የኢቢኤስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አማን ፍስሐፅዮን የብርቱካን ቃለ ምልልስ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጫርስ አደገኛ ወንጀል መሆኑን በመጠቀስ በይፋ ይቅርታ የጠየቁበትን ቪዲዮ አቀናብረው በማሰራጨታቸው በሽብር ወንጀል የታሰሩትን ሰራተኞች አስመልክቶ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቱ CPJ “ክሱ በሽብር ክስት መታየት የለበትም” ሲል አስተያየት ሰጠ።
ብርቱካን በአደባባይ “የፈጠራ ታሪክ ነው” በማለት ምስክርነቷን የሰጠችበትን ፊልም ያሰራጩትንና ዐቃቤ ህግ የሽብር ክስ ያቀረቡባቸውን ሰባት የኢቢኤስ (EBS) ጋዜጠኞች ነው ድርጅቱ ክሳቸው የሽብር ክስ ሊሆን እንደማይገባ ያሳሰበው።
መቀመጫውን በአሜሪካ ኒውዮርክ ያደረገው ራሱን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች Committee to Protect Journalists (ሲፒጄ- CPJ) ብሎ የሚጠራው ይህ ድርጅት ይኸው ድርጅት ብርቱካን የደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲን ስም አለመጥራቷን አመልክቷል። አያይዞም የዩኒቨርስቲው ተማሪ እንዳልሆነች ገልጿል።
አርትኦት ወይም ኤዲት ባልተደርገበትና ፖሊስ እጅ ከገባው ቪዲዮ ላይ የዩኒቨርስቲው ስም ስለመነሳቱ ሲፒጄ ያለው ነገር የለም። ይህን ባያደርግም የቀረበው የብርቱካን ታሪክ “fabricated,” የፈጠራ መባሉንና ባለቤቱን በመንግስት ቴሌቪዥን ቀርበው ይቅርታ መጠይቃቸውን ክሱ ሊቃለል የሚያስችል እንደሆነ ጠቅሷል።
“አዲስ ምዕራፍ” የተባለው የኢቢኤስ ፕሮግራም አዘጋጆች ብርቱካን ተመስገን በተባለች ተከሳሽ ዙርያ በሰሩት የተቀነባበረና ከውጭ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ የተደረገበት ፕሮግራም መነሻ ለእስር መዳረጋቸውን ጠቅሰው የኤርትራ ዜግነት ያላቸው የቴሌቭዥን ጣብያው ባለቤት አቶ አማን ፍስሀፅዮን ይቅርታ መጠየቃቸውን ያልሸሸገው የሲፒጄ መግለጫ ክሱ የማይጣጣም እንደሆነ አመልክቷል።
በመግለጫው የተጠቀሱት የሲፒጄ አፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ “የጋዜጠኝነት ስርዐት ተጣሰ በሚል ጋዜጠኞችን አስሮ የሽብር ክስ መምዘዝ ያልተመጣጠነ አካሄድ ነው፣ በዛ ላይ ፕሮግራሙ እገዳ ተጥሎበታል” ብለዋል። ሙቶኪ ያልተመጠጠነ ክስ መሆኑን ቢገልጹም የቴሌቪዥን ጣቢያው አቶ አማን የተሰራጨው ፕሮግራም “ሕዝብን ከሕዝብ” ሊያጋጭ እንደሚችል መጥቀሳቸውን አስመልክቶ አስተያየት አልሰጡም።
