ቅድሚያ ባህር ዳርንና አካባቢውን ፣ ሲቀጥል አዲስ አበባንና መላው አማራ ክልልን በንዴትና ቁጭት ለማነሳሳት ዝግጅቱን ያጠናቀቀውን የብርቱካን ድራማ፣ “በሀሰት ተዘርቶ፣ በሤራ ፖለቲካ ታጭዶ፣ በጥላቻ ተፈጭቶ፣ በእምባ ተቦክቶ የደም ማዕድ ሆኖ የቀረበው የብርቱካን ፊልም” ሲል ሰይሞ ዶክመታሪ ያቀረበው ፋና ይፋ ያደረጋቸው እውነታዎች ከቶውንም ሊስተባበል የሚችል አይደለም። ጥያቄው ይህን ስርጭት እዲያስተላለፍ የተመረጠው የቴሌቪዥን ጣቢያ ስራ እንዲቀጥል የፈቀደው ክፍል ጋር ያለው ጉዳይ አለመጥራቱ ነው።
“ኢቤኤስ በባለቤቶቹ የትወልድ አገር ኤርትራ እንኳን ስርጭት አስመራን መርገጥ ተከልክሎ ሳለ ኢትዮጵያን በዚህ ደረጃ ለማተራመስ በማሉ ሰዎች የተዘጋጀ ፕሮግራም አስተላልፎ እንዴት ኢትዮጵያ ውስጥ ይቆያል” የሚል ጥያቄ የሚያነሱ በርካታ ዜጎች፣ “ነገስ ተመሳሳይ ተግባር ላለመፈጸሙ ምን ማስረጃ አለ?” ሲሉ ይጠይቃሉ።
ውጥኑ ባይከሽፍ ኖሮ ሊከሰት የሚችለውን አጀንዳ የሚያነሱና ከአገር ውስጥና አገር ውጭ መረጃ ያላቸው፣ ብርቱካንን ማሸሽ ወይም መሰወር ቢቻል ኖሮ ወዲያውኑ የሚበተኑ የአድማ ጥሪዎች፣ የአድማ መቀስቀሻ አጭጭር ቪዲዮዎች፣ ቲሸርቶሽ፣ ብጥብጥ የሚያስነሱ አካላት፣ ወዘተ ዘግጅት ተጠናቆ ነበር። አስቀድመውም ሚናቸውን መወጣት የጀመሩ እንደታዩት “ልክ ጥቁር ልበሱ” ተብሎ እንደከሸፈው ኣይነት ከፍተኛ ዝግጅት ነበር።
ብርቱካን ኢቢኤስ ላይ እንድተቀረጸች የንግድ ባንኳ በሁለት ቀን ብቻ ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ገብቶላታል። ይህ ምርመራውን ወደፊት እንደሚያሰፋው ይገመታል። ከአዲስ አበባ ወደ ካናዳ፣ ከካናዳ ወደ አሜሪካ ተዘርግቶ የተሰራው ድራማ ታስቦበትና ተመክሮበት የተገባበት ለመሆኑ ራሷን “ጋዜጠኛ” የምትለው “ታጋይ” መዐዛ መሐመድ በስልክ ከብርቱካን እህት ጋር ያደረግችውን የስልክ ምልልስ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። ያገናቸቻትን ሰዎች እንደምተገናኝ ጠይቃት ይህን አለች፡፡
መዐዛ መሐመድ – …ለብርቱካን ደጋግሜ ነግሪያታለሁ። የህ ታሪክ የአንቺ ታሪክ ብቻ አይደለም። የእገሌ ታሪክ ብቻ አይደለም። የመላው አማራ ሕዝብ ሁሉ ታሪክ ነው።
እህቷ ጣልቃ ገብታ – “እንደዚህ እንደሰራች አስቀድማ ታውቃለች? ትላለች
መዐዛ መሐመድ – ኢቢሲ ላይ ከሰራች ምኑን ነው የማታውቀው? ኢቢሲ መጥታ ቀርጸዋታል። እኔ በግልጽ ነው የምነግርሽ። እንደ እህት ነው የምነግርሽ። መደበቅ አለባት። ሚዲያ ላይ ሳይወጣ ነው የነገርኳት። ሚዲያ ላይ ከወጣ መንግስት ይገልሻል ብያታለሁ። ይህ የመንግስትን ትልቅ፣ትልቅ ፖለቲካ ነው የሚያበልሸው። ቀልድ አይደልም። ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ ነው [ፖለቲካውን የሚያበላሸው] የአሜሪካ መንግስት እኮ ያውቀዋል ይህን ጉዳይ። ቀልድ መስሎሽ ነው? እግዚአብሄር ምስክሬ ነው። እኔ በልጄ ነው የምምልልሽ። የአሜሪካ መንግስት ድረስ እኮ አሳውቀናል።
