የአገር መከላከያ ሰራዊት “ከተጣለበት ጥሻ ውስጥ አገኘሁት” ያለው አውሮፕላን ዳሽ ፋይፍ ወይም ቡፋሎ ይባላል። አውሮፕላኑ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ይጠቀሙበት ነበር። አውሮፕላኑ ነው። ዛሬ የተሰማው ዜና ይህ አውሮፕላን ከ37 ዓመታት በኋላ ተጠግኖ የበረራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ነው።
ዳሽ ፋይፍ ወይም ቡፋሎ በሚል መጠሪያ የሚታወቀውና ለቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃይለ ማርያም አገልግሎት ይሠጥ የነበረው ይህ አውሮፕላን በኢትዮጵያ አየር ኃይል የጥገና ሰራተኞች ነው ነው የተጠገነው።
የጥገና ሥራው ተቋሙ በሁሉም መስክ ውጤታማ ሥራ እየሠራ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ሲሉ፤ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገልፀዋል።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው፥ አየር ኃይል በሰው ሃይል ግንባታ፣ ትጥቆችን በማሣደግና ከዘመኑ አቅም ላይ ማድረስ፣ መሠረተ ልማቶችን ተቋሙን በሚመጥን ልክ ማሥፋፋት ትኩረት የተሠጠባቸው መሠረታዊ ነጥቦች መሆናቸውን ገልፀው፤ አውሮፕላኑን ጠግኖ ወደ ኃይል መመለስ የዚሁ አንድ አካል ነው ብለዋል።
አውሮፕላኑ ለትራንስፖርት ፣ለፓራሹት ዝላይ፣ ለካርጎ አገልግሎት መሥጠት የሚችል መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።