የጣቢያው ባለቤት አቶ አማን ስርጭቱ ግጭት የሚቀስቀስ፣ ሕዝብን ከሕዝብ የሚያነሳሳ አደገኛ ይዘት ያለው፣ ሙያዊ ግዴታን ያልተከተለ፣ በግላቸው የሚያፍሩበት፣ የታቢያቸውን ተአማኒነት የሚጎዳ እንደሆነ ጠቅሰው ይቅርታ ማለታቸውን ከቪዲዮ ጋር አባሪ አድርገን መዘገባችን አይዘነጋም። የህገ-መንግስቱን ስርዐት በሀይል ለመናድ እና መንግስት ለመገልበጥ ማሴር የሚሉ ክሶችን ማቅረቡ ይታወሳል።
ነብዩ ጥኡመልሳን፣ ታሩኩ ሀይሌ፣ ህሊና ታረቀኝ እና ንጥር ደረጄ የተባሉ የኢቢኤስ ጋዜጠኞች መጋቢት 17/2017 ዓ/ም በቁጥጥር ስር መዋላቸው የሚታወስ ሲሆን ግርማ ተፈራ፣ ሄኖክ አባተ እና ሀብታሙ አለማየሁ የተባሉ ተጨማሪ የሚድያ ሰራተኞች በቀጣይ ቀናት መታሰራቸው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ፖሊስ ማስታወቁም አይዘነጋም።
የታሳሪዎቹ ጋዜጠኞች ጠበቆች የኤዲቶሪያል ችግሮች በሽብር ህጉ ሳይሆን በኢትዮጵያ የሚድያ ህግ መዳኘት እንደሚገባው ጠቁመው መከራከሪያ አቅርበው ነበር።
ሲፒጄ በጋዜጠኞቹ እስር ዙርያ የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስቴርን ለማናገር ሞክሮ ሳይሳከለት እንደቀረ ዜናውን ያሰራጩት ወገኖች አመልክተዋል። የኢትዮሪቬው የአዲስ አበባ ተባባሪ ከፍተህ ሚኒስቴር ባገኘው መረጃ ሲፒጄ ህጋዊ ጥያቄ አላቀረበም። ህጋዊ ጥያቄ በዝርዝር ካቀረበ ምላሽ የሚከለከልበት አግባብ ሊኖር እንደማይችል ጠቁመዋል። ከምንም በላይ ግን የቴሌቪዥን ጣቢያው ባለቤት በገልጽ ሕዝብን ይቅርታ የጠየቁበትና “ሕዝብን ከሕዝብ የሚያነሳሳ ነው ” ሲሉ በግልጽ ምስክር የሰጡበት ጉዳይ ስለመሆኑ በቂ መረጃ እንዳላቸው ጥርጥር እንደሌላቸው ገልጸዋል። “አስተያየታቸውን ሰጡ የተባሉት ሴትም ሰጡት በተባለው አንድ መስመር መረጃ ላይ ይህንኑ ነካ አድርገው ማለፋቸው መረጃው እንዳላቸው አመላካች ነው”
ኢቢኤስ የብርቱካንን ቪዲዮ ካሰራጨ በሁዋላ በራስዋ በበርቱካን ተማጽኖ እንዲወርድ መደረጉ ባለቤቱ ምስክርነት ሰጥጠዋል። ይህ ከሆነ በሁዋላ ፖሊስ ባድረገው ክትትል ብርቱካን ወደ ደብረብርሃን አምርታ ከፋኖ ጋር እንድትቀላቀል መዐዛ መሐመድ እና ባለደረባዋ በስልክ ሲያነጋግሯት መሰማቱ አይዘነጋም። ሲፒጄ ይህን አስመልክቶ በመግለጫው ዝርዝር አላለነሳም።
ራስዋን “እኔ ጋዜጠኛ ነኝ” በማለት አስተዋውቃት የነበርችው መዐዛ መሐመድና ባልደረባዋ በስልክ ሲያነጋግሯት “አማራ አይለቅሽም፤ መንግስትም አይለቅሽም። ወደ ደብረብርሃን ሂጂንስ ፍኖ በሚቆጣጠርበት ተቀመጪ” የሚለው የስልክ ውይይት፣ ብርቱካን የቪዲዮ ቀረጻና የስክሪፕት ልምምድ ስታደርግ የሚያሳየው ፊልም ላይ እንደታየው ዝግጅቱ ሰፊ እንደሆነ በርካቶች በወቅቱ መጠቆማቸው አይዘነጋም።