በልጇ ምላ፣ የእግዜአብሄርን ስም ጠርታ ሴራውን የምትተነትነው መዐዛና ይህንኑ የተመከረበትና በጀት ተመድቦለት የተከናወነ ድራማ የከወኑ ተጠቃለው “ጋዜጠኛ” ተብለው እነ ሲፒጄና የመብት ተቆርቋሪ ነን የሚሉ አገር በቀል ድርክጅትና ዜጎች ጩኸት የሚያሰሙት።
ሉላ የምታባለው የኢቢኤስ አቅራቢ ለፖሊስ እንዲህ ብላለች። በጉዳዩ ትኑርበት አትኑርበት ለራስዋና ለፖሊስ ቀጣይ ምርመራ ትተነው ምስክርነቷን ስንመለከት “አልገባኝም” በሚል ነው የምንትጀምረው። እሷ ብቻ ሳትሆን በዚህ ደረጃ አመጽ ለመቀሰቀስ የተፈለገበት ምክኛት ለበርካቶች አልገባቸውም።
“ምን ተፈልጎ እንደሆነ እስካሁን ለራሴም ያልተመለሰልኝ ጥያቄ ነው”:- ሉላ ገዙ
የብርቱካን ያልሆነው የብርቱካን ታሪክ ለምን በዚህ ደረጃ በሀሰት መስራት እንዳስፍለገ እስካሁን ያልተመለሰልኝ ጥያቄ ነው ትላለች በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አስተዋዋቂዋ ሉላ ገዙ።
ሉላ ገዙ “የብርቱካን ያልሆነው የብርቱካን ታሪክ” በሚል ርእስ በተሰራው የምርመራ ዘገባ ላይ “የሰው ልጅ ለምን በዚህ ልክ ሊሆን ይችላል? በቃ ስጠይቅ የነበረው እንዴት? ለምን? ምን ተፈልጎ ነው? እስካሁንም ያልተመለሰልኝ ጥያቄ ነው ለራሴም” ብላለች።
“በብርቱካን ታሪክ ላይ ከተለመደው ወጣ ያለብኝ ከዚህ በፊት አንድ ሴት ከተደፈረች ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ ክስ ተጀምሮ አንዳንዴም ውሳኔ የተሰጠበት ታሪክ ይመጣል፤ የብርቱካን ታሪክ ግን ምንም ዓይነት ክስ አልነበረም” ስትል ሉላ ለፖሊስ በሰጠችው የእምነት ቃል ገልፃለች።
“በኢቢ ኤስ አንድ ባለታሪክ ጉዳት ደረሰብኝ ካለ ጉዳት የደረሰበትን ቦታ ለምሳሌ አይን፣ ጆሮ፣ ራስ፣ የቁስል ለውጥ ካለ በካሜራ ተለይቶ ይቀረጽ ነበር። ነገር ግን የብርቱካን ታሪክ ላይ ጭንቅላቷን ‘በቢላዋ ፈቅፍቀውኛል’ ብላ ብትናገርም ጭንቅላቷ ላይ ያለውን ነገር የሚሳይ የተቀረፀ ነገር አልነበረም” ስትል ነው ቃሏን ለፖሊስ የሰጠችው።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት፦ https://youtu.be/rswIl7mVC-8

የብርቱካን ታሪክ ልክ እንደ ምርጥ ፊልም ድርሰት ተዘጋጅቶለት፣ ድርሰቱ ተጠንቶ ዳይሬክተር ተመድቦለት በብርቱካን ዋና ገጸ ባህሪነት የተተወነ የፈጠራ ድርሰት ነው ይላል ኢቢሲ።
የብርቱካንን ጉዳት ለማሳየት ሜካፕ ተሠርቶ ሀዘኗን ለመግለጽ ቪክስ ቀብተዋት በማስለቀስ ነው ትወናው እውነት እንዲመስል በደንብ ዝገጅት የተደረገበት።
ይህ በሀሰት ተዘርቶ፣ በሤራ ፖለቲካ ታጭዶ፣ በጥላቻ ተፈጭቶ፣ በእምባ ተቦክቶ የደም ማዕድ ሆኖ የቀረበው የብርቱካን ፊልም የተሠራው እንዴት ነበር?
