆ ዛሬ የኢትዮጵያ ልጆች ወቅት ተገልጧል።
ይህንን ለመረዳት እይታ ያስፈልጋል። አይኖች መገለጥና መመልከት አለባቸው፣ ምልከታወችም ዙሪያገብ መሆን አለባቸው፣ ግንዛቤወች መጥለቅ አለባቸው፣ መረዳቶች መስፋት አለባቸው፣ ኢትዮጵያዊነትን ይጠይቃል!
እርግጠኛ ሆኘ የማምነው ኢትዮጵያ ሀገራችን ዛሬም ድረስ በአራቱም አቅጣጫ ቁጭት ያነገቡ ድንቅ ጀግኖች ልጆች ያሏት መሆኑን ነው። ይህ እውነት ለባንዳ መራራ ኮሶ ነው! ባንዳ ይህን አይቀበለውም። በባንዳ አለም ውስጥ ምስልና ውክልና ሁሉ የባንዳነት ነው። ለባንዳ፤ አለም ሁሉ ጨለማ ተስፋቢስና ደካማ ይመስለዋል፣ ትርጉም ሁሉ ባንዳነት ይመስለዋል!
ውሀ በተፈጥሯዊ እነሆታው ውስጥ ሲሆን ሽቅብ እንዲፈስ እንደማይጠበቀው ሁሉ፤ ባንዳ ሆኖ ሀገሩን የወደደ ከቶ በየት ታይቶ ይታወቃልና! ባንዳ ያው ባንዳ ነው!
ይህንን መሆኑም፤ ተፈጥሯዊ እነሆታው፣ መገለጡ፣ ራሱን መሆኑ፣ ለመሠረታዊ ባህሪው ታማኝ ሆኖ ሲቆም አቋቋሙ ሁሉ ባንዳነት ነው።
ባንዳ ያው ባንዳ ነው!
አብንም ህዝቡንና ሀገሩን መነሻና መድረሻ አጀንዳው አድርጎ ይቀጥላል!
ይሄው ነው!
ኢትዮሪቬውን ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች የከተሉ – የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ ፡ @ethioreview
ፌስቡክ ገጻችንን ላይክ ያድርጉ ፡ ethioreview
ኤክስ ፡ twitter