የፊልሙ ደራሲያን እና አዘጋጆች በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የመንግሥት መዋቅር ውስጥ የመሸጉ ሴረኞች፣ በጋዜጠኝነት ሽፋን ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ውስጥ የመሸጉት እና ውጭ ሀገር ሆነው የራሳቸውን የፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት የሕዝብን ስቃይ የሚዘሩት ቡድኖች ጥምር ውጤት ነው።
መቼቱ ከአዲስ አበባ እስከ ካናዳ፣ ከሀዋሳ እስከ አሜሪካ የተዘረጋው ይህ ፊልም ዋና ዓላማው ሕዝብን አደናግሮ ቁጣ በመቀስቀስ እልቂት እንዲፈጸም ማድረግ ነው።
ቀድሞውንም የደምቢ ዶሎን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታሪክ ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ በማምጣት በነጩ ቤተመንግሥት የተሸለመችበት መዓዛ መሐመድ እና አጋሯ ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ከአዲስ አበባ የሴራ ተባባሪዎቻቸውን መርጠው በኢቢኤስ ቴልቪዥን የአዲስ ምዕራፍ ታሪኩ ኃይሉ የተጻፈውን የሴራውን ድርሰት ሰጥተዋቸዋል።
በአዲስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 ሠራተኛ የሆነው ልጅ አዲስ ተዋንያን እንዲያዘጋጅ በተሰጠው ተልዕኮ መሰረት ወዳጅነት የሚመስል ግንኙነት በመፍጠር ተዋናይ መረጣውን በብቃት ተወጥቷል።
ዋለልኝ፣ ካሳሁን እና ሌሎች ለጉዳዩ የሚያስፈልጉ ሰዎች ተመርጠው ሀዋሳ እና አዲስ አበባን ማዕከል በማድረግ የፊልሙን ቀረጻ አከናወኑ፤ ይህን ሲያደርጉ ታሪኩ እውነት እንዲመስል የሚችሉትን ሁሉ ጥረት አድርገዋል።
ልጅ አዲስ እና እዚያው አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሠራተኞች የሆኑት የሤራ ተባባሪዎቹ ለዋና ገጸ ባሕሪዋ ብርቱካን የሀሰት መታወቂያ አዘጋጅተው ሰጥተዋታል፤ የመታወቂያውን አድራሻ ለመስጠት ደግሞ ቤታቸውን ቀደም ብለው ሽጠው ከወረዳው የለቀቁ ነገር ግን ፋይላቸውን ያልዘጉ ዶክተር ተመስገን የሚባሉ ሰውን ፋይል ተጠቅመዋል።
ዶክተር ተመስገን እንደሚሉት እሳቸው ሲያውቁ በፋይላቸው የተመዘገቡት ስድስት ሰዎች ብቻ እንደነበሩ እና በኋላ ሲደርሱበት ግን 14 ሰዎች ተመዝግበው አግኝተዋል።
ይህ ሁሉ ከተከናወነ በኋላ ኢቢኤስ ቴሌቪዥንን መርጠው የሴራውን ጥልፍልፍ የሚያፋጥኑ ሰዎች ከአዲስ አበባ ካናዳ ከዚያም አሜሪካ ተገናኝተው መክረውበት ሥራውን አከናውነዋል።
ብርቱካን እንደምትናገረው ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ እሷ ያልገባት እንቅስቃሴ ተጀመረ፤ እሷ የፊልም ጽሑፉን ጥናት ጨርሳ በፊልም ዳይሬክተሩ ታግዛ የፊልሙ ቀረጻ በሚፈለገው ቦታ ከተከናወነ በኋላ ጉዳዩ እንዳይነሳ ብርቱካንን አስጠንቅቀዋት ቀረጻው እነሱ በሚፈልጉት መንገድ ተጠናቀቀ።
ዝግጅቱ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ከቀረበ በኋላ እነ መዓዛ መሐመድ እና ሌሎች በውጭ የሚገኙ የድራማው ጠንሳሾች ጉዳዩን በደንብ አራገቡት፣ ለጊዜውም ግርታን ቢፈጥርም ውሎ አድሮ አውነታው ተደረሰበት።
የፈራችው ባይቀርላትም አውነታው እንደሚወጣ ቀድማ የተረዳች የምትመስለው መዓዛ መሐመድ ከብርቱካን እህት አዱኛ ተመስገን ጋር ባደረገችው የስልክ ንግግር ይህ ነገር ከወጣ በጣም አደገኛ እንደሆነ፣ እንኳን ምንም ጉዳዩ ውስጥ የሌለችበት ብርቱካን ቀርቶ እውነተኛ ታሪክ እንኳን ቢሆን ከተሰማ ጥያቄ እንደሚያስነሳ አስጠንቅቃታለች።